ኬሪ ሌክ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ኤጀንሲ ልዩ አማካሪ ኾኑ
newsare.net
ፖለቲከኛ እና የቀድሞ ጋዜጠኛ የነበሩት ኬሪ ሌክ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ኤጀንሲ (ዩ.ኤስ.ኤ.ጂ.ኤም.) አማካሪ ኾነው መሾማቸውን ተቋሙ ፣ ሐሙስ የካኬሪ ሌክ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ኤጀንሲ ልዩ አማካሪ ኾኑ
ፖለቲከኛ እና የቀድሞ ጋዜጠኛ የነበሩት ኬሪ ሌክ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ኤጀንሲ (ዩ.ኤስ.ኤ.ጂ.ኤም.) አማካሪ ኾነው መሾማቸውን ተቋሙ ፣ ሐሙስ የካቲት፣ 20 ቀን 2017 ዓ.ም አስታወቀ። ላለፉት 30 ዓመታት በጋዜጠኝነት ያገለገሉት ኬሪ ሌክ፣ በመንግሥት ለሚደገፈውና ዓለም አቀፍ ሥርጭት ላለው አሜሪካ ድምፅ በዲሬክተርነት እንዲሾሙ መታጨታቸውን፣ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም አስታውቀው ነበር። ኾኖም የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ኤጀንሲን (ዩ.ኤስ.ኤ.ጂ.ኤም.) በዋና ሥራ አስፈፃሚነት እንዲመሩ በትረምፕ የተመረጡት፣ ወግ አጥባቂ ሐሳቦች አራማጅ እና ጸሐፊው ኤል ብሬንት ቦዜል ሹመት፤ የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት)ማረጋገጫ በመጠባበቅ ላይ በመኾኑ የኬሪ ሌክ ሹመት አጓቶታል። ሚዲያ ኤጀንሲንው፣ የተለያዩ እህትማማች ተቋማት ኃላፊዎችን መሾም ወይም ማሰናበትን ጨምሮ ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋራ አብሮ የሚሠራ፣ ከሁለቱ ፓርቲዎች የተዋቀረ ቦርድ እስኪሰየም በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። የኤጀንሲው የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አማንዳ ቤኔት፣ ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኾነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ሮማን ናፖሊ፣ ሌክ በልዩ አማካሪነት መቀላቀላቸውን ለተቋሙ ሠራተኞች በላኩት ኢሜል አስታውቀዋል። “ከሁለት ዐስርት ዓመታት በላይ በታላላቅ ብዙኅን መገናኛ ውስጥ በዘጋቢነት እና ዜና አቅራቢነት ያገለገሉት ሌክ፣ በብሮድካስት ጋዜጠኝነት ውስጥ ብዙ ልምድ አላቸው” በማለት ናፖሊ አክለዋል። ናፖሊ የሌክን ስኬት በማጉላትም፣ ከዚኽ ቀደም ለኹለት የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ቃለ መጠየቅ ማድረጋቸውን እና በዓለም አቀፍ ዘገባዎች ምክኒያት ሁለት ጊዜ የኤሚ ሽልማት መቀበላቸውን፣ ጠቅሰዋል። «ኬሪ የትረምፕ አስተዳደር ከፍተኛ አማካሪ እንደመኾናቸው፣ የሚዲያ ኤጀንሲውን፣ የእህትማማች ተቋማቱን እና የፈንዱን ሥራ ለማቀላጠፍ፣ የሚያስፈልጉትን ፖሊሲዎች እና ስልቶች ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛሉ»ሲሉ ናፖሊ በኢሜል መልዕክታቸው ጠቅሰዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ኤጀንሲ (ዩ.ኤስ.ኤ.ጂ.ኤም.)፣ ከ420 ሚሊዮን በላይ የሚኾኑ ዓለም አቀፍ አድማጮችና ተመልካቾችን ያላቸው፣ በዜና ዘገባ እና ቅድመ ምርመራ ወይም ሳንሱርን በመዋጋት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የሚሠሩ በርካታ ተቋማትን ይቆጣጠራል። በዩ.ኤስ.ኤ.ጂ.ኤም. ሥር የሚገኙ እነዚኽ እህትማማች ድርጅቶች፣ የአሜሪካ ድምፅ፣ የኩባ ብሮድካስቲንግ ቢሮ (Cuba Broadcasting) እና ለትርፍ ያልተቋቋመው የነፃ አውሮፓ ራዲዮ ወይም ራዲዮ ሊበርቲ (Free Europe/Radio Liberty)፣ የነፃ እሥያ ራዲዮ(Radio Free Asia)፣ የመካከለኛው ምሥራቅ ብሮድካስቲንግ መረብ እና የኦፕን ቴክኖሎጂ ፈንድ እና የፍሮንት ላይን ፈንድን ናቸው። የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ሚዲያ ኤጀንሲ (ዩ.ኤስ.ኤ.ጂ.ኤም.)፣ የሕዝብ ጉዳዮች ክፍል የኬሪ ሌክን ሹመት በተመለከተ ለአሜሪካ ድምፅ ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም። «ፋየርዎል» በመባል የሚታወቀው የኢዲቶሪያሉ ገለልተኝነት መጠበቂያ፣ ዩ.ኤስ.ኤ.ጂ.ኤም በሚያስተዳድራቸው ብዙኅን መገናኛ የጋዜጠኝነት ሥራ ውጤት ላይ ጣልቃ እንዳይገባ ይከለክላል። ሌክ በዓመታዊው የወግ አጥባቂ አቀንቃኞች የፖለቲካ ጉባኤ ላይ በሰጡት አስተያየት የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ሚዲያ የቀረበበትን ትችት በንግግራቸው ዳሰዋል፡፡ ሌክ ለታዳሚው እንደ ቪኦኤ ዲሬክተር የዜና ተቋሙ “ትክክለኛ እና ታማኝ ዘገባዎችን” ማዘጋጀቱ ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ሌክ አክለው ፣ “የፊታችን ሰኞ 83 ዓመት የሚኾነው ቪኦኤ አሜሪካን ታሪክ ለዓለም ሲያቀርብ ቆይቷል። አንዳንድ ጊዜ በዜና ሽፋኑ አስደናቂ ሲኾን በሌሎች ወቅቶች ደግሞ አሳዛኝ ነበር” ብለዋል፡፡ አያይዘውም “እኛ የምንዋጋው የመረጃ ጦርነት ነው፤ በመሆኑም ከእውነት የተሻለ መሳሪያ የለም፣ እናም ቪኦኤ ይህ መሳሪያ ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ” በማለት ተናግረዋል፡፡ የዜና ጣቢያው እንዲዘጋ ከጠየቁት መካከል የትራምፕ ልዩ አማካሪ ኢላን መስክ ይገኙበታል። ይሁን እንጂ ሌክ “የትራምፕ ቴሌቭዥን አንሆንም” በማለት የተናገሩ ሲኾን፤ “ሆኖም ግን ዲጂታል ኬብል ቴሌቭዥን እንደማንኾን ግን እርግጠኛ ነው” ብለዋል፡፡ አክለውም “ትረምፕን ምክኒያታዊ ባልኾነ መልኩ መተቸትን ከሲ.ኤን.ኤን፣ ኤም.ኤስ.ኤም.ቢ.ሲ፣ 60 ደቂቃ፣ ዘ ዋሺንግተን ፖስት እና ከኒውዮርክ ታይምስ ልታገኙ ትችላላቹ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ኬሪ ሌክ በኮቪድ 19 ወረርሽኙ ወቅት የተሳሳተ መረጃ ነው ብለው ባመኑት መረጃ ምክንያት ከአሪዞና የዜና ጣቢያ ሥራቸውን ለቀዋል። በኋላም ለአሪዞና ሀገረ ገዥነት ተወዳድረ ያልተሳካላቸው ሲኾን ሽንፈታቸውን ባለመቀበል ክስ መስርተዋል። በመቀጠልም ለግዛቱ ሴናተርነት ያደረጉት ውድድርም አልተሳካላቸውም። Read more