የዩክሬኑ ዜለንስኪ በእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ስታርመር ሞቅ ያለ አቀባበል ተደረገላቸው
newsare.net
የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋራ የተጋጋለ ኃይለ ቃል ከተለዋወጡ ከአንድ ቀን በኋላ ለንደን ሲደርየዩክሬኑ ዜለንስኪ በእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ስታርመር ሞቅ ያለ አቀባበል ተደረገላቸው
የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋራ የተጋጋለ ኃይለ ቃል ከተለዋወጡ ከአንድ ቀን በኋላ ለንደን ሲደርሱ፣ በእንግሊዝ ጠቅላይ ምኒስትር ኪር ስታርመር ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ሁለቱ ሀገራት የዩክሬን የመከላከያ አቅምን ለመደገፍ የ2.84 ቢሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ይፋ ያደረጉ ሲኾን፤ ብድሩ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች ሽያጭ ትርፍ ላይ የሚከፈል ነው። ሞስኮ ኪየቭን በወረረችበት ወቅት፣ የአውሮፓ ባለሥልጣናት፣ ከሩስያ ውጭ የሚገኙ ማንኛውንም የሩሲያ ንብረቶችን እንዳይንቀሳቀሱ በማገድ፣ ሞስኮን ለመቅጣት መወሰናቸው ይታወሳል። ዜለንስኪ በዶውኒንግ ጎዳና ከአቻቸው ስታመር ጋራ ፎቶ ለመነሳት ለአፍታ የቆሙ ሲሆን፤ እንግሊዛውያን በጩኸት ድጋፋቸውን አሳይተዋቸዋል። ስታመርም ለዜለንስኪ “በዳውኒንግ ጎዳና ሁሌም እንቀበሎታለን” ብለዋቸዋል። አክለውም፣ «ከቤት ውጭ በጎዳናው ላይ እንደሰሙት፣ በዩናይትድ ኪንግደም ሙሉ ድጋፍ አሎት፣ ምን ዐይነት ጊዜ ቢወስድም ሁሌም ከዩክሬን እና ከእርሶ ጋራ እንቆማለን» ብለዋቸዋል። ሁለቱ መሪዎች 75 ደቂቃ የፈጀ ውይይት ካደረጉ በኋላ ስታመር ዜለንስኪን እስከ መኪናቸው ድረስ ሸኝተዋቸዋል። ምንም እንኳን የትረምፕ እና ዜለንስኪ ውይይት ባለመግባባት ቢጠናቀቅም፣ የትረምፕ ድጋፍ ለዩክሬን በእጅጉ አስፈላጊ መኾኑን ዜለንስኪ ትላንት ቅዳሜ አጽንኦት ሰጥተውበታል። Read more