“አኖራ” የኦስካር አሸናፊ ፊልም
newsare.net
አኖራ” የተሰኘው ፊልም እሑድ ምሽት 97ኛው የኦስካር አካዳሚ ሽልማቶች (አካዳሚ አዋርድስ) ላይ የምርጥ ፊልም አሸናፊ ሆኗል። አስቂኝና የመረረ የህይወት የተሞላ“አኖራ” የኦስካር አሸናፊ ፊልም
አኖራ” የተሰኘው ፊልም እሑድ ምሽት 97ኛው የኦስካር አካዳሚ ሽልማቶች (አካዳሚ አዋርድስ) ላይ የምርጥ ፊልም አሸናፊ ሆኗል። አስቂኝና የመረረ የህይወት የተሞላበት የብሩክሊኑ ፊልም ዳይሬክተር ሾን ቤከርን፣ በሆሊውድ ትልቁንና ተደራራቢውን ሽልማት እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡ እርቃን በሚደነስበት ቤት (strip club) ውስጥ ያጠነጠነው የሲንደሬላ ገጸባህርይ ታሪክ፣ በአዲስና ባልተለመደ አጨራረስ የቀረበ ፊልም ነው፡፡ ከጥንታዊው የሲንደሬላ ተረት በጣም በተለየ መልኩ፣ ነባሩ ታሪክ ላይ ቆሞ፣ አዲሱን ያሳየ ዘመናዊ ፊልም ነው፡፡ በሽልማት ስነስርዐቱ ላይ የነበሩ ብዙ ሰዎች በጣም የተለየ ሥራ ነው ሲሉ አድንቀውታል። ምክንያቱም አቀራረቡ የተለየ ነበር፡፡ ፊልሙ በህይወት ውስጥ ብዙ ፈተናዎች ስላጋጠሟት አንዲት ወጣት ታሪክ ይተርካል። በሲንደሬላ ታሪክ ሲገለጽ እንደቆየው ህይወት ሄዶ ሄዶ ፍፃሜዋ በአስደሳች አስማት ይቋጫል፡፡ የሲንደሬላ ታሪክ እንዲያ ሆኖ ሲተረክ ቢኖርም፣ የአኖራ ህይወት ግን ውስብስብ ሆኖ የህይወት ማለቂያው የተለየ ሊሆን እንደሚችል አሳይቷል፡፡ በተረት ላይ የተመሰረተው ፊልም ህይወትን ግን ተረት ተረት አላደረጋትም፡፡ እውነተኛ ሕይወት ፍጹም ባይሆንም አስደሳች እንደሚሆን አስተምሯል። ፊልሙ ጠንክሮ መሥራት እና መታገል ታሪክን ጠንካራ እንደሚያደርገው አሳይቷል። ሕይወት ውጣ ውረዶች እንዳላት ለሁሉም አስታውሷል፡፡ አሸናፊው ማን እንደሆነ ግራ መጋባት በሰነፈነበት የኦስካር ወቅት፣ አኖራ ባልተጠበቀ መልኩ አሸናፊ ሆኖ ወጥቷል፡፡ በርግጥ ቀደም ሲልም በካነስ ፊልም ፌስቲቫል አሸናፊ ሆኗል፡፡ የቤከር ፊልም ከሩሲያው ባለጸጋ ጋር በፍቅር ነሁልላ ስለከነፈቸው የምሽት ዳንሰኛ ይተርካል፡፡ 6 ሚሊዮን ዶላር ብቻ የፈጀው ፊልም ያን ለመሰለ ድል መብቃቱ አስገርሟል፡፡ አሸናፊዎቹን የሚወስኑት የኦስካር ድምጽ ሰጭዎች ግን እንደ ዊክድ ወይም ዱን ክፍል ሁለት የመሳሰሉትን ትላልቆቹን (“የብላክባስተር”) ፊልሞችን አልመረጡም፡፡ ቤከር ትላንት እሁድ አራት የኦስካር ሽልማቶችን በማሸነፍ እኤአ በ1954 አራት ሽልማቶችን ያሸነፈው ዎልት ዲሲን ያስመዘገበውን ሪከርድ ደግሟል፡፡ ሌላው “ዘ ፍሎሪዳ ፕሮጀክት” የተሰኘው የቤከር ፊልም የተሰራው ፍሎሪዳ ውስጥ ከዲዝኒላንድ ብዙም በማይርቀው ትንሽ ሞቴል ውስጥ ነው። በትላንቱ ምሽት ሌሎች በርካታ ሽልማቶች የተሰጡ ሲሆን “ዘ ፒያኒስት” በተሰኘው ፊልም ላይ አሸናፊ የነበረው ተዋናዩ አድሪያን ብራዲ ተመሳሳይ የኦስካር ሽልማት አሸነፏል፡፡ ብራዲ ያሸነፈው የሆሎኮስት እልቂት እስረኛ ሆኖ በተጫወተው “ዘ ብሩታሊስት” በተሰኘው ሌላ ተመሳሳይ ፊልም ነው፡፡ ሚኪ ማዲሲን “አኖራ” ላይ ባሳየችው ትወና ምርጥ የሴት ተዋናይ በመሆን አሸንፋለች፡፡ ሾን ቤከር ምርጥ ዳይሬክተር ፣ ምርጥ ስክሪፕት ጸሀፊና ምርጥ ኤዲተር በመሆን ተደራራቢ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ ለምርጥነት ከታጩት 10 ፊልሞች ስምንቱ ቢያንስ አንድ ሽልማት አግኝተዋል፡፡ የሁለት ሽልማቶች አሸናፊ በሆነው ዊክድ ፊልም ላይ የተጫወተችው እውቋ ድምጻዊ አሪያና ግራንዴ እና ሲንቲያ ኢሪቮ የሽልማቱን ስነስርዓቱን የጀመሩት በዚህ ዓመት መግቢያ ላይ በደቡብ ካሊፍሮኒያው እሳት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን በማሰብ ነው፡፡ ግራንዴ Somewhere Over the Rainbow« የተሰኘው ዜማዋን የተጫወተች ሲሆን ኢርቪም የዳያና ሮስን “Home» አዚማለች፡፡ የፊልም ኢንደስትሪው ዙሪያ በጣም አስቸጋሪ የሆኑ በርካታ ነገሮች በመከሰታቸው የዘንድሮው የኦስካር ሽልማት በጣም ያልተጠበቀ ነበር። የቲኬት ሽያጩ ከአምናው በ3 በመቶ የቀነሰ ሲሆን ከኮቪድ ወረርሽኙ በፊት ከነበረው በጣም አንሷል። እ.ኤ.አ. በ2023 የተከሰቱት የሥራ ማቆም አድማዎች በ2024 ፊልሞችን ለመለቀቅ አስቸጋሪ አድርጎታል። ብዙ ስቱዲዮዎች አነስተኛ ፊልሞችን ሰርተዋል፣ ብዙ ሰዎች ሥራቸውን አጥተዋል። በጥር ወር የተከሰቱት የእሳት ቃጠሎዎችም ሁሉንም ነገር የበለጠ ከባድ አድርገውታል። Read more