ለሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ለመጸለይ ምእመናን በጴጥሮስ አደባባይ ተሰባስበዋል
newsare.net
በመተንፈሻ አካላት ሕመም ሳቢያ ጥብቅ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ለሚገኙት የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ለመጸለይ ከዓለም ዙሪያ የተጓዙ፣ በርለሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ለመጸለይ ምእመናን በጴጥሮስ አደባባይ ተሰባስበዋል
በመተንፈሻ አካላት ሕመም ሳቢያ ጥብቅ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ለሚገኙት የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ ለመጸለይ ከዓለም ዙሪያ የተጓዙ፣ በርካታ ምእመናን ዛሬ ማክሰኞ ሮም በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተሰባስበዋል። ቫቲካን በትላንትናው ዕለት ይፋ እንዳደረገችው በሮሙ የጌሜሊ ሆስፒታል የሚገኙ ሃኪሞች ከሊቀ ጳጳሱ ሳንባ ከፍተኛ መጠን ያለው ፈሳሽ አውጥተዋል። የሕክምና አገልግሎቱ በተደረገላቸው ወቅት አባ ፍራንሲስ እንደነበሩ እና ቆይቶም ሰውነት ውስጥ ዘልቆ ሳይገባ መደረግ የሚችል አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ እንደተደረገላቸው ታውቋል። አባ ፍራንሲስ ካለፈው የካቲት 7 ጀምሮ፣ ሁለቱንም ሳንባቸውን ላጠቃ የሳንባ ምች እና የተወሳሰበ የመተንፈሻ አካላት ሕመም ሕክምና ሲደረግላቸው ቆይተዋል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር መጋቢት 2013 ጀምሮ የጵጵስና ሥልጣናቸውን የተረከቡት አባ ፍራንሲስ፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ፣ ለረዥም ጊዜ ከአደባባይ ለመራቅ የተገደዱበት የአኹኑ የመጀመሪያው ነው። አባ ፍራንሲስ ሌሊቱን ሙሉ በጥሩ ሁኔታ ተኝተው ማደራቸውን ቫቲካን ይፋ አድርጋለች። ማምሻው ላይም የተሟላ የጤና ሁኔታቸውን የሚያሳይ የሕክምና መረጃ ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል። አባ ፍራንሲስ ገና ወጣት ሳሉ የሳምባቸው ክፍል ተቆርጦ እንዲወጣ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ለመተንፈሻ አካላት ሕመም ሲጋለጡ ቆይተዋል። Read more