ግጭት በቀጠለባት ኢትዮጵያ በወባ ወረርሽኝ የሚሞተው ሰው ቁጥር እየጨመረ መኾኑ ተነገረ
newsare.net
በአንድ ወር ዕድሜ ውስጥ አራት ሕጻናት ልጆቻቸውን በወባ ወረርሽኝ መነጠቃቸውን ሳግ እየተናነቃቸው የተናገሩት አቶ ለማ ተፈራ፤ በሚኖሩበት የኦሮሚያ ክልል የቀግጭት በቀጠለባት ኢትዮጵያ በወባ ወረርሽኝ የሚሞተው ሰው ቁጥር እየጨመረ መኾኑ ተነገረ
በአንድ ወር ዕድሜ ውስጥ አራት ሕጻናት ልጆቻቸውን በወባ ወረርሽኝ መነጠቃቸውን ሳግ እየተናነቃቸው የተናገሩት አቶ ለማ ተፈራ፤ በሚኖሩበት የኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት ባይኖር ኖሮ የልጆቻቸውን ሕይወት ማትረፍ ይቻል ነበር ብለው እንደሚያምኑ ያስረዳሉ። አርሶ አደሩ አክለውም “በግጭቱ ሳቢያ መንደራችን ውስጥ ለወባ መከላከያ የሚረዳው መድኃኒት እና የሕክምና አገልግሎት አልነበረም" ሲሉ በስልክ ላነጋገራቸው የኤኤፍፒ ዘጋቢ አስረድተዋል። በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ከሚከሰተው ቁጥሩ ከ250 ሚሊዮን በላይ የወባ ተጋላጭ እና በዚሁ ወረርሽኝ ሳቢያ ለሕልፈት ከሚዳረገው ከ600 ሺሕ በላይ ሕዝብ 95 በመቶው አፍሪካውያን መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ባለፉት በርካታ ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በመንግሥቱ ኃይሎች እና በአማፂው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦላ) መካከል ተባብሶ የቀጠለው ግጭት የጤና አገልግሎት አቅርቦቱን ክፉኛ እያስተጓጎለ መኾኑን ባለሞያዎች ይገልጻሉ። በርካታ ልጆቻቸውን በወባ ወረርሽኝ ሳቢያ ላጡት እና የሰባት ልጆች አባት እንደሆኑት እንደ አቶ ለማ ላሉ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ገቢ ለሚተዳደሩ አርሶ አደሮች ሁኔታው ቀድሞውንም ከባድ እንደነበር ያስረዱት ሃኪሞች፣ ሌሎች ባለሞያዎች እና የርዳታ ሠራተኞች ለኤኤፍፒ በሰጡት አስተያየት አክለውም፤ የአየር ንብረት ለውጡ እና በአካባቢው የቀጠለው ግጭት ተዳምረው ሁኔታውን እጅግ የከፋ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። በተያያዘ ዜና ካለፈው ዓመት ጥር ወር አንስቶ እስከ ጥቅምት ድረስ በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ7.3 ሚሊዮን በላይ የወባ ወረርሽኝ ተጋላጮች እና 1,157 የሚደርስ የሟች ቁጥር መመዝገቡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ይህም አሃዝ በቀደመው የአውሮፓውያኑ 2023 ከተመዘገበው በእጥፍ መጨመሩ እና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከታየው እና ለሕልፈት ከተዳረጉት ግማሽ ያህሉ በኦሮሚያ መሆኑ ተመልክቷል። Read more