ዓመታዊው የቻይና የፖለቲካ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ በቤጂንግ ላይ የጣለችው ቀረጥ ተፈጻሚ ከሚሆንበት ዕለት ጋር ተገጣጥሟል
newsare.net
ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ላይ የጣለችው ተጨማሪ ቀረጥ በጀመረበት እና ፕሬዝዳንት ሺ «ውስብስብ እና ዘርፈ ብዙ» ያሏቸውን የምጣኔ ፈተናዎች ለመፍታት የሚዓመታዊው የቻይና የፖለቲካ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ በቤጂንግ ላይ የጣለችው ቀረጥ ተፈጻሚ ከሚሆንበት ዕለት ጋር ተገጣጥሟል
ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ላይ የጣለችው ተጨማሪ ቀረጥ በጀመረበት እና ፕሬዝዳንት ሺ «ውስብስብ እና ዘርፈ ብዙ» ያሏቸውን የምጣኔ ፈተናዎች ለመፍታት የሚያስችሉ መላዎች ፍለጋ በያዙበት ባሁኑ ወቅት፤ ቻይና ዓመታዊውን ታላላቅ የፖለቲካ ጉባኤዋን ጀምራለች። ከዛሬ አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ የቻይና ልሂቃን እና የሃገሪቱ ምክር ቤት አባላት የ2025ቱን የፖሊሲ አጀንዳዎች ለመቅረጽ የሚያግዝ መሆኑ በተነገረለት ጉባኤ መሳተፍ ይዘዋል። ከንግዱ ማሕበረሰብ እና ከከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት እስከ የአገሪቱ መንግሥት እና የፓርቲው የፖለቲካ አማካሪዎች ጉባኤ ሰፊ የሕዝብ ውክልና ያላቸው ከተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገናኝተዋል። ነገ ረቡዕ በአመዛኙ የመንግሥቱን አመለካከት የሚያስተጋባው ብሔራዊ ምክር ቤት፣ ዓመታዊውን የሕግ አውጭዎች ጉባኤ ይጀምራል። ጠቅላይ ሚንስትር ሊ ኪያንግ በበኩላቸው በሥፋት የሚጠበቀውን የመንግሥቱን የ2025 የኢኮኖሚ እድገት እና ሌሎች ቁልፍ የምጣኔ ሃብት ፖሊሲዎች የሚያስረዳውን የመንግሥቱን የሥራ ሪፖርት በምክር ቤቱ የመክፈቻ ጉባኤ ላይ ያቀርባሉ። የዘንድሮው ጉባኤ የሚካሄደው የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በእጅጉ በተዳከመበት፣ የአገር ውስጥ ገበያ ፍላጎት በተቀዛቀዘበት፣ ባለ ሃብቱ እና ሸማቹ በኢኮኖሚው ይዞታ ላይ ያለው ዕምነት ባዘቀዘቀበት፣ በንብረት ባለቤትነቱ ዘርፍ የታየው ቀውስ በቀጠለበት ብሎም በዓለም አቀፉ የንግድ ዘርፍ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የተጀመረው የንግድ ጦርነት አንድምታ እያጠላ ባለበት ባሁኑ ወቅት ነው። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በሁሉም የቻይና ምርቶች ላይ የጣለው ተጨማሪ የ10 በመቶ ቀረጥ ዛሬ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል። በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፈተናዎች በተደቀኑበት የሚካሄደው የዘንድሮው የብሔራዊ ምክር ቤቱ ጉባኤ፣ የቻይና መሪዎች “የፖለቲካ አንድነት” ፕሮጀክት ለመንደፍ እና አገሪቱ “በሺ ጂንፒንግ አመራር ታላቅ ሃገር ለመሆን በሚያበቃት ትክክለኛ መንገድ ላይ መሆኗን ለማሳየት መልካም አጋጣሚ ለማድረግ ይጠቀሙበታል” ሲሉ ተንታኞች አስተያየታቸውን ፈንጥቀዋል። Read more