ኬንያ ውስጥ በስደተኞች የምግብ ዕደላ ወቅት በተቀሰቀሰ ግጭት ተረጂዎች ተጎዱ
newsare.net
ሰሜን ኬንያ በሚገኘው ካኩማ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት ፖሊስ በወሰደው ርምጃ አራት ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ። በትላንቱ የምግብ ዕኬንያ ውስጥ በስደተኞች የምግብ ዕደላ ወቅት በተቀሰቀሰ ግጭት ተረጂዎች ተጎዱ
ሰሜን ኬንያ በሚገኘው ካኩማ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት ፖሊስ በወሰደው ርምጃ አራት ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ። በትላንቱ የምግብ ዕደላ ላይ የተቀሰቀሰው ግጭት ለስደተኛው ከሚሰጠው የምግብ ርዳታ እጥረት ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል። ከኬንያ አጎራባቾች ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲ እና ኮንጎ ግጭቶችን በመሸሽ እና በድርቅ ሳቢያ የሚሰደዱ ወገኖችን በሚያስጠልለው ካምፕ ውስጥ ለሚገኙት በብዙ ሺሕዎች የሚገመቱ ስደተኞች ይሰጥ የነበረው የምግብ አቅርቦት፤ በተፈጠረው የርዳታ ገንዘብ እጥረት የተነሳ የወትሮ አሠራሩ መስተጓጎሉ ተዘግቧል። በካምፑ ለስደተኞች የሚሰጠውን ምግብ የሚያከፋፍለው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለፈው ታኅሣሥ ወር ለስደተኞች ከሚሰጠው ምግብ "በገጠመው የአቅርቦት እጥረት የተነሳ ከሚያስፈልገው ከ45 በመቶ በታች እንደነበር አመልክቷል። የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከለጋሽ አገሮች መንግሥታት ያገኝ የነበረው መዋጮ እጥረት እንደሚገጥመው ለዓመታት ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወቃል። Read more