እስራኤል ዕርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ በማገዷ የረድኤት ድርጅቶች ስጋት ገብቷቸዋል
newsare.net
እስራኤል ከውሃ በስተቀር ማንኛውም የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ ማገዷ፣ ወትሮውንም በሕይወት ለመቆየት ትግል ላይ ባሉት ሕፃናትና ቤተሰቦቻቸውእስራኤል ዕርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ በማገዷ የረድኤት ድርጅቶች ስጋት ገብቷቸዋል
እስራኤል ከውሃ በስተቀር ማንኛውም የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ ማገዷ፣ ወትሮውንም በሕይወት ለመቆየት ትግል ላይ ባሉት ሕፃናትና ቤተሰቦቻቸው ላይ አደገኛ ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታውቋል። “ትላንት በዕርዳታ ላይ የተጣለው እገዳ የሲቪሎችን ሕይወት ለመታደግ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል” ሲሉ የቀጠናው የዩኒሴፍ ኅላፊ ኤድዋርድ ቤግበደር አስታውቀዋል። የሕፃናትን ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ የሆነው የተኩስ አቁም መቀጠሉ አስፈላጊ እንደሆነም ኅላፊው ጨምረው ተናግረዋል። በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ልዑክ የሆኑት ስቲቨን ዊትኮፍ ተኩስ አቁሙ እስከ እ.አ.አ ሚያዚያ 20 ድረስ እንዲራዘም መጠየቃቸውን ያወሱት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ይህም የረመዳን ወር እና የአይሁድ በዓላትን የሚሸፍን ሲሆን፣ በዚህ ወቅት በመጀመሪያው ቀን ሃማስ ግማሽ የሚሆኑ ታጋቾችን እንደሚለቅ፣ በመቀጠል ቋሚ የተኩስ ማቆም ሲፈጸም ደግሞ የተቀሩትን ታጋቾች እንደሚለቅ ተናግረዋል። “ይህን ሃሳብ እቀበላለሁ፣ ሃማስ ግን እስከ አሁን እየተቃወመው ነው” ሲሉ አክለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እስራኤል ዕርዳታ እንዳይገባ ያገደችው ሃማስ ዕርዳታውን በመስረቁ እና ፍልስጤማውያን እንዳያገኙት በማድረጉ እንደሆነም ኔታንያሁ አስታውቀዋል። “ዕርዳታውን ለሽብር ተግባር እየተጠቀመብት ነው” ሲሉም ክስ አሰምተዋል። የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ኔታንያሁ የጠቀሱት ጉዳይ ስለመከሰቱ በሥፍራው የሚገኙ ባልደረቦቻቸው ሪፖርት እንዳላደርጉ አስታውቀዋል። Read more