የደቡብ ሱዳን ጦር የምክትል ፕሬዝደንቱን ቤት ከቧል
newsare.net
ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቻር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው የታጠቀ ቡድን፤ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኝ የጦር ሠፈር መውረሩን ተከትሎ፣ የመንየደቡብ ሱዳን ጦር የምክትል ፕሬዝደንቱን ቤት ከቧል
ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቻር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው የታጠቀ ቡድን፤ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኝ የጦር ሠፈር መውረሩን ተከትሎ፣ የመንግሥቱ ወታደሮች ዛሬ በዋና ከተማዋ ጁባ የሚገኘውን የምክትል ፕሬዝደንቱን መኖሪያ ቤት ከበዋል፡፡ በርካታ አጋሮቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል። ማቻር፤ ባለፈው ወር የመንግሥት ባለስልጣን የነበሩ በርካታ አጋሮቻቸው መባረራቸው እ.አ.አ በ2018 በእሳቸው እና በፖለቲካ ተቀናቃኛቸው ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ ይጥላል ብለው ነበር። በሁለቱ ተቀናቃኞች መካከል ለአምስት ዓመታት በተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ለማቻር ታማኝ የነበሩት የጦሩ ምክትል አዛዥ ጀነራል ጋብሪኤል ዱፕ ላም በሰሜኑ ግዛት ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ትላንት ማክሰኞ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በተመሳሳይ የማቻር አጋሩ የነዳጅ ዘይት ሚኒስትር ፑት ካንግ ቾል ከጠባቂዎቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ዛሬ ረቡዕ በቁጥጥር ስር ውለዋል። የታሰሩበት ምክንያት ግን እስካሁን አልተገለጸም። የምዕራብ ሀገራት ልዑካን መሪዎቹ ውጥረቱን እንዲያረግቡ ባለፈው ሳምንት አሳስበው ነበር። ደቡብ ሱዳን እ.አ.አ በ2018 የተደረሰውን ስምምነት እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ያላደረገች ሲሆን ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው ምርጫም በገንዘብ እጦት ምክንያት ለሁለት ዓመት ተራዝሟል። Read more