በኮንጎ ግጭት ምክንያት ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ ርዳታ አቆመች
newsare.net
ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ የልማት ርዳታ ማቆሟን እና ቃል የገባቻቸውን ድጋፎችም እየገመገመች መኾኑን ዛሬ ማክሰኞ አስታውቃለች። ጀርመን ይህን ርበኮንጎ ግጭት ምክንያት ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ ርዳታ አቆመች
ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ የልማት ርዳታ ማቆሟን እና ቃል የገባቻቸውን ድጋፎችም እየገመገመች መኾኑን ዛሬ ማክሰኞ አስታውቃለች። ጀርመን ይህን ርምጃ የወሰደችው፣ ሩዋንዳ በጎረቤቷ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚካሄደው ግጭት ውስጥ ላላት ሚና ምላሽ ለመስጠት ነው። የጀርመን ልማት ምኒስትር ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ በርሊን ውሳኔዋን አስቀድማ ለሩዋንዳ ማሳወቋን እና በምስራቅ ኮንጎ የበላይነት እያገኘ ላለው የኤም 23 አማፂ ቡድን የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቆም ማሳሰቧን አመልክተዋል። ኮንጎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሞያዎች እና የምዕራብ ኃያላን ሀገሮች ሩዋንዳ አማፂውን ቡድን ትደግፋለች በማለት ይከሷታል። ክሱን የምትቃወመው ሩዋንዳ በበኩሏ በኮንጎ የቱትሲ ተወላጆችን ለመጨፍጨፍ እና ለሩዋንዳ ስጋት ለመፍጠር ከሚንቀሳቀሱ የሁቱ ተወላጅ ታጣቂዎች እራሷን እየተከላከለች እንደሆነ ትገልጻለች። የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የጀርመን ውሳኔ «የተሳሳተ እና አሉታዊ ውጤት ያለው ነው» ሲል ምላሽ ሰጥቷል። መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ «በቀጠናው በተደጋጋሚ ለሚከሰቱ አለመረጋጋቶች ታሪካዊ ኃላፊነት የተሸከሙ እንደ ጀርመን ያሉ ሀገራት ለአንድ ወገን ያደላ አስገዳጅ ርምጃዎችን ከመተግበር የተሻለ ማወቅ ነበረባቸው» ብሏል። የጀርመን ምኒስቴር እንደገለፀው በርሊን፣ እ.አ.አ ከጥቅምት 2022 እስከ 2024 ላለው ጊዜ የ98 ሚሊየን ዶላር ርዳታ ለሩዋንዳ ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር። Read more