የአሜሪካ እና የካናዳ መሪዎች ስለዘገዩት ቀረጦች እና ስለ ንግድ ነክ ጉዳዮች ተወያዩ
newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ እና የካናዳ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ትላንት ረቡዕ በንግድ እና ሌሎች ጉዳዮች ውይይት አካሂደዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትየአሜሪካ እና የካናዳ መሪዎች ስለዘገዩት ቀረጦች እና ስለ ንግድ ነክ ጉዳዮች ተወያዩ
የዩናይትድ ስቴትስ እና የካናዳ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ትላንት ረቡዕ በንግድ እና ሌሎች ጉዳዮች ውይይት አካሂደዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕም፣ ከካናዳ እና ከሜክሲኮ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ አዲስ የተጣለውን የ25 ከመቶ ቀረጥ ለአንድ ወር አዘግይተዋል ። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ «በጋራ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች፣ በድንበር ደህንነት መጠናከር ፣ በንግድ ልውውጥ እና የኢኮኖሚ ብልጽግና» ሁለቱ ሀገሮች በትብብር መሥራታቸውን ለመቀጠል ስለሚችሉበት መንገድ መወያየታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ትረምፕ ቀረጡን ማዘግየታቸውን ከማስታወቃቸው በፊት ከትላልቆቹ የዩናይትድ ስቴትስ መኪና አምራቾች፣ ከፎርድ፣ ጀነራል ሞተርስ እና ስቴላንቲስ የሥራ አስፈፃሚዎች ጋር መነጋገራቸውን የኋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሮላይን ሌቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ ትረምፕ መኪና አምራቾቹ፣ የማምረቻ ቦታዎቻቸውን ከሜክሲኮ እና ካናዳ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በማዞር የሚጣልባቸውን ቀረጥ በጠቅላላ ማስወገድ እንዲችሉ ያሳሰቧቸው መሆኑንም ቃል አቀባይዋ አክለዋል፡፡ ትረምፕ በሁለቱ ትላልቆቹ የአሜሪካ የንግድ ሸሪኮች ሌሎች ምርቶች ላይ የጣሏቸው አዲሶቹ ቀረጦች እንዳለ እንደሚቆዩ ሌቪት ገልጸዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሌሎችንም ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ማድረግ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ካሉ ለማጤን ዝግጁ መሆናቸውን ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል፡፡ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሀገራቸው ላይ የተጣሉ ሁሉም የአሜሪካ ቀረጦች እስካልተነሱ ድረስ፣ ካናዳ በአጸፋው የጣለቻቸውን ቀረጦች ለማስወገድ ፈቃደኛ አልሆኑም ። የኦንታርዮ ክፍለ ግዛት አገረ ገዥ ደግ ፎርድ “ወደ አሜሪካ በሚላኩ የካናዳ ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ቀረጥ ባለበት ከቀጠለ በካናዳ የሚገኙ የተሽከርካሪ ማምረቻዎች በ10 ቀናት ውስጥ መዘጋት ይጀምራሉ” ብለዋል፡፡ “ሰዎች ሥራቸውን ያጣሉ” ሲሉም ፎርድ አክለዋል፡ የካናዳ የክልል መሪዎች በዩናይትድ ስቴትስ ገበያ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ከሌሎች አገሮች ጋር የንግድ ልውውጥን ለማስፋት እየሰሩ ነው፡፡ ትረምፕ በቻይና ምርቶች ላይ የጣሉትን ቀረጥ በእጥፍ በማሳደግ 20 ከመቶ በማድረሳቸው የአክሲዮን ገበያው እንዲያሽቆለቁል እና ሸማቾች ላይ ዋጋ የመጨመር ስጋት እንዲፈጠር አድርጓል። ሜክሲኮ፣ ካናዳ እና ቻይና ለትረምፕ እርምጃ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የአጸፋ ቀረጥ እንደሚጥሉ አስታውቀዋል። ፕሬዝደንት ትረምፕ በትሩዝ ሶሻል መድረካቸው ላይ ባወጡት ጽሁፍ «ትሩዶ ሀገራቸው ላይ የተጣሉትን አዳዲስ ቀረጦች በሚመለከት ምን ማድረግ እንደሚቻል ትላንት ረቡዕ ስልክ ደውለው ጠይቀውኝ ነበር፡፡ እኔም በካናዳ እና በሚከሲኮ ድንበር በኩል የሚገባው ፈንቲኔል ብዙ ሰው ገድሏል፡፡ ያ መቆሙን የሚያሳምን ነገር አላገኘሁም አልኳቸው፡፡ ከበፊቱ ተሻሽሏል አሉ፡፡ እሱ በቂ እንዳልሆነ ነግሬአቸዋለሁ » ብለዋል፡፡ Read more