በመንና ጅቡቲ ጀልባዎች ሰጥመው ፍልሰተኞች መሞታቸውንና በርካቶች የደረሱበት አለመታወቁን ተመድ አስታወቀ
newsare.net
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍልሰተኞች ኤጀንሲ እንደገለፀው በየመንና ጅቡቲ የባህር ዳርቻ አራት የፍልሰተኞች ጀልባዎች ሰጥመው ሁለት ሰዎች ሲሞቱ 186 የሚበመንና ጅቡቲ ጀልባዎች ሰጥመው ፍልሰተኞች መሞታቸውንና በርካቶች የደረሱበት አለመታወቁን ተመድ አስታወቀ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍልሰተኞች ኤጀንሲ እንደገለፀው በየመንና ጅቡቲ የባህር ዳርቻ አራት የፍልሰተኞች ጀልባዎች ሰጥመው ሁለት ሰዎች ሲሞቱ 186 የሚሆኑት ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም። የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ቃል አቀባይ ታሚም ኤሊየን እንዳሉት ሁለት ጀልባዎች በየመን ባህር ላይ የሰጠሙት ሀሙስ ምሽት ሲሆን የጠፉት 181 ፍልሰተኞችና አምስት የየመን የጀልባው ሰራተኞች መሆናቸውን ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል። ሁለት የጀልባው ሰራተኞችን ማትረፍ ተችሏል ብለዋል፡፡ ሌሎች ሁለት ጀልባዎች ደግሞ በትንሿ አፍሪካዊቷ ሀገር ጅቡቲ በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ሰጥመዋል ሲሉ ተናግረዋል። የሁለት ፍልሰተኞች አስከሬን የተገኘ ሲሆን በጀልባው ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሰዎችንም ማትረፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በደቡብ ምእራብ የመን ታይዝ ግዛት በዱባብ ወረዳ የተገለበጠችው ሶስተኛዋ ጀልባ 31 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችና ሶስት የመናውያን ሰራተኞችን አሳፍራ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ አራተኛዋ ጀልባ የሰጠመችው ደግሞ በዚሁ አካባቢ አቅራቢያ ወደሚገኘው የአቢያን ግዛት አህዋር ወረዳ ሲሆን 150 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችንና አራት ሰራተኞችን አሳፋራ የነበረች ናት፡፡ ባለፉት አስርት አመታት ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን በሚወስደው በዚህ የፍልሰተኞች የባህር ጉዞ ሰጥመው መሞታቸው የተረጋገጡ 693 ሰዎችን ጨምሮ ቢያንስ 2ሽህ 82 ፍልሰተኞች ደብዛቸው ጠፍቷል፡፡ Read more