የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማርች 8ትን በሴቶች ብቻ በሚደረጉ በረራዎች እያከበረ ነው
newsare.net
ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በተለያዩ ሥነ ሥርዐቶች ያከበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከትናንት የካቲት 28 ቀን 2017 አንስቶ በሴቶች ብቻ የሚመሩ ስድስት በረራዎየኢትዮጵያ አየር መንገድ ማርች 8ትን በሴቶች ብቻ በሚደረጉ በረራዎች እያከበረ ነው
ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በተለያዩ ሥነ ሥርዐቶች ያከበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከትናንት የካቲት 28 ቀን 2017 አንስቶ በሴቶች ብቻ የሚመሩ ስድስት በረራዎችን ወደተለያዩ መዳረሻዎች ማድረግ ጀምሯል። የበረራ ፕሮግራሙ ሴት ሞያተኞችን በዓለምአቀፍ አቪየሺን ኢንዱስትሪ ላይ እያሳረፉ ያለው ደማቅ አሻራ ጎልቶ እንዳታይ የሚያደርግ ነው ሲሉ የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ ተናግረዋል ። አየር መንገዱ፣ በሴቶች ብቻ የሚመሩ በረራዎቹን የሚያደርገው ወደ አቴንስ ፣ሳኦ ፖሎ፣ኒው ደልሂ፣ዊንድሆክ፣ዱባይና ባሕርዳር መኾኑን አስታውቋል ። በሥነ ሥርዐቱ ላይ የተናገሩት የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ፣ ሰድስቱ በረራዎች ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመሩ መኾናቸውን አስታውቀዋል። በረራዎቹ የአየር መንገዱን ሴት ሠራተኞች አስተዋጽኦ እንደሚያስተዋውቁም ጠቅሰዋል ። በኹሉሞ ዘርፎች እየታያ ነው ያሉትን የሴት ሞያተኞች ተሳትፎ ያብራሩት አቶ ለማ፣ ይሄም የተቋቋሙ ጥንካሬ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በተለምዶ የወንዶች ተሳትፎ ልቆ በሚታይበት የአቪየሺን ዘርፍ ውስጥ የሴቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መኾኑን የገለፁት ኃላፊው አየር መንገዱ ሚናቸውን ይበልጥ ለማሳደግ እየሠራ መኾኑንም ጠቅሰዋል። በረራዎቹ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አጉልቶ ለማሳየትና አጋርነትን ለመግለጽ ጭምር የተካሄዱ መኾናቸውንም ተናግረዋል። ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን (ማርች 8) ዘንድሮ እየተከበረ ያለው «መብት እኩልነትና አቅም መጎልበት ለሴቶች በሙሉ» በሚል መሪ ቃል ነው። Read more