Ethiopia



የአሜሪካ ታጋቾች ተደራዳሪ ከሐማስ ጋራ የነበራቸውን ንግግር “ጠቃሚ” ብለውታል

የትረምፕ አስተዳደር የታጋቾች ተደራዳሪ በቅርቡ በአሜሪካ ከተሰየመው የሽብር ቡድን ሐማስ ተወካዮች ጋር ያደረጉትን ንግግር “ጠቃሚ” ብለውታል። ንግግሩ በ

በራያ አላማጣ ጥሙጋ ቀበሌ አንድ የቤተክርስቲያን መምሕርና አራት ተማሪዎች ተገደሉ

በራያ ኣላማጣ ጥሙጋ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ባለፈው አርብ፣ በአንድ ቤተ ክርስትያን መምህር እና ተማሪዎች በተፈፀመ ጥቃት አምስት ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው አ
የአሜሪካ ድምፅ

በራያ አላማጣ ጥሙጋ ቀበሌ አንድ የቤተክርስቲያን መምሕርና አራት ተማሪዎች ተገደሉ

በራያ ኣላማጣ ጥሙጋ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ባለፈው አርብ፣ በአንድ ቤተ ክርስትያን መምህር እና ተማሪዎች በተፈፀመ ጥቃት አምስት ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ገለጹ። የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ሕሉፍ፣ በሌሎች አራት ሰዎች ላይም በጥቃቱ ጉዳት መስረሱን ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ሩሲያ ዩክሬን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 11 ሰዎች መገደላቸውን ኪቭ አስታወቀች

ኪቭ፣ ዩክሬን — ሩሲያ ትላንት ቅዳሜ የካቲት  29 ቀን 2017 ዓ.ም፣ በዩክሬን ምሥራቃዊ ከተማ ዶቭሮፒሊያ ላይ በአንድ ምሽት ባደረሰችው፣ የሚሳዬልና ሰው አልባ አው
የአሜሪካ ድምፅ

ሩሲያ ዩክሬን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 11 ሰዎች መገደላቸውን ኪቭ አስታወቀች

ኪቭ፣ ዩክሬን — ሩሲያ ትላንት ቅዳሜ የካቲት  29 ቀን 2017 ዓ.ም፣ በዩክሬን ምሥራቃዊ ከተማ ዶቭሮፒሊያ ላይ በአንድ ምሽት ባደረሰችው፣ የሚሳዬልና ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ቢያንስ 11 ሰዎች ሲገደሉ፣ አምስት ሕፃናትን ጨምሮ 30 ሰዎች መቁሰላቸውን የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሰሜን ምስራቅ ካርኪቭ ግዛት ላይ በደረሰው ጥቃት ፣ ሌሎች ሦስት ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸውን ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል። የሩሲያ ጦር ኃይል ወደ ይክሬኗ ከተማ፣ ባስወነጨፋቸው ባላስቲክ ሚሳዬሎች፣ በተኮሰቸው በበርካታ ሮኬቶች እና በላከቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት፣ ዶቭሮፒሊያ ውስጥ የሚገኙ ስምንት የተለያዩ ሕንፃዎችና 30 መኪኖች መውደማቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል። ሚኒስቴሩ፣ በቴሌግራም መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ ላይ እንዳሰፈሩት፣ «በጥቃቱ ምክኒያት የተቀጣጠለውን እሳት ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ በነበረበት ወቅት፣ ሌላ ተጨማሪ ጥቃት ደርሶ የእሳት አደጋ መከላከያ እና ማጥፊያ መኪናውን ላይ ጉዳት አድርሷል» ብለዋል። ሚኒስቴሩ በቴሌግራም መልዕክታቸው፣ በከፊል የወደሙ ፍርስራሾችን፣ በእሳት ውስጥ የተዋጡ ሕንፃዎችን እና የነፍስ አድን ሠራተኞች ከሕንፃዎቹ ላይ ፍርስራሾችን ሲያነሱ የሚያሳዩ ምስሎችን አጋርተዋል። ከዩክሬን የዶኔትስክ ግዛት የፖክሮቭስክ ቁልፍ ማዕከል 22 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ዶቭሮፒሊያ፣ ከጦሩነቱ በፊት ወደ 28 ሺሕ የሚጠጉ ነዋሪዎች ያሉባት ከተማ ስትኾን ፣ የሩስያ ወታደሮች ለሳምንታት ጥቃት ሲሰነዝሩበት መቆየታቸውን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል። ሚኒስቴሩ አያይዘው፣ ካርኪቭ ላይ በተፈጸመ ሌላ የድሮን ጥቃት፣ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል። የዩክሬ ጦር በበኩሉ፣ ሩሲያ 145 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሦስት የተለያዩ ሚሳዬሎችን ልካ ጥቃቱን እንደፈጸመች አስታውቋል። የጦር ኃይሉ አክሎም፣ አንድ የክሩዝ ሚሳዬል እና 79 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መቶ መጣሉን ገልጿል። ሌሎች 54 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ደግሞ በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ በተወሰዱ የመከላከያ ርምጃዎች ምክንያት ዒላማቸው ላይ ሳይደርሱ እንዲከሽፉ መደረጋቸውን የዩክሬን ወታደራዊ ክንፍ አስታውቋል።

በዋይት ሐውስ አቅራቢያ የታጠቀ ግለሰብ በፕሬዝደንታዊ የደኅንነት ጥበቃ ሠራተኞች ተመታ

አንድ ከኢንዲያና ግዛት አካባቢ እንደመጣ የተገመተ እና በዋይት ሐውስ አካባቢ መሳሪያ ታጥቆ፣ ከፖሊስ ጋራ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቷል የተባለ ግለሰብ ፣ “ሴክሬ
የአሜሪካ ድምፅ

በዋይት ሐውስ አቅራቢያ የታጠቀ ግለሰብ በፕሬዝደንታዊ የደኅንነት ጥበቃ ሠራተኞች ተመታ

አንድ ከኢንዲያና ግዛት አካባቢ እንደመጣ የተገመተ እና በዋይት ሐውስ አካባቢ መሳሪያ ታጥቆ፣ ከፖሊስ ጋራ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቷል የተባለ ግለሰብ ፣ “ሴክሬት ሰርቪስ” በመባል በሚታወቀው፣ ዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዝደንታዊ የደኅንነት ጥበቃ አባላት መመታቱን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ከዋይት ሐውስ በአንድ አካፋይ መንገድ ብቻ በሚርቅ ቦታ ላይ፣ እኩለ ሌሊት አካባቢ በተፈጠረው በዚኽ ክስተት ከታጠቀው ገለሰብ በስተቀር የተጎዳ ሌላ ሰው አለመኖሩን የ«ሴክሬት ሰርቪሱ» መግለጫ አመልክቷል። በሰዓቱም ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ፍሎሪዳ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነበሩ ተብሏል። የጥበቃ አገልግሎቱ፣ «አንድ ራሱን ሊያጠፋ ነው» በሚል የሚጠረጠር ግለሰብ ከኢንዲያና ተጉዞ መምጣቱን ከአካባቢ ፖሊስ መረጃ እንደደረሰው ገልጾ፣ ከተሰጠው ዝርዝር መግለጫ ጋራ የሚመሳሰለውን መኪና እና ግለሰቡን በዋይት ሐውስ አቅራቢያ ማግኘቱን አስታውቋል። «ፖሊስ ወደ መኪናው እየቀረበ ሲኼድ ግለሰቡ መሳሪያ በማውጣት እሰጥ አገባ ገጠመ፣ በዚኽ ወቅትም ከኛ በኩል ርምጃ ተወስዷል» ሲል ፕሬዝደንታዊ ደኅንነት ጥበቃ አገልግሎቱ በመግለጫው ላይ አስፍሯል። ግለሰቡ ሆስፒታል እንደሚገኝ የጠቆመው መግልጫው ፣ አኹን ያለበት ኹኔታ ግን «አይታወቅም» ብሏል።

«ከከተሞች ውጭ ያሉ አካል ጉዳተኞችም ትኩረትን ይሻሉ» - ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ

የአብስትራክት ዘይቤ ሠዓሊው ብሩክ የሺጥላ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ስመ ጥር ከኾኑ አካል ጉዳተኛ ሠዓሊዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ብሩክ፥ ወጣት አካል ጉዳተኞችን በማ
የአሜሪካ ድምፅ

«ከከተሞች ውጭ ያሉ አካል ጉዳተኞችም ትኩረትን ይሻሉ» - ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ

የአብስትራክት ዘይቤ ሠዓሊው ብሩክ የሺጥላ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ስመ ጥር ከኾኑ አካል ጉዳተኛ ሠዓሊዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ብሩክ፥ ወጣት አካል ጉዳተኞችን በማነቃቃት፣ በማስተማር እና በማበረታታት ለማብቃት፣ ብዙኀን መገናኛዎች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ይናገራል፡፡  በተለይም፣ ከከተሞች ውጭ የሚገኙ ወጣት አካል ጉዳተኞች በሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሮች ማካሔድ እንደሚገባ ሠዓሊ ብሩክ አመልክቷል፡፡  ኤደን ገረመው፥ ከሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ጋራ ያደረገችውን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማርች 8ትን በሴቶች ብቻ በሚደረጉ በረራዎች እያከበረ ነው

ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በተለያዩ ሥነ ሥርዐቶች ያከበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከትናንት የካቲት 28 ቀን 2017 አንስቶ በሴቶች ብቻ የሚመሩ ስድስት በረራዎ
የአሜሪካ ድምፅ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማርች 8ትን በሴቶች ብቻ በሚደረጉ በረራዎች እያከበረ ነው

ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በተለያዩ ሥነ ሥርዐቶች ያከበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከትናንት የካቲት 28 ቀን 2017 አንስቶ በሴቶች ብቻ የሚመሩ ስድስት በረራዎችን ወደተለያዩ መዳረሻዎች ማድረግ ጀምሯል። የበረራ ፕሮግራሙ ሴት ሞያተኞችን በዓለምአቀፍ አቪየሺን ኢንዱስትሪ ላይ እያሳረፉ ያለው ደማቅ አሻራ ጎልቶ እንዳታይ የሚያደርግ ነው ሲሉ የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ ተናግረዋል ። አየር መንገዱ፣ በሴቶች ብቻ የሚመሩ በረራዎቹን የሚያደርገው ወደ አቴንስ ፣ሳኦ ፖሎ፣ኒው ደልሂ፣ዊንድሆክ፣ዱባይና ባሕርዳር መኾኑን አስታውቋል ። በሥነ ሥርዐቱ ላይ የተናገሩት የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያዴቻ፣ ሰድስቱ በረራዎች ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመሩ መኾናቸውን አስታውቀዋል። በረራዎቹ የአየር መንገዱን ሴት ሠራተኞች አስተዋጽኦ እንደሚያስተዋውቁም ጠቅሰዋል ። በኹሉሞ ዘርፎች እየታያ ነው ያሉትን የሴት ሞያተኞች ተሳትፎ ያብራሩት አቶ ለማ፣ ይሄም የተቋቋሙ ጥንካሬ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በተለምዶ የወንዶች ተሳትፎ ልቆ በሚታይበት የአቪየሺን ዘርፍ ውስጥ የሴቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መኾኑን የገለፁት ኃላፊው አየር መንገዱ ሚናቸውን ይበልጥ ለማሳደግ እየሠራ መኾኑንም ጠቅሰዋል። በረራዎቹ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አጉልቶ ለማሳየትና አጋርነትን ለመግለጽ ጭምር የተካሄዱ መኾናቸውንም ተናግረዋል። ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን (ማርች 8) ዘንድሮ እየተከበረ ያለው «መብት እኩልነትና አቅም መጎልበት ለሴቶች በሙሉ» በሚል መሪ ቃል ነው።

በመንና ጅቡቲ ጀልባዎች ሰጥመው ፍልሰተኞች መሞታቸውንና በርካቶች የደረሱበት አለመታወቁን ተመድ አስታወቀ 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍልሰተኞች ኤጀንሲ እንደገለፀው በየመንና ጅቡቲ የባህር ዳርቻ አራት የፍልሰተኞች ጀልባዎች ሰጥመው ሁለት ሰዎች ሲሞቱ 186 የሚ
የአሜሪካ ድምፅ

በመንና ጅቡቲ ጀልባዎች ሰጥመው ፍልሰተኞች መሞታቸውንና በርካቶች የደረሱበት አለመታወቁን ተመድ አስታወቀ 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍልሰተኞች ኤጀንሲ እንደገለፀው በየመንና ጅቡቲ የባህር ዳርቻ አራት የፍልሰተኞች ጀልባዎች ሰጥመው ሁለት ሰዎች ሲሞቱ 186 የሚሆኑት ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም። የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ቃል አቀባይ ታሚም ኤሊየን እንዳሉት ሁለት ጀልባዎች በየመን ባህር ላይ የሰጠሙት ሀሙስ ምሽት ሲሆን የጠፉት 181 ፍልሰተኞችና አምስት የየመን የጀልባው ሰራተኞች መሆናቸውን ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል። ሁለት የጀልባው ሰራተኞችን ማትረፍ ተችሏል ብለዋል፡፡ ሌሎች ሁለት ጀልባዎች ደግሞ በትንሿ አፍሪካዊቷ ሀገር ጅቡቲ በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ሰጥመዋል ሲሉ ተናግረዋል። የሁለት ፍልሰተኞች አስከሬን የተገኘ ሲሆን በጀልባው ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሰዎችንም ማትረፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በደቡብ ምእራብ የመን ታይዝ ግዛት በዱባብ ወረዳ የተገለበጠችው ሶስተኛዋ ጀልባ 31 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችና ሶስት የመናውያን ሰራተኞችን አሳፍራ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ አራተኛዋ ጀልባ የሰጠመችው ደግሞ በዚሁ አካባቢ አቅራቢያ ወደሚገኘው የአቢያን ግዛት አህዋር ወረዳ ሲሆን 150 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችንና አራት ሰራተኞችን አሳፋራ የነበረች ናት፡፡ ባለፉት አስርት አመታት ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን በሚወስደው በዚህ የፍልሰተኞች የባህር ጉዞ ሰጥመው መሞታቸው የተረጋገጡ 693 ሰዎችን ጨምሮ ቢያንስ 2ሽህ 82 ፍልሰተኞች ደብዛቸው ጠፍቷል፡፡

ፕሬዘዳንት ትራምፕ የቴሌቭዥን አቅራቢ የሆኑትን ላውራ ኢንግራሃምንና ማሪያ ባርቲሮሞን ለኬኔዲ ማዕከል ቦርድ አድርገው ሾሙ 

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት እንዳስታወቁት የፎክስ ኒውስ ፕሮግራም መሪ ላውራ ኢንግራሃምንና የጣቢያው ቢዝነስ ዘገባ አቅራቢ ማሪያ
የአሜሪካ ድምፅ

ፕሬዘዳንት ትራምፕ የቴሌቭዥን አቅራቢ የሆኑትን ላውራ ኢንግራሃምንና ማሪያ ባርቲሮሞን ለኬኔዲ ማዕከል ቦርድ አድርገው ሾሙ 

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት እንዳስታወቁት የፎክስ ኒውስ ፕሮግራም መሪ ላውራ ኢንግራሃምንና የጣቢያው ቢዝነስ ዘገባ አቅራቢ ማሪያ ባቲሮሞንን ለጆን ኤፍ ኬኔዲ የስነ ጥበባት ማዕከል ቦርድ ሹመዋል፡፡  ትራምፕ ስልጣን ከያዙ ከሳምንታት በኋላ የካቲት ወር ላይ የማዕከሉን ፕሬዝዳንት በማባረር የባለአደራ ቦርድ የተከኩ ሲሆን የድርጅቱን ሊቀመንበርም ሰይመዋል።  ርምጃዎቹ የክብር ትርኢት የሚቀርቡበትና የብሄራዊ ሲምፎኒ ኦርኬስትራ እንዲሁም የዋሽንግተን ብሄራዊ ኦፔራ የሚቀርብበት የባህል ተቋም የሆነውን የኬኔዲ ማዕከል ትራምፕን መቆጣጠራቸውን ያሳያል ተብሏል፡፡  ትራምፕ የኢንግራሃም እና የባርቲሮሞ ሹመት ካስታወቁ በኋላ «ይህ ምርጫችንን ያጠናቅቃል» ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡  ትራምፕ ባለፈው ወር የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ልዑክ የሆኑት ሪቻርድ ግሬኔል የማዕከሉ ጊዜያዊ ስራ አስፈፃሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመዋል፡፡

የየመን ሁቲዎች ለእስራኤል የጋዛን የእርዳታ እገዳ እንድታነሳ የአራት ቀናት ቀነ ገደብ ሰጡ 

የየመን ሁቲ አማጽያን መሪ እስራኤል በአራት ቀናት ውስጥ በጋዛ ላይ የጣለችውን የእርዳታ እገዳ ካላነሳች ቡድኑ በእስራኤል ላይ የሚያደርገውን የባህር ሃይል ጥ
የአሜሪካ ድምፅ

የየመን ሁቲዎች ለእስራኤል የጋዛን የእርዳታ እገዳ እንድታነሳ የአራት ቀናት ቀነ ገደብ ሰጡ 

የየመን ሁቲ አማጽያን መሪ እስራኤል በአራት ቀናት ውስጥ በጋዛ ላይ የጣለችውን የእርዳታ እገዳ ካላነሳች ቡድኑ በእስራኤል ላይ የሚያደርገውን የባህር ሃይል ጥቃት እንደሚቀጥል ትላንት አስታውቋል፡፡  ይህም  እ.ኤ.አ. በጥር ወር የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ እየቀነሰ የመጣው የሁቲዎች ጥቃት ሊባባስ እንደሚችል የሚጠቁም ነው ተብሏል፡፡  ኢራን አጋር የሆኑት የሁቲ አማጽያን እስራኤል በጋዛ በዩናይትድ ስቴትስ በሽብር የተፈረጀው ሃማስ ቡድን ላይ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት ለፍልስጤማውያን አጋርነት ለማሳየት በሚል ከእአአ ህዳር 2023 ጀምሮ በመርከብ ላይ ያነጣጠሩ ከ100 በላይ ጥቃቶችን ፈጽሟል፡፡  መሪው አል-ሁቲ በኩል «ለአራት ቀናት ቀነ ገደብ እንሰጣለን፡ ይህም የጊዜ ገደብም ለጋዛ የተኩስ አቁም አሸማጋዮች ለጥረታቸው ሲባል ነው» ብሏል፡፡  እ.ኤ.አ መጋቢት 2 ጀምሮ እስራኤል የእርዳታ መኪኖችን ወደ ጋዛ እንዳይገቡ አግዳለች፡፡ ሃማስ እርዳታዎችን በመስረቅ  ለፍልስጤማውያን እንዳይደርስ አድርጓል ስትልም ትከሳለች፡፡    

የደቡብ ኮሪያ  ፕሬዝዳንት ዩን ከእስር ተለቀቁ 

የደቡብ ኮሪያ ፍርድቤት በክስ ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የእስር ማዘዣ እንዲሰረዝ መወሰኑን ተከትሎ አቃቢ ህግ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ላለመጠየቅ በ
የአሜሪካ ድምፅ

የደቡብ ኮሪያ  ፕሬዝዳንት ዩን ከእስር ተለቀቁ 

የደቡብ ኮሪያ ፍርድቤት በክስ ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የእስር ማዘዣ እንዲሰረዝ መወሰኑን ተከትሎ አቃቢ ህግ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ላለመጠየቅ በመወሰኑ ዛሬ በሴኡል ከሚገኘው እስርቤት ተለቀዋል፡፡  ዮን በእአአ ታህሳስ 3 ቀን ባሳለፉትና ለአጭር ጊዜ በቆየው የማርሻል ህግ ምክንያት ከስራቸው እንደታገዱ የሚቆዩ ሲሆን በአመፅ የቀረበባቸው ክስም እንዳለ ይቆያል ተብሏል፡፡  የወንጀል ጉዳዩ በስልጣን ላይ በሚኖራቸው ቆይታ ዙርያ ክሚታየው የፍርድ ሂደት የተለየ ሲሆን በህገ-መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ወደ ሥራ ይመለሱ ወይም ከሥልጣናቸው ይነሱ በሚለው ጉዳይ ላይ በሚቀጥሉት ቀናት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል።   

አሜሪካ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አደረገች

ዋሽንግተን — የአሜሪካ መንግሥት፣ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በመቀጠል ላይ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥሪውን በድጋሚ አሰምቷል። የኤም 23 አማፂያን በርካታ ቦ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አደረገች

ዋሽንግተን — የአሜሪካ መንግሥት፣ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በመቀጠል ላይ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥሪውን በድጋሚ አሰምቷል። የኤም 23 አማፂያን በርካታ ቦታዎችን በመቆጣጠር ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ የአሜሪካንን መንግሥት ጥሪ በድጋሚ ያሰሙት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ፣ የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ከዚህ በፊት በጉዳዩ ላይ ያሳዩትን አቋም በድጋሚ አንጸባርቀዋል። ሩቢዮ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ እና ከኮንጎው ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቸሰደኪ ጋራ መነጋገራቸውን ያወሱት ቃል አቀባዩ፣ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆምና ለተከሰተው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂነት እንዲኖር ማስገንዘባቸውን ተናግረዋል። ለኮንጎ ሕዝብ እና ለኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሉአላዊነት ያላቸውን ድጋፍ የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ ማስታወቃቸውንም ቃል አቀባዩ አመልክተዋል። አሜሪካ በአንጎላው ፕሬዝደንት ሉዋንዳ ላይ ባለፈው ዓመት የተጀመረውንና የተኩስ ማቆም ስምምምነት እንዲፈረም ያስቻለውን ሂደት እንደምትደግፍም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል። አሜሪካ በዲፕሎማሲ በኩል ግኑኙነቷን እንደምትቀጥልም ተናግረዋል። የአፍሪካ ኅብረት፣ የተመድ የጸጥታው ም/ቤት እንዲሁም አሜሪካ በኮንጎ የሚታየውን ሁከት አውግዘዋል። ተመድና አሜሪካ፣ ሩዋንዳ የኤም 23 አማፂያንን እንደምትደግፍና ሠራዊቷንም በምስራቅ ኮንጎ ማሰማራቷን ሲገልጹ፣ ሩዋንዳ ታስተባብላለች፡፡ በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ አሜሪካ ለ90 ቀናት የውጪ ርዳታ ማቋረጧ በሰብአዊ፣ ደኅንነትና ጤና መስኮች ሊደርስ የሚችለው ጉዳት እንደሚያሳስባቸው የአህጉሪቱ መሪዎች አሜሪካ አስታውቀዋል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ በበኩላቸው፣ የማቋረጡ ውሳኔ መንግሥት ለውጪ ርዳታዎች የሚውለውን ገንዘብ እንደገና ለመመልከት እና የሚሠራና የማይሠራውን ለመለየት ጊዜና ዕድል እንዲሰጠው ይረዳል ሲሉ ተከላክለዋል። ውሳኔው አሜሪካ ከዚህ በኋላ ርዳታ እንደማትሰጥ የሚያለክት ሳይኾን፣ ውጤታማ የሆነውን የርዳታ ዐይነት ለመለየት የሚጠቅም ነውም ብለዋል። ሰዎች ርዳታ እንዳይቋረጥባቸው ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚያመለክቱበት ሂደትም እንዳለ ጠቁመዋል።

የትረምፕ አስተዳደር ለኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ ሊሰጥ የነበረውን የ400 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሰረዘ  

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር እንዳስታወቀው በኒዮርክ በሚገኘው የኮሎምብያ ዩንቨርስቲ ካምፓስና አካባቢው ባለው ፀረ ሴማዊ ትንኮ
የአሜሪካ ድምፅ

የትረምፕ አስተዳደር ለኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ ሊሰጥ የነበረውን የ400 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሰረዘ  

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር እንዳስታወቀው በኒዮርክ በሚገኘው የኮሎምብያ ዩንቨርስቲ ካምፓስና አካባቢው ባለው ፀረ ሴማዊ ትንኮሳ ምክንያት ለዩንቨርስቲው ሊሰጡ የነበሩ ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚገመቱ ዕርዳታዎችን እና ውሎችን መሰረዙን አስታውቋል፡፡ ውሳኔው ትላንት ይፋ የተደረገው የፍትህ፣ የትምህርት ፣ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት እንዲሁም የአጠቃላይ አገልግሎት አስተዳደር መምሪያዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው።  የትራምፕ አስተዳደር የገንዘብ ድጎማዎች እና ውሎች በመቋረጡ ሊጎዱ የሚችሉትን ዘርፎች አልያም የፀረ ሴማዊ ትንኮሳ ማስረጃውን ለመግለጽ ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ይሁንና ይህ ድጋፍ ለዩንቨርስቲው ቃል ከተገባለት ከ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ  እርዳታ መካከል ተቀናሽ የሚሆን ነው ተብሏል፡፡  አብዛኛው የገንዘብ ድጋፍ ለጤና አጠባበቅና ሳይንሳዊ ምርምር የሚውል እንደሆነ ያስታወቀው የሮይተርስ ዘገባ አሃዞቹን ግን ማረጋገጥ አለመቻሉንም ገልጿል፡፡  ይፋ የተደረገው “የወዲያውኑ” ቅነሳዎች ህጋዊ ተግዳሮቶች ሊገጥሙት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡ የሲቪል መብት ተሟጋች ቡድኖች የኮንትራቱ መሰረዝ ተገቢውን ሂደት ያልተከተለና ጥበቃ ባላቸው መብቶች ላይ የተወሰደ ኢ-ህገመንግስታዊ ቅጣት ነው ሲሉ ተናግረዋል።  ባለፈው አመት የእስራኤልና የጋዛ ጦርነት በተቀጣጠለበት ወቅት የኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ  የፍልስጤም ደጋፊዎችና ጸረ እስራኤል የተማሪዎች ተቃውሞ በግንባር ቀደምትነት ሲካሄድበት የነበረ ነው፡፡ 

በብዙ አገሮች የሽብር ጥቃቶች እየበረከቱ በመጡበት አፍሪካ አስከፊ ጥቃቶችን ማስተናገዷ ተዘገበ

ባለፈው ዓመት በዓለም እጅግ አውዳሚ መሆኑ የተነገረለት የአሸባሪዎች ጥቃት በአፍሪካ ሲፈፀም፤ የዓለም የምጣኔ ሃብት እና የሰላም ተቋም ይፋ ያደረገው የ2025 የዓ
የአሜሪካ ድምፅ

በብዙ አገሮች የሽብር ጥቃቶች እየበረከቱ በመጡበት አፍሪካ አስከፊ ጥቃቶችን ማስተናገዷ ተዘገበ

ባለፈው ዓመት በዓለም እጅግ አውዳሚ መሆኑ የተነገረለት የአሸባሪዎች ጥቃት በአፍሪካ ሲፈፀም፤ የዓለም የምጣኔ ሃብት እና የሰላም ተቋም ይፋ ያደረገው የ2025 የዓለም አቀፍ የሽብር ጥቃቶች ጠቋሚ ሪፖርት እንዳመለከተው፤ በአጠቃላይ ከሽብር ጋር ከተዛመዱ ግድያዎች ከገሚስ በላይ የሚሆኑት የተፈጸሙት የዓለም አቀፍ የሽብር ጥቃቶች መናሃሪያ ሆኖ በቆየው የሳሕል ክልል ነው። በሁለት ሀገራት የደረሱትን 3 አደገኛ የሽብር ጥቃቶች ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ከተዘገቡት 20 ያህል እጅግ የከፉ ጥቃቶች ውስጥም 17ቱ የተፈጸሙት በአፍሪካ ነው። ባለፈው ዓመት በሰኔ፣ በሀምሌ እና በነሀሴ ወር በኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ የተፈጸሙት ጥቃቶች ለ607 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክኒያት መሆናቸውን አክሎ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአውስትራሊያ ያደረገው ይሄው የጥናት ቡድን አረጋግጧል። በዚሁ ዓመት በሳህል ክልል ከግጭቶች ጋር ተያይዘው የደረሱ ሞቶች ቁጥር ከ25,000 በላይ ሰዎች የጠፋባቸው ድንገቶች ዓመታዊው ጥናታዊ ሪፖርት ይፋ መደረግ ከጀመረ ወዲህ ከተዘገቡት ሁሉ እጅግ ግዙፍ መሆኑ እና ከእነዚህም ውስጥ 3,885 ያህሉ በአሸባሪዎች የተፈጸሙ መሆናቸው ተመልክቷል። በመሰል የአሸባሪዎች ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ሃገራት ቀዳሚዋ ቡርኪና ፋሶ ስትሆን፤ ብርቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ጥቂት የአፍሪካ ሀገሮች ማሊ፣ ኒጀር፣ ናይጄሪያ፣ ሶማሊያ እና ካሜሩን እንደሚገኙባቸው ታውቋል። ቡርኪና ፋሶ በዘገባዎች እንደተገለጸው ክፉኛ የተጎዳች ሀገር ብትሆንም፤ አጠቃላይ የጥቃት እና የሟቾች መጠን የሚያመለክቱ አሃዞች በጠቅላላው በ21 በመቶ እና በ57 ቀንሰዋል። ያም ሆኖ ቡርኪና አሁንም በአለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪዎች በሚደርሱ ጥቃቶች የከፋ አደጋ ከሚደርስባቸው አምስተኛዋ አገር ነች። በዓመቱ ውስጥ ቢያንስ አንድ የሽብር ጥቃት የደረሰባቸው ሀገራት ቁጥር ከ58 ወደ 66 ከፍ ማለቱንም ሪፖርት አክሎ አስፍሯል። ከዚህም ውስጥ ከእስላማዊው ጽንፈኛ ቡድን አይሲስ ጋር ቁርኝት ያላቸው ቡድኖች በዓለም ዙሪያ በ22 የተለያዩ አገሮች ውስጥ ባደረሷቸው የሽብር ጥቃቶች 1, 805 ሰዎች ተገድለዋል። በሌላ በኩል እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2024 በሽብርተኞች የተፈጸሙ ጥቃቶች ቁጥር ወደ 7,555 ዝቅ ማለቱ ሲዘገብ፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ13 በመቶ ያነሰ መሆኑ ታውቋል።  

በ62 ግብር ከፋዮች ላይ የጉዞ እግድ ተላለፈ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፣ 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የታክስ ዕዳ አለባቸው ባላቸው 62 ግብር ከፋዮች ላይ ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አስታወቀ
የአሜሪካ ድምፅ

በ62 ግብር ከፋዮች ላይ የጉዞ እግድ ተላለፈ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፣ 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የታክስ ዕዳ አለባቸው ባላቸው 62 ግብር ከፋዮች ላይ ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡ ስለጉዳዩ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ የተቋሙ የኮምዩኒኬሽንስ ዲሬክተር አቶ ሰውነት አየለ፣ ከጉዞ እግዱ በተጨማሪ ቢሮው ሌሎች አስተዳደራዊ ርምጃዎችንም እየወሰደ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ በእግዱ ዙርያ አስተያየት የሰጡን አንድ የሕግ ባለሞያ ደግሞ፣ ቢሮው ይህን የማድረግ ሥልጣን በዐዋጅ እንደተሰጠው ገልጸው፣ ነገር ግን የዚህ ዐይነት ውሳኔ የሚተላለፈው፣ ታክስ ከፋዩ ግለሰብ ከሀገር ሊወጣ ይችላል የሚል በቂ ምክንያት ሲኖር ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ትራምፕ የያደረጉትን የቀረጥ ጭማሪ ተከትሎ ቻይና ‘የአፀፋ ርምጃ እወስዳለሁ’ ስትል አስጠነቀቀች

ቤጂንግ «በዘፈቀደ የተፈጸመ» ላለችው የትራምፕ አስተዳደር ለደነገገው ተጨማሪ የቀረጥ የአጸፋ መልስ እሰጣለሁ ስትል አስጠንቅቃለች። የቻይናው የውጭ
የአሜሪካ ድምፅ

ትራምፕ የያደረጉትን የቀረጥ ጭማሪ ተከትሎ ቻይና ‘የአፀፋ ርምጃ እወስዳለሁ’ ስትል አስጠነቀቀች

ቤጂንግ «በዘፈቀደ የተፈጸመ» ላለችው የትራምፕ አስተዳደር ለደነገገው ተጨማሪ የቀረጥ የአጸፋ መልስ እሰጣለሁ ስትል አስጠንቅቃለች። የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “መልካምን በክፉ ትመልሳለች” ሲሉም ዩናይትድ ስቴትስን ወንጅለዋል። የአሜሪካ ድምጹ ቢል ጋሎ እንደዘገበው፣ ይህ ቤጂንግ ራሷን ለዓለም መረጋጋት የቆመ ኃይል አድርጋ ለማሳየት የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑን ጠቁሟል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ጥንቃቄ የሚሻው የወጣቶች የማኅበራዊ ሚድያ አጠቃቀም

በኢትዮጵያ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጩ እና በሀገር ውስጥ ለሚካሄዱ የተለያዩ
የአሜሪካ ድምፅ

ጥንቃቄ የሚሻው የወጣቶች የማኅበራዊ ሚድያ አጠቃቀም

በኢትዮጵያ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጩ እና በሀገር ውስጥ ለሚካሄዱ የተለያዩ ግጭቶች መባባስ ምክንያት እየሆኑ መሄዳቸውን ተከትሎ፣ ስለሀሰተኛ መረጃ ምንነት እና መረጃን ከተለያዩ ምንጮች የማጣራት ክህሎት የሚያስጨብጥ የሚዲያ አጠቃቀም ትምህርት ወሳኝ መሆኑን በርካታ ጥናቶች ያመለከታሉ። ተማሪዎች እና ወጣቶች በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ያላቸው እውቀት ምን እንደሚመስል ጠይቀናቸዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  

ዶናልድ ትረምፕ የኑክሌር ድርድር እንዲደረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኢራን ላኩ

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ከኢራን ጋራ የኑክሌር ድርድር ማድረግ እንደሚሹ ለሀገሪቱ መሪዎች ትላንት ሐሙስ ደብዳቤ መላካቸውን አስታውቀዋል። የኢራ
የአሜሪካ ድምፅ

ዶናልድ ትረምፕ የኑክሌር ድርድር እንዲደረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለኢራን ላኩ

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ከኢራን ጋራ የኑክሌር ድርድር ማድረግ እንደሚሹ ለሀገሪቱ መሪዎች ትላንት ሐሙስ ደብዳቤ መላካቸውን አስታውቀዋል። የኢራን መሪዎች ለመነጋገር ይስማማሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ትረምፕ አስታውቀዋል። ትረምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋራ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፣ ኢራን ለድርድር ትቀርባለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉና፣ ይህም ለኢራን መልካም ሁኔታዎችን ሊፈጥር እንደሚችል ጠቁመዋል። “ደብዳቤውን ለማግኘት የፈለጉ ይመስለኛል፣ ሌላው አማራጭ ግን አንድ ነገር ማድረግ ይኖርብናል፣ ምክኒያቱም የኑክሌር መሣሪያ እንዲኖራቸው መፍቀድ  አይቻልም “ ብለዋል ትረምፕ፡፡ ደብዳቤው የተላከው ለኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ኻሚኒ እንደሆነ  የተገመተ ሲሆን፣ ይህንኑ ከኋይት ሃውስ ለማጣራት የተደረገው ሙከራ መልስ ባለመገኘቱ እንዳልተሳካ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል። የሩሲያው ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ርያብኮቭ የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም አስመልክቶ የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ጥረት በተመለከተ ከኢራኑ አምባሳደር ካዜም ጃላሊ ጋራ እንደተወያዩ የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ዓርብ አስታውቋል።

ሩቶና ኦዲንጋ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከቀድሞው ዋና ተፎካካሪያቸው ከራይላ ኦዲንጋ ጋራ በፖለቲካ ጉዳዮች ትብብር ለማድረግ ስምምነት ተፈራርመዋል። ሁለቱ ወገኖ
የአሜሪካ ድምፅ

ሩቶና ኦዲንጋ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከቀድሞው ዋና ተፎካካሪያቸው ከራይላ ኦዲንጋ ጋራ በፖለቲካ ጉዳዮች ትብብር ለማድረግ ስምምነት ተፈራርመዋል። ሁለቱ ወገኖች እየጨመረ ያለውን የሃገሪቱን ዕዳ እና ሙስናን ጨምሮ ሌሎቹንም ሃገሪቱን የገጠሟትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ አብረው ለመሥራት ተስማምተዋል። ሩቶ የግብር ጭማሪ እንደሚያደርጉ ማስታወቃቸውን ተከትሎ በሃገሪቱ በተነሳው ተቃውሞ ቢያንስ 60 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የነበራቸው የሕዝብ ድጋፍም እያሽቆለቆለ መጥቷል። ተቃውሞው በመበርታቱም ሩቶ ከተቃዋሚያቸው ከኦዲንጋና ከበርካታ የፓርቲ አባሎቻቸው ጋራ”ሰፊ መሠረት ያለው” መንግሥት ለመመስረት እንዲሠሩ አስገድዷቸዋል። ይህንን ስምምነትም ዛሬ በይፋ በመፈረም ሃገሪቱ የገጠማትን ችግሮች ለመቅረፍ በጋራ እንደሚሠሩ አስታውቀዋል። ጉምቱ የተቃዋሚ ፖለቲከኛው ራይላ ኦዲንጋ በኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አምስት ጊዜ ተሳትፈው ሳይቀናቸው ቀርቷል። ስምምነቱ በሃገር ውስጥ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ያለመ እንደሆነ የ80 ዓመቱ ኦዲንጋ አስታውቀዋል። ሩቶ በበኩላቸው ስምምነቱ “ነፃነትና መልካም አጋጣሚዎች ለሁሉም መድረሳቸውን ማረጋገጫና ወደ ተስፋይቱ ምድር የሚወስድ መንገድም ነው” ብለዋል። የፖለቲካ ተንታኞች ስምምነቱን «እየተንኮታኮተ ያለው አገዛዝ እንዲያንሰራራ የተደረገ ሙከራ» ሲሉ ገልጸውታል።

በርእደ መሬት ጉዳት ሥራ ያቆመው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በርካታ ሠራተኞቹን ሊያሰናብት ነው

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በተደጋጋሚ ባጋጠመው ርእደ መሬት የመፍረስ ጉዳት የደረሰበት የከሰም ስኳር ፋብሪካ፣ በሺሕ ለሚቆጠሩ ሠራተኞቹ የመጨረሻ የስ
የአሜሪካ ድምፅ

በርእደ መሬት ጉዳት ሥራ ያቆመው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በርካታ ሠራተኞቹን ሊያሰናብት ነው

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በተደጋጋሚ ባጋጠመው ርእደ መሬት የመፍረስ ጉዳት የደረሰበት የከሰም ስኳር ፋብሪካ፣ በሺሕ ለሚቆጠሩ ሠራተኞቹ የመጨረሻ የስንብት ማስታወቂያ አወጣ፡፡ የፋብሪካው ሠራተኞች ማኅበር ውሳኔውን «አግባብነት የሌለው» ሲል ተችቷል፡፡ «ፋብሪካው ለሠራተኞቹ የስንብት ማስታወቂያ ከማውጣቱ በፊት ሌሎች አማራጮችን መመልከት ነበረበት፤» ብሏል ማኅበሩ፡፡ የፋብሪካው ሠራተኞች በበኩላቸው፣ «በስንብት ማስታወቂያው ተደናግጠናል፡፡ ውሳኔው አኹን ያለውን የኑሮ ውድነት እና የጸጥታ ስጋት ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው፤» ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ የፋብሪካው አመራሮች፣ ውሳኔያቸውን አስመልክቶ እስከ አኹን ለብዙኃን መገናኛ የሰጡት መግለጫ የለም፡፡ የአሜሪካ ድምፅም ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጎ አልተሳካለትም፡፡ የአገሪቱን የስኳር ፋብሪካዎች በበላይነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ ፋብሪካው ሠራተኞቹን ለማስቀጠል በሚያስችል ቁመና ላይ አይደለም፤ ብሏል፡፡ የአገር አቀፍ እርሻ እና አግሮ ኢንዱስትሪ ሠራተኛ ማኅበራት ፌዴሬሽን ደግሞ፣ በሠራተኞቹ ላይ ስለደረሰው ጉዳት እና በመጻኢ ዕድላቸው ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋራ እየተወያየ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በጋምቤላ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ የሟቾች ቀጥር ከ30 መብለጡ ተገለጸ

በጋምቤላ ክልል በኑዌር ዞን በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና ከአንድ ሺሕ በላይ የሚደርሱ ደግሞ በበሽ
የአሜሪካ ድምፅ

በጋምቤላ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ የሟቾች ቀጥር ከ30 መብለጡ ተገለጸ

በጋምቤላ ክልል በኑዌር ዞን በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና ከአንድ ሺሕ በላይ የሚደርሱ ደግሞ በበሽታው መታመማቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ። የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ ሓላፊ አቶ ጋትቤል ግርማ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ወረርሽኙ ቀድሞ የተከሠተባቸው ዋንታዎ እና አኮቦ ወረዳዎች፣ አኹንም ስርጭቱ ከፍተኛ እንደኾነ ጠቅሰው፣ መድኃኒትም በበቂ ኹኔታ አልቀረበም፤ ብለዋል። ከጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ ወደ ከፍተኛ አመራሮች ስልክ ብንደውልም ጥሪው ባለመነሣቱ ምክንያት ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም።  

የአሜሪካ እና የካናዳ መሪዎች ስለዘገዩት ቀረጦች እና ስለ ንግድ ነክ ጉዳዮች ተወያዩ

የዩናይትድ ስቴትስ እና የካናዳ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ትላንት ረቡዕ በንግድ እና ሌሎች ጉዳዮች ውይይት አካሂደዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ት
የአሜሪካ ድምፅ

የአሜሪካ እና የካናዳ መሪዎች ስለዘገዩት ቀረጦች እና ስለ ንግድ ነክ ጉዳዮች ተወያዩ

የዩናይትድ ስቴትስ እና የካናዳ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ትላንት ረቡዕ በንግድ እና ሌሎች ጉዳዮች ውይይት አካሂደዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕም፣ ከካናዳ እና ከሜክሲኮ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ አዲስ የተጣለውን የ25 ከመቶ ቀረጥ ለአንድ ወር አዘግይተዋል ። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ «በጋራ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች፣ በድንበር ደህንነት መጠናከር ፣ በንግድ ልውውጥ እና የኢኮኖሚ ብልጽግና» ሁለቱ ሀገሮች በትብብር መሥራታቸውን ለመቀጠል ስለሚችሉበት መንገድ መወያየታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ትረምፕ ቀረጡን ማዘግየታቸውን ከማስታወቃቸው በፊት ከትላልቆቹ የዩናይትድ ስቴትስ መኪና አምራቾች፣ ከፎርድ፣ ጀነራል ሞተርስ እና ስቴላንቲስ የሥራ አስፈፃሚዎች ጋር መነጋገራቸውን የኋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሮላይን ሌቪት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ ትረምፕ መኪና አምራቾቹ፣ የማምረቻ ቦታዎቻቸውን ከሜክሲኮ እና ካናዳ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በማዞር የሚጣልባቸውን ቀረጥ በጠቅላላ ማስወገድ እንዲችሉ ያሳሰቧቸው መሆኑንም ቃል አቀባይዋ አክለዋል፡፡ ትረምፕ በሁለቱ ትላልቆቹ የአሜሪካ የንግድ ሸሪኮች ሌሎች ምርቶች ላይ የጣሏቸው አዲሶቹ ቀረጦች እንዳለ እንደሚቆዩ ሌቪት ገልጸዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሌሎችንም ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ማድረግ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ካሉ ለማጤን ዝግጁ መሆናቸውን ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል፡፡ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሀገራቸው ላይ የተጣሉ ሁሉም የአሜሪካ ቀረጦች እስካልተነሱ ድረስ፣ ካናዳ በአጸፋው የጣለቻቸውን ቀረጦች ለማስወገድ ፈቃደኛ አልሆኑም ። የኦንታርዮ ክፍለ ግዛት አገረ ገዥ ደግ ፎርድ “ወደ አሜሪካ በሚላኩ የካናዳ ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ቀረጥ ባለበት ከቀጠለ በካናዳ የሚገኙ የተሽከርካሪ ማምረቻዎች በ10 ቀናት ውስጥ መዘጋት ይጀምራሉ” ብለዋል፡፡ “ሰዎች ሥራቸውን ያጣሉ” ሲሉም ፎርድ አክለዋል፡ የካናዳ የክልል መሪዎች በዩናይትድ ስቴትስ ገበያ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ከሌሎች አገሮች ጋር የንግድ ልውውጥን ለማስፋት እየሰሩ ነው፡፡ ትረምፕ በቻይና ምርቶች ላይ የጣሉትን ቀረጥ በእጥፍ በማሳደግ 20 ከመቶ በማድረሳቸው የአክሲዮን ገበያው እንዲያሽቆለቁል እና ሸማቾች ላይ ዋጋ የመጨመር ስጋት እንዲፈጠር አድርጓል። ሜክሲኮ፣ ካናዳ እና ቻይና ለትረምፕ እርምጃ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የአጸፋ ቀረጥ እንደሚጥሉ አስታውቀዋል። ፕሬዝደንት ትረምፕ በትሩዝ ሶሻል መድረካቸው ላይ ባወጡት ጽሁፍ «ትሩዶ ሀገራቸው ላይ የተጣሉትን አዳዲስ ቀረጦች በሚመለከት ምን ማድረግ እንደሚቻል ትላንት ረቡዕ ስልክ ደውለው ጠይቀውኝ ነበር፡፡ እኔም በካናዳ እና በሚከሲኮ ድንበር በኩል የሚገባው ፈንቲኔል ብዙ ሰው ገድሏል፡፡ ያ መቆሙን የሚያሳምን ነገር አላገኘሁም አልኳቸው፡፡ ከበፊቱ ተሻሽሏል አሉ፡፡ እሱ በቂ እንዳልሆነ ነግሬአቸዋለሁ » ብለዋል፡፡

አሜሪካ የመረጃ ልውውጥ ማቋረጧን ተከትሎ ፈረንሳይ ለዩክሬን የስለላ መረጃ ማጋራት ቀጥላለች

የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስትር ሴባስቲየን ለኮርኑ ሀገራቸው ለዩክሬን የስለላ መረጃ እያጋራች መሆኗን ዛሬ ሐሙስ ተናገሩ፡፡ ርምጃው ዩናይትድ ስቴትስ ከዩክሬ
የአሜሪካ ድምፅ

አሜሪካ የመረጃ ልውውጥ ማቋረጧን ተከትሎ ፈረንሳይ ለዩክሬን የስለላ መረጃ ማጋራት ቀጥላለች

የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስትር ሴባስቲየን ለኮርኑ ሀገራቸው ለዩክሬን የስለላ መረጃ እያጋራች መሆኗን ዛሬ ሐሙስ ተናገሩ፡፡ ርምጃው ዩናይትድ ስቴትስ ከዩክሬን ጋራ የምታደርገውን የመረጃ ልውውጥ አቋርጫለሁ ማለቷን ተከትሎ የተሰማ ነው። ርምጃው የተወሰደው የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች በብራሰልስ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በተገኙበት  የመከላከያ ወጪያቸውን በማሳደግ እና ዩክሬን ከሩሲያ ጋራ በምታደርገው ጦርነት ድጋፍ ለመስጠት ቃል ስለ መግባት ውይይት ባደረጉበት በዛሬው ዕለት መሆኑ  ነው፡፡ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከውይይቱ በፊት የአውሮፓ ኅብረት አባላት “ወደፊት ወሳኝ ርምጃዎችን እንደሚወስዱ” ተናግረዋል፡፡ በአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ስለምትሰጠው ድጋፍ በወሰደው የአቋም ለውጥ ስጋት ያላቸው መሆኑንም ማክሮን ገልጸዋ፡፡ «የአውሮፓ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በዋሽንግተን ወይም በሞስኮ መወሰን የለበትም» ብለዋል ማክሮን፡፡ ትረምፕ ባለፈው ሳምንት ከዘሌንስኪ ጋራ በኋይት ሀውስ ካደረጉት አወዛጋቢ ውይይት በኋላ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለኪቭ ተዋጊዎች የምትሰጠውን ወታደራዊ ርዳታ እንድታቆም በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ አዘዋል። የየዩናይትድ ስቴትስ የማዕከላዊ ስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለጊዜው የስለላ መረጃ ለኪቭ መረጃ ማጋራቷን ማቆሟን ትላንት ረቡዕ ተናግረዋል:: ሆኖም ዘሌንስኪ በኋይት ሀውስ ከትረምፕ ጋራ የነበራቸውን ልውውጥ “የሚጸጽት” በማለታቸውን እና ሀገራቸው  ከሩሲያ ጋራ ለሚደረገው የሰላም ድርድር ዝግጁ መሆኗን በመናገራቸው  የመረጃ ልውውጡ መቋረጥ ለረጅም ጊዜ ላይቆይ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

ሐማስ የትረምፕ አስተያየት እስራኤል ከስምምነቱ እንድታፈገፍግ ያበረታታል አለ

ዩናይትድ ስቴትስ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሐማስ  “የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛቻዎች እስራኤል ከጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንድትወጣ እያበረታታ ነው
የአሜሪካ ድምፅ

ሐማስ የትረምፕ አስተያየት እስራኤል ከስምምነቱ እንድታፈገፍግ ያበረታታል አለ

ዩናይትድ ስቴትስ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሐማስ  “የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛቻዎች እስራኤል ከጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንድትወጣ እያበረታታ ነው” ሲል ዛሬ ሐሙስ ተናገረ። ሐማስ ይህን የገለጸው፣ ትረምፕ ሐማስ ጋዛ የሚገኙ ቀሪዎቹን ታጋቾች ካልፈታ “ ከባድ ቅጣት ያገኘዋል” ካሉ አንድ ቀን በኋላ ነው። ትረምፕ ትሩዝ ሶሻል በተባለው የማኅበራዊ መገናኛ መድረካቸው ላይ “ሁሉንም ታጋቾች ሳይዘገይ፣ አሁኑኑ ልቀቁ ፣ የገደላችኋቸውን ሰዎች አስከሬንም በሙሉ አሁኑኑ መልሱ፡፡ ካልሆነ አለቀላችሁ።” ብለዋል፡፡ ትረምፕ አክለውም “እስራኤል ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጋትን ሁሉን ነገር እየላኩ ነው፡፡ ያልኩትን  ካላደረጋችሁ አንድም የሐማስ አባል አይተርፍም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ የተኩስ አቁሙ የመጀመሪያው ምዕራፍ ባለፈው ቅዳሜ አብቅቷል። በስምምነቱ መሠረት ሐማስ 33 እስራኤላውያን ታጋቾችን እና አምስት የታይላንድ ዜጎችን ሲለቅ፣ እስራኤል 2 ሺሕ የሚጠጉ የፍልስጤም እስረኞች ለቃለች። ኋይት ሀውስ ከሐማስ ጋራ በቀጥታ ውይይት ማድረጉን ትላንት ረቡዕ አረጋግጧል። “ውይይቱ ያተኮረው አሁንም በጋዛ ታግተው የሚገኙ አሜሪካውያንን ስለ መልቀቅ ነው” ሲሉ፣ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች ገልጸዋል። የኋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ካሮላይን ሌቪት ንግግሮቹን “ለአሜሪካ ሕዝብ የሚጠቅመውን ለማድረግ በቅን ልቦና የተደረገ ጥረት ነው” ሲሉ ገልፀውታል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት በሰጠው መግለጫ ደግሞ እስራኤል «ከሐማስ ጋራ በቀጥታ መነጋገርን በሚመለከት ያላትን አቋም ለአሜሪካ አስታውቃለች» ብሏል። የጋዛ ጦርነት የጀመረው፣ ሐማስ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2023 እስራኤል ላይ ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት፣ 1ሺሕ 200 የሚጠጉ ሰዎችን ከገደለ እና 250 ሰዎች አግቶ ከወሰደ በኋላ ነበር። እስራኤል በአፀፋው ጋዛ ላይ በወሰደችው ጥቃት ከ48 ሺሕ 400 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል ሲል የጋዛው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቋል።

ትረምፕ በምክር ቤት ንግግራቸው የአስተዳደራቸውን የመጀመሪያ እርምጃዎች አወደሱ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ማክሰኞ  ምሽት ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች ጣምራ ጉባኤ ባሰሙት ንግግር የፌዴራል መንግሥቱን መጠን እና ተጽዕኖ ለመቀነ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ በምክር ቤት ንግግራቸው የአስተዳደራቸውን የመጀመሪያ እርምጃዎች አወደሱ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ማክሰኞ  ምሽት ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች ጣምራ ጉባኤ ባሰሙት ንግግር የፌዴራል መንግሥቱን መጠን እና ተጽዕኖ ለመቀነስ አስተዳደራቸው የወሰዳቸውን ቀዳሚ ርምጃዎች በማድነቅ አውስተዋል፡፡ በአሜሪካ የቅርብ የንግድ አጋሮች ላይ የጣሉትን ከፍተኛ ቀረጥ እና ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመመከት የገባችውን ጦርነት እንድታቆም  የሚያደርጉትን ግፊት ጨምረው ዘርዝረዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የታደሙ ዲሞክራት የምክር ቤቶቹ አባላት በበኩላቸው ተቃውሟቸውን ግልጽ አድርገዋል። የአሜሪካ ድምጽ የኋይት ሀውስ ቢሮ ኃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ  ያደረሰችንን ዘገባ አሉላ ከበደ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

ቻይና የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም ትላልቅ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ማቀዷን ይፋ አደረገች

ቻይና የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያስችሏትን ፕሮጀክቶች እንደምታዘጋጅ ዛሬ ረቡዕ አስታውቃለች። ፕሮጀክቶቹ እ.አ.አ ከ2030 አስቀድማ የካርበን ዳይኦክ
የአሜሪካ ድምፅ

ቻይና የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም ትላልቅ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ማቀዷን ይፋ አደረገች

ቻይና የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያስችሏትን ፕሮጀክቶች እንደምታዘጋጅ ዛሬ ረቡዕ አስታውቃለች። ፕሮጀክቶቹ እ.አ.አ ከ2030 አስቀድማ የካርበን ዳይኦክሳይድ በካይ ጋዝ ልቀቷን መጠን በመገደብ በ2060 ደግሞ ከካርበን ልቀት ነፃ የሚያደርጋት መሆኑን አመልክታለች። ሙቀት አማቂ ጋዞችን በብዛት ወደ አየር በመልቀቅ ከዓለም ቀዳሚ የሆነችው ቻይና፣ በባሕር ዳርቻዎች ላይ አዳዲስ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን እንደምታለማ እና በበረሃማ አካባቢዎች «አዳዲስ የኃይል መሠረተልማቶችን» እንደምትገነባ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እቅድ አውጪ ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። ሪፖርቱ አክሎ «ቻይና የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እና በሂደት ሙሉ ለሙሉ ለማቆም በንቃት እና በጥንቃቄ ትሰራለች» ብሏል። ሆኖም በሀገሪቱ የድንጋይ ከሰል ቁልፍ የኃይል ምንጭ ሆኖ እንደሚቀጥል ያመለከተው ሪፖርቱ፤ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን እያቀደች ባለችበት ወቅትም በዚህ ዓመት የድንጋይ ከሰል ምርትና አቅርቦትን ማሳደጓን እንደምትቀጥል ገልጿል። 

በኮንጎ ግጭት ምክንያት ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ ርዳታ አቆመች

ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ የልማት ርዳታ ማቆሟን እና ቃል የገባቻቸውን ድጋፎችም እየገመገመች መኾኑን ዛሬ ማክሰኞ አስታውቃለች። ጀርመን ይህን ር
የአሜሪካ ድምፅ

በኮንጎ ግጭት ምክንያት ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ ርዳታ አቆመች

ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ የልማት ርዳታ ማቆሟን እና ቃል የገባቻቸውን ድጋፎችም እየገመገመች መኾኑን ዛሬ ማክሰኞ አስታውቃለች። ጀርመን ይህን ርምጃ የወሰደችው፣ ሩዋንዳ በጎረቤቷ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚካሄደው ግጭት ውስጥ ላላት ሚና ምላሽ ለመስጠት ነው። የጀርመን ልማት ምኒስትር ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ በርሊን ውሳኔዋን አስቀድማ ለሩዋንዳ ማሳወቋን እና በምስራቅ ኮንጎ የበላይነት እያገኘ ላለው የኤም 23 አማፂ ቡድን የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቆም ማሳሰቧን አመልክተዋል። ኮንጎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሞያዎች እና የምዕራብ ኃያላን ሀገሮች ሩዋንዳ አማፂውን ቡድን ትደግፋለች በማለት ይከሷታል። ክሱን የምትቃወመው ሩዋንዳ በበኩሏ በኮንጎ የቱትሲ ተወላጆችን ለመጨፍጨፍ እና ለሩዋንዳ ስጋት ለመፍጠር ከሚንቀሳቀሱ የሁቱ ተወላጅ ታጣቂዎች እራሷን እየተከላከለች እንደሆነ ትገልጻለች። የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የጀርመን ውሳኔ «የተሳሳተ እና አሉታዊ ውጤት ያለው ነው» ሲል ምላሽ ሰጥቷል። መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ «በቀጠናው በተደጋጋሚ ለሚከሰቱ አለመረጋጋቶች ታሪካዊ ኃላፊነት የተሸከሙ እንደ ጀርመን ያሉ ሀገራት ለአንድ ወገን ያደላ አስገዳጅ ርምጃዎችን ከመተግበር የተሻለ ማወቅ ነበረባቸው» ብሏል። የጀርመን ምኒስቴር እንደገለፀው በርሊን፣ እ.አ.አ ከጥቅምት 2022 እስከ 2024 ላለው ጊዜ የ98 ሚሊየን ዶላር ርዳታ ለሩዋንዳ ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር። 

የደቡብ ሱዳን ጦር የምክትል ፕሬዝደንቱን ቤት ከቧል

ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቻር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው የታጠቀ ቡድን፤ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኝ የጦር ሠፈር  መውረሩን ተከትሎ፣ የመን
የአሜሪካ ድምፅ

የደቡብ ሱዳን ጦር የምክትል ፕሬዝደንቱን ቤት ከቧል

ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቻር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው የታጠቀ ቡድን፤ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኝ የጦር ሠፈር  መውረሩን ተከትሎ፣ የመንግሥቱ ወታደሮች ዛሬ በዋና ከተማዋ ጁባ የሚገኘውን የምክትል ፕሬዝደንቱን መኖሪያ ቤት ከበዋል፡፡ በርካታ አጋሮቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል። ማቻር፤ ባለፈው ወር የመንግሥት ባለስልጣን የነበሩ በርካታ አጋሮቻቸው  መባረራቸው እ.አ.አ በ2018 በእሳቸው እና በፖለቲካ ተቀናቃኛቸው ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ ይጥላል ብለው ነበር። በሁለቱ ተቀናቃኞች መካከል ለአምስት ዓመታት በተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ለማቻር ታማኝ የነበሩት የጦሩ ምክትል አዛዥ ጀነራል ጋብሪኤል ዱፕ ላም በሰሜኑ ግዛት ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ትላንት ማክሰኞ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በተመሳሳይ የማቻር አጋሩ  የነዳጅ ዘይት ሚኒስትር  ፑት ካንግ ቾል ከጠባቂዎቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ዛሬ ረቡዕ  በቁጥጥር ስር ውለዋል። የታሰሩበት ምክንያት ግን እስካሁን አልተገለጸም። የምዕራብ ሀገራት ልዑካን መሪዎቹ ውጥረቱን እንዲያረግቡ ባለፈው ሳምንት አሳስበው ነበር። ደቡብ ሱዳን እ.አ.አ በ2018 የተደረሰውን ስምምነት እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ያላደረገች ሲሆን ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው ምርጫም በገንዘብ እጦት ምክንያት ለሁለት ዓመት ተራዝሟል። 

ትረምፕ «አሜሪካ ተመልሳለች» አሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ማክሰኞ ምሽት በአሜሪካ የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ያደረጉትንን ንግግር «አሜሪካ ተመልሳ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ «አሜሪካ ተመልሳለች» አሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ማክሰኞ ምሽት በአሜሪካ የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ያደረጉትንን ንግግር «አሜሪካ ተመልሳለች» በማለት የጀመሩት ሲኾን፣ የሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች «ዩ ኤስ ኤ» በሚል ዝማሬ አጅበዋቸዋል። «ከስድስት ሳምንት በፊት እዚህ ቆሜ የአሜሪካን ወርቃማ ዘመን ዐውጄ» ነበር ያሉት ትራምፕ ከዚያን ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ታላቅ እና ስኬታማ ዘመን ለማምጣት ፈጣን እና የማያቋርጥ ተግባራት ተከናውነዋል« ብለዋል። »አስተዳደራቸው በ43 ቀናት ውስጥ ብቻ ሌሎች ብዙ አስተዳደሮች በአራት እና ስምንት ዓመታት ውስጥ ካከናወኗቸው የበለጠ መሠራቱን« የገለጹት ትረምፕ »ገና እየጀመርን ነው« ብለዋል። ትረምፕ እስካሁን 76 የፕሬዝደንት ማዘዣዎችን የፈረሙ ሲሆን አብዛኞቹ በፍርድቤት ክስ ተመስርቶባቸዋል። ትረምፕ ንግግራቸውን ከጀመሩ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በምክር ቤቱ አዳራሽ ከተሰበሰቡ ሰዎች በተሰማ የስላቅ ድምፅ ንግግራቸው በመስተጓጎሉ የተወካዮች ምክርቤቱ አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን የምክርቤቱ ሥነ ስርዐት አስከባሪዎች፣ በቴክሳስ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው ለምክርቤት አባልነት የተመረጡትን አል ግሪን ከምክርቤቱ እንዲያስወጧቸው አዘዋል። ሌሎች የምክር ቤቱ አባላትም ሥነ-ስርዐት እንዲከተሉ አሳስበዋል። ግሪን ከምክርቤቱ አዳራሽ ከወጡ በኋላ ትረምፕ ንግግራቸውን ቀጥለዋል። ተረምፕ በዚኹ የማክሰኞ ምሽት ንግግራቸው »የመጀመሪያው ወር የፕሬዝደንትነት ዘመኔ፣ በሀገራችን ታሪክ እጅግ ስኬታማው መሆኑን ብዙዎች ገልጸውታል« ያሉት ትራምፕ፣ በድንበር በኩል የሚፈፀም ሕገወጥ ሽግግርን ለማስቆም የወሰዱትን ርምጃም አብራርተዋል። »በሀገራችን ላይ የሚፈፀመውን ወረራ ለመመከት« በደቡባዊ ድንበር ላይ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጃቸውን እና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር በድንበር ላይ እንዲሰፍ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት »ባለፈው ወር በሕገወጥ መንገድ ድንበር አያርጠው የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር እስከዛሬ ከተመዘገበው ዝቅተኛ ነው« ብለዋል። በተጨማሪም ወደ ዋይት ሐውስ እንደተመለሱ የፌደራል ቅጥር ሂደቶች እና የውጭ ርዳታዎች ላይ እግድ መጣላቸውን ገልጸዋል። የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ቁጥር እና ሠራተኞችን ለመቀነስ፣ በምፅሃረ ቃሉ 'ዶጅ' በመባል የሚጠራ በኢላን መስክ የሚመራ ተቋም መመስረታቸውን የተናገሩት ትረምፕ በቢሊየኖች የሚቆጠር የመንግሥት ገንዘብ እያዳነ መሆኑንም አመልክተዋል። ትረምፕ በንግግራቸው በዩናይትድ ስቴትስ በ48 ዓመት ውስጥ ያልታየውን የዋጋ ግሽበት ለማስተካከል ከወሰዷቸው ርምጃዎች መካከል »ወርቃማ ፈሳሽ« ሲሉ የጠሩትን የነዳጅ ጋዝ ቁፋሮ እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል። »የወሳኝ እና ብርቅዬ ማዕድናት« ምርት እንደሚፋጠንም ገልጸዋል። »ቀጣዩ የግብር ቅነሳ ነው« ያሉት ትራምፕ፣ ከገቢ ግብር፣ ከቲፕ ገንዘብ እና ከትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ግብር እንደሚያነሱም ተናግረዋል። ትረምፕ አክለው አሜሪካን »ኢ-ፍትሃዊ« ሲሉ ከገለጹት የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት፣ »ሙሰኛ« ካሉት የዓለም ጤና ድርጅት እና »ፀረ-አሜሪካዊ« ሲሉ ከገለፁት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ማስወጣታቸውን አብራርተዋል። የፕሬዝደንት በዓለ ሲመት ባልተካሄደባቸው ዓመታት »ዘ ስቴት ኦፍ ዘ ዩኒየን« በመባል የሚጠራው እና የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ለጋራ ምክርቤቱ የአሜሪካን አኹናዊ ሁኔታ በሚያብራሩበት በዚህ ንግግር፤ ትራምፕ ለዩናይትድ ስቴትስ ኢኮኖሚ እና ኢሚግሬሽን ፖሊሲ ያላቸውን ርዕይ ለሕዝብ የሚያቀርቡበት እና የፌደራል ሠራተኞችን ቅነሳ እና ከዩክሬን ፕሬዝደንት ጋራ የነበራቸውን እሰጥ አገባ አስመልክቶ የሚያብራሩበት ዕድል ፈጥሮላቸዋል። ትረምፕ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋራ ያደረጉትን ኃይለቃል የተሞላበት ውይይት ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ርዳታ አቋርጣለች። »አውሮፓውያን ዩክሬንን ከመደገፍ ይልቅ ከሩስያ ለሚገዙት ነዳጅ እና ዘይት የበለጠ አውጥተዋል« ያሉት ትራምፕ የዩክሬን ፕሬዝደንት ለሰላም ዝግጁ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደፃፉላቸው አመልክተዋል። ትረምፕ አክለው »በተመሳሳይ ጊዜ ከሩሲያ ጋራ ጠንከር ያለ ውይይት አድርገን ለሰላም ዝግጁ መኾናቸውን የሚያሳይ ምልክቶች አግኝተናል" ብለዋል።

እስራኤል ዕርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ በማገዷ የረድኤት ድርጅቶች ስጋት ገብቷቸዋል

እስራኤል ከውሃ በስተቀር ማንኛውም የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ ማገዷ፣ ወትሮውንም በሕይወት ለመቆየት ትግል ላይ ባሉት ሕፃናትና ቤተሰቦቻቸው
የአሜሪካ ድምፅ

እስራኤል ዕርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ በማገዷ የረድኤት ድርጅቶች ስጋት ገብቷቸዋል

እስራኤል ከውሃ በስተቀር ማንኛውም የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ ማገዷ፣ ወትሮውንም በሕይወት ለመቆየት ትግል ላይ ባሉት ሕፃናትና ቤተሰቦቻቸው ላይ አደገኛ ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት  የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታውቋል። “ትላንት በዕርዳታ ላይ የተጣለው እገዳ የሲቪሎችን ሕይወት ለመታደግ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል” ሲሉ የቀጠናው የዩኒሴፍ ኅላፊ ኤድዋርድ ቤግበደር አስታውቀዋል። የሕፃናትን ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ የሆነው የተኩስ አቁም መቀጠሉ አስፈላጊ እንደሆነም ኅላፊው ጨምረው ተናግረዋል። በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ልዑክ የሆኑት ስቲቨን ዊትኮፍ ተኩስ አቁሙ እስከ እ.አ.አ ሚያዚያ 20 ድረስ እንዲራዘም መጠየቃቸውን ያወሱት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ይህም የረመዳን ወር እና የአይሁድ በዓላትን የሚሸፍን ሲሆን፣ በዚህ ወቅት በመጀመሪያው ቀን ሃማስ ግማሽ የሚሆኑ ታጋቾችን እንደሚለቅ፣ በመቀጠል ቋሚ የተኩስ ማቆም ሲፈጸም ደግሞ የተቀሩትን ታጋቾች እንደሚለቅ ተናግረዋል። “ይህን ሃሳብ እቀበላለሁ፣ ሃማስ ግን እስከ አሁን እየተቃወመው ነው” ሲሉ አክለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እስራኤል ዕርዳታ እንዳይገባ ያገደችው ሃማስ ዕርዳታውን በመስረቁ እና ፍልስጤማውያን እንዳያገኙት በማድረጉ እንደሆነም ኔታንያሁ አስታውቀዋል። “ዕርዳታውን ለሽብር ተግባር እየተጠቀመብት ነው” ሲሉም ክስ አሰምተዋል። የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ኔታንያሁ የጠቀሱት ጉዳይ ስለመከሰቱ በሥፍራው የሚገኙ ባልደረቦቻቸው ሪፖርት እንዳላደርጉ አስታውቀዋል።

ትረምፕ የጣሉትን ቀረጥ ተከትሎ ሜክሲኮ፡ ካናዳ እና ቻይና የአጸፋ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠነቀቁ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ መጣላቸውን ተከትሎ ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይናም በየበኩላቸው የአጸ
የአሜሪካ ድምፅ

ትረምፕ የጣሉትን ቀረጥ ተከትሎ ሜክሲኮ፡ ካናዳ እና ቻይና የአጸፋ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠነቀቁ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ መጣላቸውን ተከትሎ ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይናም በየበኩላቸው የአጸፋ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠነቀቁ። ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ዋና ዋና የንግድ ሸሪኮቿ ሜክሲኮ እና ካናዳ በሚልኳቸው ምርቶች ላይ የጣለችው አዲስ የ25 በመቶ ቀረጥ ዛሬ ተግባራዊ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ዛሬ የሚጀምረው እና  በቻይና ምርቶች ላይ የጣለችውን ቀደም ሲል 10 በመቶ የነበረውን ተጨማሪ ቀረጥ በእጥፍ አሳድጋው 20 በመቶ ማስገባቷ ታውቋል። ትረምፕ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚፈልሱትን ሕገ-ወጥ ስደተኞች እና ድንበር ተሻግሮ የሚጓጓዘውን ሕገ ወጥ እና አደገኛ መድሃኒት ዝውውር እንዲያግዱ የጠየቋቸው ሁለቱ የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ጎረቤቶች ሜክሲኮ እና ካናዳ የተባለውን ማድረጋቸውን ይፋ ካደረጉም በኋላ አዲሱን ቀረጥ ጥለውባቸዋል። ትረምፕ በትላንትናው ዕለት ይህንኑ ማስታወቃቸውን ተከትሎም ሦስቱ የዩናይትድ ስቴትስ ዋና ዋና የአክሲዮን ገበያዎች ከፍተኛ ውድቀት ሲያስመዘግቡ፤ ዛሬ ማለዳ በአክሲዮን ገበያዎቹ መክፈቻ ላይም እያንዳንዳችው በ2 በመቶ አዘቅዝቀው ታይተዋል። ከሦስቱ ሀገራት በሚገቡ ምርቶች ላይ በጣሉት ከፍተኛ የቀረጥ ጭማሪ የተነሳ አሜሪካውያን ሸማቾች እና የንግድ ድርጅቶች አንዳንድ ጊዜያዊ የኢኮኖሚ ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል’ ያሉት ትረምፕ «ነገር ግን በሦስቱ አገሮች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች የቀረጥ ክፍያውን ለማስቀረት ሲሉ ፋብሪካዎቻቸው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለማዘዋወር ይገደዳሉ» ሲሉ  ተናግረል። ይህ በእንዲህ እንዳለ  ትረምፕ ለወሰዱት የቀረጥ ጭማሪ አገራቸው አፀፋ እንደምትሰጥ የተናገሩት የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ "ይህ ፍትሃዊነት የጎደለው እርምጃ በዋዛ አይታለፍም”ብለዋል። አክለውም አገራቸው 107 ቢሊዮን ዶላር በሚገመቱ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ የምትጥል መሆኗን ተናግረዋል።

የለጋሾች ድጋፍ በመቀነሱ  መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አዲስ የርዳታ ምንጭ እየፈለጉ ነው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በግጭት ወቅት የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶች ጉዳይ ልዩ ተወካይ ፣”በዓለም አቀፍ ደረጃ ወታደራዊ ወጪ እያደገ ሲሄድ ፣ ግጭት ይጨምራል
የአሜሪካ ድምፅ

የለጋሾች ድጋፍ በመቀነሱ  መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አዲስ የርዳታ ምንጭ እየፈለጉ ነው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በግጭት ወቅት የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶች ጉዳይ ልዩ ተወካይ ፣”በዓለም አቀፍ ደረጃ ወታደራዊ ወጪ እያደገ ሲሄድ ፣ ግጭት ይጨምራል፡፡ በዚያ ደግሞ በዋናነት የሚጎዱት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው« ሲሉ ተናገሩ። ኮሎምበስ ማቭሁንጋ እንደዘገበው፣ በግጭት ቀጣና ውስጥ ያለውን ስቃይ ለማስታገስ የሰብአዊ ረድዔት ድርጅቶች፣ እንደ ሳዑዲ አረቢያ ያሉ ከተለመዱት የተለዩ አዳዲስ የገንዘብ ድጋፍ ምንጮችን በመፈለግ ላይ ናቸው። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በግጭት ውስጥ የሚፈጸሙ የፆታዊ ጥቃቶች ጉዳይ ልዩ ተወካይ ፕራሚላ ፓተን በሪያድ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ርዳታ መድረክ ላይ ለቪኦኤ ሲናገሩ “ዓለም አቀፋዊ ግጭቶች በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ” እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡ »እያየን ያለነው በግጭቶች ወቅት ፆታዊ ጥቃት በብዛት እንደሚፈጸም ነው፣” ያሉት ፓተን “ በዚህ ደግሞ ሰላማዊ ዜጎች በሙሉ በጣም ይጎዳሉ፣ በይበልጥ የሚጎዱት ግን ሴቶች እና ልጃገረዶችው። በመከላከል ላይ የበለጠ መሥራት ይኖርብናል። መገለልን፣ ድህነትን፣ የፆታ እኩልነት መዛባትን ዋና መንስኤ ለመፍታት መሥራት አለብን። በእርግጥ ምላሽ መስጠት ይኖርብናል፣ መከላከል ግን ላይ የበለጠ መሥራት ያለብን ይመስለኛል።” ብለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ስር ያሉና በሳዑዲ አረብያ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የተሳተፉ ብዙ የሰብአዊ ቡድኖች ነባሮቹ «የምዕራባውያን» ለጋሾች የገንዘብ ድጋፋቸውን ቀንሰዋል ወይም አቁመዋል ሲሉ ተናግረዋል። ምንም እንኳን በፍርድ ቤቶች በኩል ሕጋዊ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም፣ የትረምፕ አስተዳደር በብዙ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የውጭ ርዳታን ለማቁረጥ ተንቀሳቅሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዩኒሴፍ የተመድ የህጻናት እርዳታ ድርጅት አቅርቦት ክፍል ዳይሬክተር ሌይላ ፓካላ ተቋማቸው “ከ109 ሚሊዮን በላይ ተጋላጭ ህጻናትን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት 9.9 ቢሊዮን ዶላር እየፈለገ ነው” ብለዋል። «በዚህ ዓመት በሰብአዊነት ዙሪያ የሚያስፈልገውን ሁሉ ስንመለከት በአመጋገብ ይሁን፣ በውሃ እና በንፅህና አጠባበቅ ይሁን፣ በጤና ተደራሽነት፣ እና ህጻናት ክትባት እንዳያጡ ለማድረግ ተጨማሪ ፍላጎቶች መኖራቸውን እንመለከታለን፣ “ ሲሉ ፓካላ ያለው አቅም ከፍላጎቶች ጋር እየተራመደ እንዳልሆነም አክለዋል። ፓካላ አያይዘውም »በዓለም ዙሪያ በከባድ አጣዳፊ የምግብ እጦት የሚሰቃዩ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ ነው። በግጭት ዞኖች እና ያልተረጋጉ ሁኔታዎች ወይም በደቡባዊ አፍሪካ እንዳየነው በማያቋርጥ ድርቅ ፣ ጎርፍ እና የከባድ አውሎ ነፋስ በመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች፣ በሚሰጥ የመጀመሪያው አጣዳፊ ምላሽ እጥረት ህጻናትና ቤተሰቦች እየተጎዱ ነው።” በማለት “ያለው ፍላጎት ምላሽ ከመስጠት አቅም በላይ ነው።” ብለዋል። ኤስ.ኦ. ኤስ ኢንተርናሽናል የህፃናት መንደር የተባለው ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት ፕሬዝደንት፣ ደረጀ ወርዶፋ፣ “የአየር ንብረት ለውጥ ለአጠቃላዩ ሰብአዊ ቀውስ አስተዋፅዖ እያደረገ ነው” ይላሉ።“ሁኔታው “በተለይም በምስራቅ እና በደቡባዊ አፍሪካ እየተባባሰ ነው። ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ በሰብአዊ ቀውስ የተጎዱ ብዙ ሰዎች አሉ። “ የሚሉት ደረጀ “ለእነዚህ የተጎዱ ማኅበረሰቦች አገልግሎቶችን እና ቁሳቁሶችን ለማምጣት የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን በጣም በጣም ከፍተኛ ነው። የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድጋፍ ወደዚህ ደረጃ እና የፍላጎት መጠን እየመጣ አይደለም” ይላሉ። አንዳንድ ቡድኖች የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ፊታቸውን ወደ ሳዑዲው- የንጉሥ ሳልማን የሰብአዊ እና የአስቸኳይ ርዳታ ማእከል (KSRelief) ወደ መሳሰሉ ድርጅቶች ፊታቸውን እያዞሩ ነው። የዚህ ድርጅት (KSRelief) የአጋርነት እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ሃና ኦማር፣ “ግጭቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ ብዙ ሰዎችን ለችግር መዳረጉን” ገልጸው፣ ድርጅቱ ብዙ የአፍሪካ ሀገራትን እየረዳ ነው ይላሉ። ኦማር አክለውም “ርዳታ ለማድረስ፣ ለእነዚህ ሰዎች መብት የምንሟገትበትን መንገዶች ለመፈለግ እና ለተቸገሩት መድረሳችንን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን። ሰዎች አሁንም እነዚህን ሁሉ ተግዳሮቶች ለመፍታት እና መፍትሄዎችንም እንደሚፈልጉ ተስፋ አለ።” ብለዋል። በዚህ ዓመት ድርጅቱ (KSRelief) ከሳውዲ አረቢያ ውጪ የሰብአዊ ሥራውን የጀመረበትን 10ኛ ዓመት ሲያከብር “የሰብአዊ ምላሽን የወደፊት እጣ ፈንታን ማሰስ” በሚል መሪ ቃል ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር የሰአብ አዊ ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

አውሮፓን ዳግም ማስታጠቅ? .. የአውሮፓ ሕብረት የተግባር ጥሪ አጀንዳ 

ዋሽንግተን ለዩክሬን የምትሰጠው የጦር መሣሪያ ዕርዳታ በድንገት እንዲቋረጥ በተደረገበት፤ ሃሳብ የገባቸው የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ከሩስያ ወታደራዊ እንቅስ
የአሜሪካ ድምፅ

አውሮፓን ዳግም ማስታጠቅ? .. የአውሮፓ ሕብረት የተግባር ጥሪ አጀንዳ 

ዋሽንግተን ለዩክሬን የምትሰጠው የጦር መሣሪያ ዕርዳታ በድንገት እንዲቋረጥ በተደረገበት፤ ሃሳብ የገባቸው የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ከሩስያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጋር በተዛመደ የሕብረቱን የመከላከያ አቅም ለማጎልበት በሚያስችሉ መንገዶች ዙሪያ ለመምከር የፊታችን ሃሙስ ብረስልስ ላይ እንደሚሰበሰቡ ተገለጠ። “ጥያቄው የአውሮፓ ደኅንነት በተጨባጭ አደጋ ላይ ወድቋል፣ ወይም አውሮፓ ደህንነቷን ለማስከበር የምትወስደውን ኃላፊነት ማሳደግ አለባት’ የሚለው አይደለም” ያሉት የአውሮፓ ኮሚሽነር ኡርሱላ ቮን ደር ሊን “ከፊታችን ያለው ትክክለኛ ጥያቄ አውሮፓ ሁኔታው በሚጠይቀው ደረጃ ቁርጠኛ ምላሽ ለመስጠት፣ ብሎም በሚፈለገው ፍጥነት እና እቅድ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ማረጋገጥ ነው” ብለዋል። የሕብረቱ ኮሚሽነር ከጉባኤው አስቀድሞ በሰጡት አስተያየት፣ በርካታ ዝርዝሮች ያቀፈውን የ840 ቢሊዮን ዶላር የመከላከያ በጀት ዕቅድ 27 አባል አገራት ላሉት ሕብረት አቅርበዋል። ኮሚሽነሯ ያስተላፉት ይህ መልእክት ‘የዩናይትድ ስቴትስ የአጋርነት ተሳትፎ የሚጓደልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል’ በሚል ሥጋት የአሕጉሪቱ መሪዎች በተገኙባቸው በርከት ያሉ አስቸኳይ ስብሰባዎች ላይም ተስተጋብቷል። ዋሽንግተን ‘የአውሮፓ መሪዎች ተጨማሪ ኃላፊነት እንዲወስዱ’ በሚል ለዓመታት ስታሰማ የቆየችው ጥሪ እና የወቅቱ ሁኔታ አዲሱን የአውሮፓ የመከላከያ ወጪ ዕቅድ ቅርብ አድርገውታል። ይሁንና የሕብረቱ አባላት አንዳንድ ፈተና ከገጠማቸው መንግሥታት እና ኢኮኖሚዎች፤ ሁኔታውን አስመልክቶ የጎላ ጥርጣሬ የሚያንጸባርቁ ማሕበረሰቦች እስካሉባቸው፤ እና በአመዛኙ ለሩስያ ተስማሚ የሆነ ቀኝ ዘመም አመለካከት ያላቸው ኃይሎች እየገነኑ የመጡባቸው አገራት የደቀኑት ፈተና ድረስ የአሕጉሪቱን መከላከያ የማጎልበቱን ጥረት አቀበት ያደርጉታል ተብሏል።

 ኬንያ ውስጥ በስደተኞች የምግብ ዕደላ ወቅት በተቀሰቀሰ ግጭት ተረጂዎች ተጎዱ

ሰሜን ኬንያ በሚገኘው ካኩማ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት ፖሊስ በወሰደው ርምጃ አራት ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ። በትላንቱ የምግብ ዕ
የአሜሪካ ድምፅ

 ኬንያ ውስጥ በስደተኞች የምግብ ዕደላ ወቅት በተቀሰቀሰ ግጭት ተረጂዎች ተጎዱ

ሰሜን ኬንያ በሚገኘው ካኩማ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት ፖሊስ በወሰደው ርምጃ አራት ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ። በትላንቱ የምግብ ዕደላ ላይ የተቀሰቀሰው ግጭት ለስደተኛው ከሚሰጠው የምግብ ርዳታ እጥረት ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል። ከኬንያ አጎራባቾች ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲ እና ኮንጎ ግጭቶችን በመሸሽ እና በድርቅ ሳቢያ የሚሰደዱ ወገኖችን በሚያስጠልለው ካምፕ ውስጥ ለሚገኙት በብዙ ሺሕዎች የሚገመቱ ስደተኞች ይሰጥ የነበረው የምግብ አቅርቦት፤ በተፈጠረው የርዳታ ገንዘብ እጥረት የተነሳ የወትሮ አሠራሩ መስተጓጎሉ ተዘግቧል። በካምፑ ለስደተኞች የሚሰጠውን ምግብ የሚያከፋፍለው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለፈው ታኅሣሥ ወር ለስደተኞች ከሚሰጠው ምግብ "በገጠመው የአቅርቦት እጥረት የተነሳ ከሚያስፈልገው ከ45 በመቶ በታች እንደነበር አመልክቷል። የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከለጋሽ አገሮች መንግሥታት ያገኝ የነበረው መዋጮ እጥረት እንደሚገጥመው ለዓመታት ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወቃል።

ዓመታዊው የቻይና የፖለቲካ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ በቤጂንግ ላይ የጣለችው ቀረጥ ተፈጻሚ ከሚሆንበት ዕለት ጋር ተገጣጥሟል

ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ላይ የጣለችው ተጨማሪ ቀረጥ በጀመረበት እና ፕሬዝዳንት ሺ «ውስብስብ እና ዘርፈ ብዙ» ያሏቸውን የምጣኔ ፈተናዎች ለመፍታት የሚ
የአሜሪካ ድምፅ

ዓመታዊው የቻይና የፖለቲካ ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ በቤጂንግ ላይ የጣለችው ቀረጥ ተፈጻሚ ከሚሆንበት ዕለት ጋር ተገጣጥሟል

ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ላይ የጣለችው ተጨማሪ ቀረጥ በጀመረበት እና ፕሬዝዳንት ሺ «ውስብስብ እና ዘርፈ ብዙ» ያሏቸውን የምጣኔ ፈተናዎች ለመፍታት የሚያስችሉ መላዎች ፍለጋ በያዙበት ባሁኑ ወቅት፤ ቻይና ዓመታዊውን ታላላቅ የፖለቲካ ጉባኤዋን ጀምራለች። ከዛሬ አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ የቻይና ልሂቃን እና የሃገሪቱ ምክር ቤት አባላት የ2025ቱን የፖሊሲ አጀንዳዎች ለመቅረጽ የሚያግዝ መሆኑ በተነገረለት ጉባኤ መሳተፍ ይዘዋል። ከንግዱ ማሕበረሰብ እና ከከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት እስከ የአገሪቱ መንግሥት እና የፓርቲው የፖለቲካ አማካሪዎች ጉባኤ ሰፊ የሕዝብ ውክልና ያላቸው ከተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገናኝተዋል። ነገ ረቡዕ በአመዛኙ የመንግሥቱን አመለካከት የሚያስተጋባው ብሔራዊ ምክር ቤት፣ ዓመታዊውን የሕግ አውጭዎች ጉባኤ ይጀምራል። ጠቅላይ ሚንስትር ሊ ኪያንግ በበኩላቸው በሥፋት የሚጠበቀውን የመንግሥቱን የ2025 የኢኮኖሚ እድገት እና ሌሎች ቁልፍ የምጣኔ ሃብት ፖሊሲዎች የሚያስረዳውን የመንግሥቱን የሥራ ሪፖርት በምክር ቤቱ የመክፈቻ ጉባኤ ላይ ያቀርባሉ። የዘንድሮው ጉባኤ የሚካሄደው የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በእጅጉ በተዳከመበት፣ የአገር ውስጥ ገበያ ፍላጎት በተቀዛቀዘበት፣ ባለ ሃብቱ እና ሸማቹ በኢኮኖሚው ይዞታ ላይ ያለው ዕምነት ባዘቀዘቀበት፣ በንብረት ባለቤትነቱ ዘርፍ የታየው ቀውስ በቀጠለበት  ብሎም በዓለም አቀፉ የንግድ ዘርፍ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የተጀመረው የንግድ ጦርነት አንድምታ እያጠላ ባለበት ባሁኑ ወቅት ነው። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በሁሉም የቻይና ምርቶች ላይ የጣለው ተጨማሪ የ10 በመቶ ቀረጥ ዛሬ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል። በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፈተናዎች በተደቀኑበት የሚካሄደው የዘንድሮው የብሔራዊ ምክር ቤቱ ጉባኤ፣ የቻይና መሪዎች “የፖለቲካ አንድነት” ፕሮጀክት ለመንደፍ እና አገሪቱ “በሺ ጂንፒንግ አመራር ታላቅ ሃገር ለመሆን በሚያበቃት ትክክለኛ መንገድ ላይ መሆኗን ለማሳየት መልካም አጋጣሚ ለማድረግ ይጠቀሙበታል” ሲሉ ተንታኞች አስተያየታቸውን ፈንጥቀዋል።

ግጭት በቀጠለባት ኢትዮጵያ በወባ ወረርሽኝ የሚሞተው ሰው ቁጥር እየጨመረ መኾኑ ተነገረ

በአንድ ወር ዕድሜ ውስጥ አራት ሕጻናት ልጆቻቸውን በወባ ወረርሽኝ መነጠቃቸውን ሳግ እየተናነቃቸው የተናገሩት አቶ ለማ ተፈራ፤ በሚኖሩበት የኦሮሚያ ክልል የቀ
የአሜሪካ ድምፅ

ግጭት በቀጠለባት ኢትዮጵያ በወባ ወረርሽኝ የሚሞተው ሰው ቁጥር እየጨመረ መኾኑ ተነገረ

በአንድ ወር ዕድሜ ውስጥ አራት ሕጻናት ልጆቻቸውን በወባ ወረርሽኝ መነጠቃቸውን ሳግ እየተናነቃቸው የተናገሩት አቶ ለማ ተፈራ፤ በሚኖሩበት የኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት ባይኖር ኖሮ የልጆቻቸውን ሕይወት ማትረፍ ይቻል ነበር ብለው እንደሚያምኑ ያስረዳሉ። አርሶ አደሩ አክለውም “በግጭቱ ሳቢያ መንደራችን ውስጥ ለወባ መከላከያ የሚረዳው መድኃኒት እና የሕክምና አገልግሎት አልነበረም" ሲሉ በስልክ ላነጋገራቸው የኤኤፍፒ ዘጋቢ አስረድተዋል። በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ከሚከሰተው ቁጥሩ ከ250 ሚሊዮን በላይ የወባ ተጋላጭ እና በዚሁ ወረርሽኝ ሳቢያ ለሕልፈት ከሚዳረገው ከ600 ሺሕ በላይ ሕዝብ 95 በመቶው አፍሪካውያን መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ባለፉት በርካታ ዓመታት በኦሮሚያ ክልል በመንግሥቱ ኃይሎች እና በአማፂው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦላ) መካከል ተባብሶ የቀጠለው ግጭት የጤና አገልግሎት አቅርቦቱን ክፉኛ እያስተጓጎለ መኾኑን ባለሞያዎች ይገልጻሉ። በርካታ ልጆቻቸውን በወባ ወረርሽኝ ሳቢያ ላጡት እና የሰባት ልጆች አባት እንደሆኑት እንደ አቶ ለማ ላሉ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ገቢ ለሚተዳደሩ አርሶ አደሮች ሁኔታው ቀድሞውንም ከባድ እንደነበር ያስረዱት ሃኪሞች፣ ሌሎች ባለሞያዎች እና የርዳታ ሠራተኞች ለኤኤፍፒ በሰጡት አስተያየት አክለውም፤ የአየር ንብረት ለውጡ እና በአካባቢው የቀጠለው ግጭት ተዳምረው ሁኔታውን እጅግ የከፋ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። በተያያዘ ዜና ካለፈው ዓመት ጥር ወር አንስቶ እስከ ጥቅምት ድረስ በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ7.3 ሚሊዮን በላይ የወባ ወረርሽኝ ተጋላጮች እና 1,157 የሚደርስ የሟች ቁጥር መመዝገቡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ይህም አሃዝ በቀደመው የአውሮፓውያኑ 2023 ከተመዘገበው በእጥፍ መጨመሩ እና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከታየው እና ለሕልፈት ከተዳረጉት ግማሽ ያህሉ በኦሮሚያ መሆኑ ተመልክቷል።

Get more results via ClueGoal