የአላባማዋ ሰልማ ከተማ 60ኛውን 'የሰንበት ሰቆቃ' መታሰቢያ አከበረች
newsare.net
እ.አ.አ በመጋቢት 7፣ 1965፣ በዩናይትድ ስቴትስ አላባማ ግዛት፣ ሰልማ ከተማ ውስጥ የመምረጥ መብት እንዲሰጣቸው ጥንድ ጥንድ እየሆኑ በኤድመንድ ፔተስ ድልድይ ላይየአላባማዋ ሰልማ ከተማ 60ኛውን 'የሰንበት ሰቆቃ' መታሰቢያ አከበረች
እ.አ.አ በመጋቢት 7፣ 1965፣ በዩናይትድ ስቴትስ አላባማ ግዛት፣ ሰልማ ከተማ ውስጥ የመምረጥ መብት እንዲሰጣቸው ጥንድ ጥንድ እየሆኑ በኤድመንድ ፔተስ ድልድይ ላይ የተጓዙ ሰልፈኞችን ከፊት ከሚመሩት መካከል አንዱ ቻርለን ሞልዲን ነበሩ። ሰልፈኞቹ ነጭ ባለሥልጣናት፣ ጥቁር አላባማውያን ድምፅ ለመስጠት እንዳይመዘገቡ መከልከላቸውን እና ከቀናት በፊት ጂሚ ሊ ጃክሰን የተሰኘው ሚኒስትር እና የመምረጥ መብት አደራጅ፣ በመንግሥት ወታደሮች ተተኩሶበት መገደሉን ተቃውመው ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ነበሩ። ድንገት ግን ከአላባማ ወንዝ ጫፍ ላይ ምን እንደሚጠብቃቸው ተመለከቱ፤ በፈረስ ላይ የተቀመጡ ሰዎች፣ የመንግስት ተወካዮች እና ወታደሮች። እየቀረቡ ሲመጡ የሕግ አስከባሪ አካላት እንዲበታተኑ ማስጠንቀቂያ ሰጧቸው፣ ብጥብጥም ተፈጠረ። በወቅቱ የ17 ዓመት ወጣት የነበሩት ሞልዲን ሁኔታውን ሲያስታውሱ «ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፖሊሶቹ ጋሻቸውን አውጥተው ይገፉን ጀመር። ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ሕፃናትን መምታት፣ አስለቃሽ ጋዝ መጠቀም እና በኤሌክትሪክ ማንዘር ጀመሩ» ይላሉ። ሰልማ ከተማ ትላንት እሑድ «በደም የታጠበው እሑድ» በመባል የሚጠራውን ጥቃት 60ኛ ዓመት አክብራ ውላለች። በሰልፈኞቹ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መላ ሀገሪቱን ያስደነገጠ ሲሆን እ.አ.አ በ1965 ድምፅ የመስጠት መብት እንዲፀድቅ ድጋፍ አስገኝቷል። በዚህ ዓመታዊ መታሰቢያ የጥቁሮች የመምረጥ መብት እንዲከበር ለታገሉ ክብር የተሰጠ ሲሆን፣ እኩልነት ለማምጣት ለሚደረገው ትግልም በድጋሚ ጥሪ ቀርቧል። የዘንድሮ በዓል የተከበረው በመምረጥ መብት ዙሪያ አዳዲስ ክልከላዎች እየመጡ ነው የሚል ስጋት ባየለበት እና የትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ ለሁሉም ዜጎች ዲሞክራሲያዊ እንድትሆን የረዱ የፌደራል ተቋማት እንደአዲስ እንዲቋቋሙ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት ነው። ዓመታዊው ክብረ በዓል የሚጠናቀቀው 'በደም የታጠበው እሁድ' በተፈፀመበት የኤድመንድ ፔተስ ድልድይ ላይ የእግር ጉዞ በማድረግ ነው። Read more