ውጥረቱ እያየለ በመጣባት ሰርቢያ ተቃዋሚዎች ወደ ዋናው የሰርቢያ ቴሌቭዥን ጣቢያ የሚወስደውን መንገድ ዘግተው ዋሉ
newsare.net
በመቶዎች የተቆጠሩ ተማሪዎች ውጥረቱ እያየለ በመጣባት የባልካን ሀገር፣ ለፊታችን ቅዳሜና እሑድ ከታቀደው ግዙፍ ሰልፍ ቀናት አስቀድመው ቤልግሬድ የመንግሥቱውጥረቱ እያየለ በመጣባት ሰርቢያ ተቃዋሚዎች ወደ ዋናው የሰርቢያ ቴሌቭዥን ጣቢያ የሚወስደውን መንገድ ዘግተው ዋሉ
በመቶዎች የተቆጠሩ ተማሪዎች ውጥረቱ እያየለ በመጣባት የባልካን ሀገር፣ ለፊታችን ቅዳሜና እሑድ ከታቀደው ግዙፍ ሰልፍ ቀናት አስቀድመው ቤልግሬድ የመንግሥቱን የሰርቢያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ህንጻ ዘግተው ውለዋል። ለሳምንቱ መጨረሻ የተጠራው ግዙፍ ሰልፍ ለወራት የቀጠለው የጸረ መንግሥት ተቃውሞ መዳረሻ ተደርጎ ታይቷል። ማዕከላዊ ቤልግሬድ የሚገኘውን የቴሌቭዥን ሕንጻ ትላንት ማምሻው ላይ የዘጉት ተማሪዎች፣ ዛሬ ማክሰኞም ብዙ መቶዎች ኾነው ተሰባስበው የመንገድ መዝጋቱ ጥረት ለተጨማሪ 22 ሰዓታት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በሁለተኛዋ የሃገሪቱ ትልቅ ከተማ ኖቪ ሳድ’ም ተመሳሳይ ተቃውሞ ተደራጅቷል። በኖቪ ሳድ የባቡር ጣቢያ የኮንክሪት ጣሪያ ተደርምሶ የ15 ሰዎች ህይወት ካጠፋ በኋላ፣ በየዕለቱ የሚካሄዱትን ሰልፎች የሚያደራጁት በተለያዩ የሰርቢያ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ተማሪዎች ናቸው። የተቃውሞ ሰልፎቹ የሕዝበኝነት አቀንቃኙን የፕሬዝዳንት አሌክሳንዳር ቩቲች አገዛዝ እና ሥልጣን የሙጥኝ ብለው በመቀጠል የያዙትን አቋም አናውጠዋል። ትላንት ሰኞ አመሻሹ ላይ በቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና የዜና እወጃ ወቅት እንግዳ የነበሩት የሰርቢያው ፕሬዝደንት በቃለ መጠይቁ ወቅት በተማሪዎች የሚመራውን የተቃውሞ ሰልፍ ሲዘልፉ ታይተዋል። «የጸጥታ ኃይሎች በቅዳሜው ታላቅ ሰልፍ ላይ የኃይል ርምጃ ይወስዳሉ» ሲልም አስጠንቅቀዋል። በመላ አገሪቱ የተካሄደውን መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ ከሥልጣን አልወርድም ሲሉ የዛቱት ቩቲች «ሃሳባችሁ እኔን መተካት ከሆነ የምትተኩኝ ገድላችሁኝ ነው» ሲሉ ተደምጠዋል። ተማሪዎቹ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት ከቩቲች እና ከአስተዳደራቸው ጎን የቆመውን የመንግሥቱን ቴሌቭዥን ጣቢያ ፈጸመ ላሉት ድርጊት ተጠያቂ አድርገዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቩቲች በዛሬው ዕለት ቤልግሬድ ከገቡት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የበኩር ልጅ ዶናልድ ትረምፕ ጁኒየር ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። የጉብኝቱ ዓላማ ግን ለጊዜው አልታወቀም።ሩሲያው ቩቲች የፕሬዝደንት ትረምፕ ዋና ደጋፊ መሆናቸው ይታወቃል። Read more