የአውሮፓ ኅብረት በትግራይ ያለው ውጥረት እንደሚያሳስበው ገለፀ
newsare.net
በትግራይ ክልል ያለው ውጥረት በንግግር እንዲፈታ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ጠይቀዋል። አምባሳደሯ ሶፊ ፍሮም፣ በኅብረቱ እና በኢትዮጵያ የሁለየአውሮፓ ኅብረት በትግራይ ያለው ውጥረት እንደሚያሳስበው ገለፀ
በትግራይ ክልል ያለው ውጥረት በንግግር እንዲፈታ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ጠይቀዋል። አምባሳደሯ ሶፊ ፍሮም፣ በኅብረቱ እና በኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ዛሬ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ ለሰብአዊ መብቶች መሻሻልም መሥራት እንዳለባት ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኤመንስበርገር ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 2 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ አምባሳደሯ፣ ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ ላይ፣ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶችን እና ውጥረቶችን በተመለከተ ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል፡፡ በዋናነት፣ በፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ግምገማ እና ከህወሓት ሕጋዊ ቁመና ጋራ በተገናኘ ያለውን አለመግባባት ተከትሎ በትግራይ ክልል ያለው ውጥረት የአውሮፓ ኅብረትን እንደሚያሳስብ አምባሳደሯ ገልፀዋል፡፡ በክልሉ ያለው ውጥረት እንዲሁም በአማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ Read more