የእስራኤል ወግ አጥባቂዎች ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የሚያስወጣ «የፍልሰት ባለሥልጣን» ለማቋቋም አቅደዋል
newsare.net
የእስራኤል አክራሪ ወግ አጥባቂዎች ከ2.3 ሚሊዮኑ ፍልስጤማውያን ብዙዎቹ ጋዛን ለቀው እንዲወጡ የሚያደርገውን የፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕን እቅድ በደስታ ተየእስራኤል ወግ አጥባቂዎች ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የሚያስወጣ «የፍልሰት ባለሥልጣን» ለማቋቋም አቅደዋል
የእስራኤል አክራሪ ወግ አጥባቂዎች ከ2.3 ሚሊዮኑ ፍልስጤማውያን ብዙዎቹ ጋዛን ለቀው እንዲወጡ የሚያደርገውን የፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕን እቅድ በደስታ ተቀብለዋል። “ስደትን ማበረታታት ዓለም አቀፍ ሕግን አይጥስም” ይላሉ። ፍልስጤማውያን ግን እቅዱን ውድቅ አድርገውታል። የእስራኤሉ የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች ፍልስጤማውያን ጋዛን ለቀው እንዲወጡ ለማበረታታት በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ «የፍልሰት ባለሥልጣን» እያቋቋሙ መኾኑን ተናግረዋል። ቤዛሌል ስሞትሪች፣ የእስራኤል የገንዘብ ሚኒስትር “ስደትን ለማበረታታት የምናወጣው እያንዳንዱ ብር፣ ደጋግመን በመታገል ከምንከፍለው ዋጋ ያነሰ ነው። በጀቱ ለዚህ እቅድ እንቅፋት አይሆንም፣ ይህ ሌላ እቅድ ብቻ አይደለም። በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስራኤል ታሪካዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል አቅም ነው« ብለዋል። የኬኔሴት አባል የሆኑት ሲምቻ ሮትማን ይህ »ወደሌላ ቦታ የማዛወር« እቅድ በቅርቡ በግብጽ እና በአረብ ሊግ ከቀረበው እቅድ የበለጠ ተጨባጭ ነው፣ የእነሱ እቅድ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በአሸባሪነት የፈረጀችው ሐማስ ትጥቅ ሳይፈታ የፍልስጤም አስተዳደር፣ ጋዛን እንዲመራ ያስችለዋል።” ይላሉ። »ሰዎች ሐማስን መልሰን እናቋቁም ፣ ሐማስ ኃይሉን መልሶ እንዲገነባ ሁሉንም ዕድል እንስጥ ይላሉ።” ያሉት ሮትማን “ይህ እንዴት ተጨባጭ መፍትሔ ሊሆን ይችላል? አይደለም ፤ አደገኛ ነው። ለጋዛ አደገኛ ነው። ለጋዛ ሕዝብ አደገኛ ነው፤ እንዲሁም ለአካባቢው ሰላም አደገኛ ነው።” ሲሉ ሀሳቡን አጣጥለውታል። ቀኝ አክራሪዎቹ የህግ ምሁራን፣ የእስራኤልን የታሪክ እና የግዛት ሉአላዊነት ለማስከበር በሚሟገተው ቡድን ስብሰባ ላይ ሲናገሩ “ስደተኞችን ከጦርነት ቀጠና እንዲወጡ ማበረታት የዓለም አቀፍ ህግን መጣስ አይደለም” ብለዋል ። የከኮሄሌት ፖሊሲ መድረክ የህግ ምሁር የሆኑት ዩጂን ኮንቶሮቪች “በጦርነት ጊዜ ስደተኞች እንደሚኖሩ እናውቃለን። ከአፍጋኒስታን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች። ከሶሪያ ጦርነት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች፣ ከዩክሬን ጦርነት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች። ከእነዚህ ውስጥ አንዳቸውም የዘር ማፅዳት አልተባሉም። አሁን እንደዚህ ዓይነት ስደተኞችን ሆን ብሎ መፍጠር አይቻልም። በተለይ ጦርነትን ተከትሎ የመጣ በመሆኑ ምክንያት ግን ሊከለከል አይገባም።” ሲሉ ስደተኞችን አስመልክቶ የሚነሳውን የተቃውሞ ሀሳብን ተከላክለዋል። የእስራኤል ግራ ዘመም (ሊበራል) ድርጅቶች ተወካዮች ግን በዚህ አይስማሙም። በእስራኤል “ሰላም አሁን” ለተሰኘው እንቅስቃሴ የሰፈራ ፕሮጀክት ላይ የሚሰሩ ሃጊት ኦፍራን «ይህ ሰዎችን በፈቃደኝነት ማስወገድ አይደለም። ይህ ማፈናቀል ወይም ማስተላለፍ ነው። የጦር ወንጀል ነው። ሥነ ምግባር የጎደለው ነው። የሰዎችን ህይወት ስቃይ የበዛበት ካደረጋችሁ፣ ሰዎች ከዚያ ቦታ ለቀው መውጣት ይፈልጋሉ፣ በፈቃዳቸው መውጣታቸው ነው ማለት ግን አይደለም።” ይላሉ። ብዙዎቹ የካንሴት ቡድን አባላት ፣ እ.ኤ.አ. በ2005 እስራኤል ሙሉ ለሙሉ ግዛቱን ለቃ በወጣችበት ወቅት ከጋዛ ሰርጥ የለቀቁት 21 የአይሁድ ሰፈሮች፣ መልሰው እንዲመሰረቱ ጠይቀዋል። የረዥም ጊዜ የአይሁድ የሰፈራ ንቅናቄ መሪ ዳንዬላ ዌይስ ፣ ወደ ጋዛ ለመሄድ ዝግጁ መሆናቸውን ሲገልጹ»የእስራኤል ሰዎች ለመታገል ዝግጁ ናቸው፣ ጋዛውያን ወደ ሌላ ቦታ ለቀው እንዲሄዱ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ያቀረቡትን ሀሳብ ለመፈጸም ዝግጁ ናቸው፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ የእስራኤል ሕዝብ የአይሁድ ሰፋሪዎችን በመላው ጋዛ ለማስፈር፣ የጽዮናዊነትን ግብ ለመፈጸም ዝግጁ እና ፈቃደኞች ናቸው።” ብለዋል። በጋዛ የአይሁዶችን ሰፈራ መልሶ የመገንባት ተስፋ የማይመስል ቢመስልም፣ አብዛኞቹ እስራኤላውያን ሃማስ በወደፊቷ ጋዛ ምንም አይነት ሚና ሊኖረው እንደማይገባ ይስማማሉ፣ አንዳንዶች ይህን ለማረጋገጥ የተሻለው መንገድ አብዛኞቹ ፍልስጤማውያን ጋዛን ለቀው እንዲወጡ ማድረግ ነው ብለው ያምናሉ። Read more