የሩሲያ ሚሳይል ጥቃት በኦዴሣ አራት ሰዎች መግደሉን የዩክሬን ባለሥልጣናት አስታወቁ
newsare.net
የዩክሬን ባለሥልጣናት በደቡባዊ ዩክሬን የወደብ ከተማ ኦዴሣ፣ ሌሊቱን በደረሰ የሩሲያ ሚሳይል ጥቃት፣ አራት ሶሪያውያን ሲገደሉ፣ በርካቶች ቆስለዋል ሲሉ፣ ዛየሩሲያ ሚሳይል ጥቃት በኦዴሣ አራት ሰዎች መግደሉን የዩክሬን ባለሥልጣናት አስታወቁ
የዩክሬን ባለሥልጣናት በደቡባዊ ዩክሬን የወደብ ከተማ ኦዴሣ፣ ሌሊቱን በደረሰ የሩሲያ ሚሳይል ጥቃት፣ አራት ሶሪያውያን ሲገደሉ፣ በርካቶች ቆስለዋል ሲሉ፣ ዛሬ ረቡዕ አስታወቁ፡፡ የመልሶ ግንባታ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሌክሲ ኩሌባ በቴሌግራም ማኅበራዊ መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ ሚሳይሉ ወደ አልጄሪያ የሚላክ ስንዴ በመጫን ላይ በነበረች የጭነት መርከብ ላይ ጉዳት አድርሷል። ሩሲያ የዓለምን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ላይ የተሰማሩ ወደቦችን ጨምሮ የዩክሬን መሠረተ ልማቶችን እያጠቃች መኾኑ ተመልክቷል። ሌላ የሚሳይል ጥቃት በዲኒፕሮፔትሮቭስክ ክልል ውስጥ በምትገኘው የፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ የትውልድ ከተማ ክሪቪ ሪህ ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ በዚህ ጥቃት ቢያንስ አንድ ሰው ሲሞት ዘጠኝ ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የክልሉ ገዥ ተናግረዋል። አገረ ገዥው ሰርሂ ሊሳክ ክልሉ ከሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት እንደደረሰበት እና በጥቃቱም ከፍተኛ ፎቆች፣ አስተዳደራዊ ሕንፃዎች እና ትምህርት ቤት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። የዛፖሪዥያ ክልል ባለሥልጣናት የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላን ሕክምና ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት ማድረሱንም ገልጸዋል፡፡ የዩክሬን ጦር ዛሬ ረቡዕ እንዳስታወቀው የሩሲያ ጦር በአንድ ሌሊት ካስወነጨፋቸው 133 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ውስጥ 98ቱን መትቶ ማውረዱን አስታውቋል። ድሮኖቹ የተመቱት “በቼርካሲ፣ ቼርኒሂቭ፣ ዲኒፕሮፔትሮቭስክ፣ ካርኪቭ፣ ክኸርሰን፣ ክምለኒትስኪ፣ ኪይቭ፣ ኦዴሳ፣ ፖልታቫ፣ ሪቪኔ፣ ሱሚ፣ ቴርኖፒል፣ ቪኒትሲያ፣ ዛፖሪዥያ እና ዚሂቶሚር ክልሎች ላይ ነው” ሲል ጦር ሠራዊቱ ይፋ አድርጓል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ረቡዕ ፣ 21 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) አውድሟል፡፡ የአየር መከላከያው ድሮኖቹ የተመቱት በብሪያንስክ፣ ኩርስክ እና ካልጋ ክልሎች እንዲሁም በጥቁር ባህር እና በሩሲያ በተያዘው ክራይሚያ ውስጥ መኾኑን ገልጿል። የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት በዩክሬን ጥቃት ስለደረሰው ጉዳት እና ውድመት አልገለጹም። Read more