በቀነኒ አዱኛን አሟሟት ዙሪያ ፖሊስ ባለቤቷን ድምፃዊ አንዷለምን አስሮ እየመረመረ መኾኑን አስታወቀ
newsare.net
በኦሮምኛ ቋንቋ ዘፈኑ የሚታወቀው አንዷለም ጎሳ ባለቤት፣ ሞዴልና የማስታወቂያ ባለሞያ ወ/ሮ ቀነኒ አዱኛ ዋቆ ፣ ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት አካባበቀነኒ አዱኛን አሟሟት ዙሪያ ፖሊስ ባለቤቷን ድምፃዊ አንዷለምን አስሮ እየመረመረ መኾኑን አስታወቀ
በኦሮምኛ ቋንቋ ዘፈኑ የሚታወቀው አንዷለም ጎሳ ባለቤት፣ ሞዴልና የማስታወቂያ ባለሞያ ወ/ሮ ቀነኒ አዱኛ ዋቆ ፣ ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት አካባቢ ከቤቷ ማብሰያ ክፍል በኩል ካለው በረንዳ 5ኛ ፎቅ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወድቃ ለሕክምና ርዳታ ወደ ያኔት ሆስፒታል እየተወሰደች ባለበት ወቅት ሕይወቷ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ አስታውቋል፡፡ ክስተቱ በተፈጸመበት ወቅት በቤት ውስጥ ነበረ ያለውን ባለቤቷን፣ ድምፃዊ አንዷለም ጎሳን በቁጥጥር ስር አውሎ እየመረመረ መሆኑንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል። ለቤተሰቡ ቅርበት ያላቸውን ምንጮች፣ ጥንዶቹ በሕግ ትዳር አለመመስረታቸውን ጠቅሰው የፍቅር አጋር መኾናቸውን ትላንት ለአሜሪካ ድምጽ የገለጹ ሲኾን፣ በአንድ ቤት ውስጥ ሦስት ዓመት አብረው እንደኖሩንም ነግረውናል። ነገር ግን ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አርቲስ አንዷለም ጎሳ የቀነኒ አዱኛ ባለቤት መኾኑን ጠቅሷል። ፖሊስ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣው በዚኽ መግለጫ፣ የምርመራ ቡድን በማዋቀርና ቦታው ድረስ በመሄድ ለምርመራ ሥራ የሚጠቅሙት ተገቢ መረጃዎች ማሰባሰቡን ገልጿል። የሟችንም አስከሬን ወደ ዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል ለተጨማሪ ምርመራ መላኩን እማ የመጨረሻውን የምርመራ ውጤትም በቀጣይ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ምዕራብ ሐረርጌ ውስጥ የተወለደችው ቀነኒ፣ ሞዴልና የማስታወቂያ ባለሞያ ነበረች። የባህላዊ አልባሳትን በመልበስ በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በይበልጥ ትታወቅ ነበር። Read more