በግሪንላንድ ምርጫ ያሸነፈው ፓርቲ የትረምፕን ዕቅድ ተቃወመ
newsare.net
በግሪንላንድ በተካሄደው የምክር ቤት ምርጫ፣ ሀገሪቱ በሂደት ከዴንማርክ ነጻ እንድትወጣ የሚደግፈው ዴሞክራቲት ፓርቲ ያልተጠበቀ ድል ተቀዳጅቷል፡፡ የትላንበግሪንላንድ ምርጫ ያሸነፈው ፓርቲ የትረምፕን ዕቅድ ተቃወመ
በግሪንላንድ በተካሄደው የምክር ቤት ምርጫ፣ ሀገሪቱ በሂደት ከዴንማርክ ነጻ እንድትወጣ የሚደግፈው ዴሞክራቲት ፓርቲ ያልተጠበቀ ድል ተቀዳጅቷል፡፡ የትላንት ማክሰኞው ምርጫ የተካሄደው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ደሴቲቱን ለመጠቅለል ያላቸውን እቅድ ይፋ ባደረጉበት ድባብ ውስጥ ነው፡፡ ዲሞክራቲት ፓርቲ “የግዛቲቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስኑት የግሪላንድ ነዋሪዎች ናቸው” በማለት የትረምፕን ንግግር ሲቃወም ቆይቷል፡፡ “የምርጫው ውጤት ግሪንላንድ አትሸጥም የሚለውን ግልፅ መልዕክት ለትረምፕ ማስተላለፍ አለበት” ሲሉ የፓርቲው መሪ ጄንስ ፍሪደሪክ ኒልሰን ለስካይ ኒውስ ተናግረዋል። «እኛ አሜሪካዊ መሆን አንፈልግም። ፣ ዴኒሽ መኾንም አንፈልግም። የምንፈልገው ግሪንላንድነታችንን ነው። ወደፊትም ነፃነታችንን እንፈልጋለን። የራሳችንን ሀገር እርሳቸው በሚሰጡት ተስፋ ሳይሆን በራሳችን መገንባት እንፈልጋለን» ብለዋል። ግሪንላንድ ሞባይል ሞባይል ስልክ እና የታዳሽ ኅይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ ለመሥራት አስፈላጊ ግብዓት የኾኑ ውድ የምድር ማዕድናት ክምችት የያዘች ናት፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል የጦር ሰፈር የሚገኝባት ስትኾን ለሰሜን አትላንቲክ የአየር እና የባህል መስመሮች ቁልፍ የስትራቴጂ ስፍራ ናት፡፡ ትረምፕ ግሪንላንድን የመቆጣጠር ፍላጎታቸውን በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባኤ ባሰሙት ንግግር «ዩናይትድ ስቴትስ “በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ታገኛዋለች» ሲሉ ሐሳባቸውን ገልጸዋል። 56 ሺሕ የሕዝብ ብዛት ያላት ግሪንላንድ ከ300 ዓመታት በፊት የዴንማርክ ቅኝ ግዛት የነበረች ሲኾን አሁንም የውጭ እና የመከላከያ ፖሊሲዋን የምትቆጣጠረው ዴንማርክ ነች፡፡ Read more