የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግሥቱን ጣልቃ ገብነት ጠየቀ
newsare.net
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱን ጣልቃ ገብነት ጠየቀ። የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፣የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግሥቱን ጣልቃ ገብነት ጠየቀ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱን ጣልቃ ገብነት ጠየቀ። የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፣ “የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈርስ እና የትግራይ ሕዝብ ወደ ዳግም እልቂት ሲገባ ዝም ብሎ ማየት አይገባውም” ብሏል። በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራ ህወሓት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ሦስተኛ ወገን ወደ ክልሉ እንዲገባ መጥራት ተቀባይነት የሌለው እና የፕሪቶርያው ስምምነት የሚጥስ ነው ብሏል። በተያያዘ ዜና በክልሉ ደቡብ ምስራቃዊ ዞን ዓዲጉደም በተባለ ከተማ የፀጥታ ኃይሎች ወሰዱት በተባለ ርምጃ፣ አራት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት እና በርካቶች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ ተፈጠረ ያለውን ቀውስና የፌደራል መንግሥቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቀበትን መግለጫ ተከትሎ እስካሁን ከአዲስ አበባ በይፋ የተሰጠ ምላሽም ይሁን አስተያየት የለም። የአሜሪካ ድምፅ ከመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት እና ከሌሎች የፌደራል መንግሥት አካላት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረትም አልተሳካም። ከሰሜኑ ጦርነት መጠናቀቅና ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው መጋቢት 2016 ዓ.ም ከትግራይ ክልል ከመጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋራ የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ክልሉን እንደገና ወደ ጦርነት ለመመለስ የሚሠሩ ያሏቸውንና በስም ያልጠቀሷቸውን አካላት በማንሳት የማሳሰቢያ መልዕክት ማስተላለፍቸው ይታወሳል። Read more