በሰሜን ጋዛ የእስራኤል ጥቃት 22 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም ባለሥልጣናት ተናገሩ
newsare.net
በሰሜን ጋዛ ዛሬ እሁድ በተፈጸመ የእስራኤል የአየር ድብደባ አብዛኞቹ ህጻናትና ሴቶች የሚገኙበት ቢያንስ 22 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርበሰሜን ጋዛ የእስራኤል ጥቃት 22 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም ባለሥልጣናት ተናገሩ
በሰሜን ጋዛ ዛሬ እሁድ በተፈጸመ የእስራኤል የአየር ድብደባ አብዛኞቹ ህጻናትና ሴቶች የሚገኙበት ቢያንስ 22 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ እስራኤል ጥቃቱ በታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ስትል የተዘገበውንም የሟቾችን ቁጥር አስተባብላለች። ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት ሰሜን ጋዛን በመነጠል የሚካሄዱት የእስራኤል ጥቃቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው በጋዛ ሰሜናዊ ክፍል ያለው የሰብአዊነት ሁኔታ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን የረድኤት ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡ ቀይ መስቀል ነዋሪዎች የሚያገኟቸው የምግብ፣ የውሃ እና የህክምና አቅርቦት ውስን ሲሆን በአካባቢው የተረፉት ጥቂት ሆስፒታሎች እየተጨናነቁ መምጣታቸውን አስታውቋል፡፡ በሰሜን ጋዛ በግጭቱ መካከል መውጫ አጥተው የሚገኙ ሰላማዊ ሰዎች የህክምና እንክብካቤ በማጣት የሚደርስባቸውን ዘግናኝ ሁኔታዎች ያሳሰበው መሆኑንም ቀይ መስቀል ጨምሮ ገልጿል፡፡ በተያያዘ ሌላ ዜና ፣ ዛሬ እሁድ በቴል አቪቭ ከተማ አካባቢ ወደሚገኝ የአውቶብስ ማቆሚያ ደርምሶ በገባ አንድ ከባድ መኪና 35 ሰዎች መቁሰላቸውን የእስራኤል የአደጋ ጊዜ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡ በእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ዋና መሥሪያ ቤት አቅራቢያ የደረሰውን አደጋ ባለሥልጣናት ሆን ተብሎ የተፈጸመ እንደሆነ ጠርጥረዋል፡፡ ስለ አሸከርካሪውና ዓላማው የገለጹት ዝርዝር ነገር የለም፡፡ አሽከርካሪው ወዲያውኑ ርምጃ እንደተወሰደበት ተነግሯል፡፡ Read more