ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬይን የምትሰጠውን ዕርዳታ መጠን ስታደርግ ’ጂ-20’ ቡድን ውስጥ ልዩነቶች እየታዩ ነው
newsare.net
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ሊያበቃ በቀረው የሁለት ወራት ዕድሜ ውስጥ አስተዳደራቸው ዩክሬይን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል ለያዘችው ጥረት የሚሰዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬይን የምትሰጠውን ዕርዳታ መጠን ስታደርግ ’ጂ-20’ ቡድን ውስጥ ልዩነቶች እየታዩ ነው
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን ሊያበቃ በቀረው የሁለት ወራት ዕድሜ ውስጥ አስተዳደራቸው ዩክሬይን የሩሲያን ወረራ ለመከላከል ለያዘችው ጥረት የሚሰጠውን የገንዘብ፣ የወታደራዊ እና የዲፕሎማሲያዊ ድጋፎች አሳድጓል። ሃያ የዓለም ሃገራት የተካተቱበትን የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ እያስተናገደች ባለችው የብራዚሏ የባሕር ዳርቻ ከተማ ሪዮ ዲ ጄኔሮ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ለዩክሬን የሚሰጠውን ድጋፍ አስመልክቶ “ብርቱ” ግፊት እያደረጉ መሆናቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮች ምክትል አማካሪ ጃን ፋይነር በትላንትናው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ሩስያ ባለፈው ሳምንት መገባደጂያ በዩክሬይን የፈጸመችውን የአየር ድብደባ ተከትሎ፤ ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች በሞስኮ ላይ ጠንካራ ትችት እንዲሰነዘር ግፊት እያደረጉ ነው። የሰሞኑም የሩስያ የአየር ጥቃት ለወራት ከታዩት ሁሉ ግዙፉ መሆኑ ተመልክቷል። ባለስልጣናቱ አክለውም የሩስያ ጥቃት ማየል ‘ከአውሮፓ የሚሻገር ያለመረጋጋት ተጽእኖ ሊያስከትል እንደሚችል’ አስጠንቅቀዋል። በሩስያዋ የከርስክ ግዛት የዩክሬን ኃይሎች የተቆጣጠሩትን አካባቢ ለማስለቀቅ ከ10 ሺሕ ላይ የሚሆኑ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሞስኮ መግባታቸውን ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩክሬን በወሩ መጀመሪያ ላይ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ሆኖም የመጨረሻው የመሪዎች መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ግፊት ያደረገችበትን አገላለጽ አላካተተም። መግለጫው ሩስያ የወሰደችውን እርምጃ ሳያወግዝ፤ ዩክሬን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ በሰው ልጆች ላይ በሚደርሰው ስቃይ እና በአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ባስከተለው አሉታዊ ተፅእኖ ላይ ትኩረት አድርጓል። የመካከለኛውን ጦርነት አስመልክቶም በጋዛ እና በሊባኖስ የተኩስ አቁም እንዲደረስ እና እስራኤል እና ፍልስጤም ነጻ ሃገር ሆነው በሰላም የሚኖሩበት የሁለት-አገሮች መፍትሄ የተባለው ይሳካ ዘንድ የሚያስፈልገውን ቁርጠኝነት ጠይቋል። የእስራኤልን ራስን የመከላከል መብት በተመለከተ ያለው የለም። ፋይነር አክለውም፤ በቡድኑ ከታቀፉት አገሮች ስብጥር አንጻር አለም አቀፍ ግጭቶችን አስመልክቶ ሁሉም የሚስማሙበት ሃሳብ መቅረጽ ቀላል አለመሆኑን አምነዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለኪቭ የምትሰጠውን ወታደራዊ ዕርዳታ ያሳደገችው ዩናይትድ ስቴትስ፤ ዩክሬን አሜሪካ-ሰራሹን የረዥም ርቀት ሚሳይሎች በሩሲያ ድንበር ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን ለመምታት እንድትጠቀምበት ፍቃድ መስጠቷን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣናትን ጠቅሰው የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ቡድን 20 - ባብዛኛው ተመሳሳይ እይታ የሚጋሩት የሰባቱ የዓለም ባለ ጸጋ ሃገሮች ካሉበት ቡድን 7 በተጨማሪ፤ ሩስያን፣ ቻይናን፤ እንዲሁም በደቡቡ የዓለም ንፍቀ ክበብ የሚገኙት አንዳንድ በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት ያጠቃልላል። Read more