የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንትን ለመያዝ የተደረገው ሙከራ ከሸፈ
newsare.net
የደቡብ ኮሪያ መርማሪዎች ተከሳሹን የአገሪቱ ፕሬዝደንት ዩን ሶክ ዮል በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የነበራቸውን ሙከራ አቁመዋል። መርማሪዎቹ ሙከራውን የተውት ፕሬየደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንትን ለመያዝ የተደረገው ሙከራ ከሸፈ
የደቡብ ኮሪያ መርማሪዎች ተከሳሹን የአገሪቱ ፕሬዝደንት ዩን ሶክ ዮል በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የነበራቸውን ሙከራ አቁመዋል። መርማሪዎቹ ሙከራውን የተውት ፕሬዝደንቱን ከመኖሪያ ቤታቸው ለመያዝ ያደርጉት ሙከራ በጠባቂዎቻቸው በመገታቱ ነው። የሀገሪቱ ሕግ አውጪ ምክር ቤት ፕሬዝደንቱን ከሥራቸው ያገደ ሲሆን፣ የመያዣ ትዕዛዙ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ ዩን ሶክ ዮል በደቡብ ኮሪያ ታሪክ የተያዙ የመጀመሪያ ፕሬዝደንት ይሆናሉ። ባለፈው ወረ የማርሻል ሕግ አውጀው ሀገሪቱን ወደ ወታደራዊ አስተዳደር ለመቀየር የሞከሩት ፕሬዝደንቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቻው ሐሳባቸውን ወዲያው እንዲተው ተገደዋል። በዚህም እሥራት፣ ከከፋ ደግሞ የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ሃያ የሚሆኑ መርማሪዎችና 80 የሚሆኑ ፖሊሶች መኖሪያ ግቢያቸው ገብተው ፕሬዝደንቱን ለመያዝ ሲሞክሩ፣ 200 የሚሆኑ ወታደሮችና ጠባቂዎቻቸው ገተዋቸዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ድርድር ተሞክሮ ሳይሳከ በመቅረቱ መርማሪዎችና ፖሊሶች ወደ መጡበት ተመልሰዋል። የመያዣ ትዕዛዙ የቀን ገደብ ሰኞ የሚያበቃ ሲሆን፣ ፕሬዝደንቱ ራሳቸውን ለመከላከል “እንደሚፋለሙ” ዝተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመያዣ ትዕዛዙ የቀን ገደብ በሚያከትምበት ሰኞ ዕለት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከሰሜን ኮሪያው አቻቸው ጋራ ለመነጋገር ሶል እንደሚገቡ ታውቋል። በደቡብ ኮሪያ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ አስተያየት ሰጥታ የማታውቀው ሰንሜን ኮሪያ፣ ዮንን ለመያዝ በሚደረግ ጥረት ምክንያት፣ ሶል የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታለች ሲሉ የሃገሪቱ የመንግሥት ብዙኅን መገናኛ አስታውቀዋል። Read more