የጂሚ ካርተ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
newsare.net
በ100 ዓመታቸው ባለፈው እሑድ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስከሬን ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ብሔራዊ ካቴድራል ዛሬየጂሚ ካርተ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
በ100 ዓመታቸው ባለፈው እሑድ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አስከሬን ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ብሔራዊ ካቴድራል ዛሬ የአሸኛኘት ሥነ ሥርዓት ተደርጎለታል። ከብሔራዊ ካቴድራሉ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት በኋላ 39ኛው ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር በትውልድ ከተማቸው ፕሌይንስ፣ ጆርጂያ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ቅጥር ጊቢ ውስጥ ባለፈው ዓመት በሞት ከተለዩትና የ77 ዓመታት የትዳር አጋራቸው ሮዘሊን ካርተር ጎን እንደሚቀበሩም ታውቋል። በብሔራዊ ካቴድራል በተደረገው ሥነ ሥርዓት የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝደንቶችና ምክትል ፕሬዝደንቶች የተገኙ ሲሆን፣ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የውዳሴ ንግግር አድርገዋል። ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሚፈጸመው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የቤተሰብ ዓባላትና ጓደኞች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ብቻ እንደሚገኙ ታውቋል። ጂሚ ካርተር ፕሌይንስ በተሰነች የጆርጂያ ከተማ በእ.አ.አ 1924 ተወለዱ። ከአሜሪካው የባሕር ኃይል ማሰልጠኛ በ1946 ተመረቁ። የአባታቸውን ሞት ተከትሎ የቤተሰቡን የግብርና ሥራ ለማስተዳደር በ1953 ወደ ትውልድ ከተማቸው ፕሌይንስ እስኪመለሱ ድረስ በባሕር ኃይሉ በሰብመሪን ኦፊሰርነት አገልግለዋል። በ1971 ብዙም ያልታወቁትና በደቡብ የሃገሪቱ ክፍል የጆርጂያ አገረ ገዥ የነበሩት ካርተር፣ በ1976 ሪፐብሊካኑን ጀራልድ ፎርድ በጠባብ ውጤት በማሸነፍ ፕሬዝደንት 39ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነዋል። ካርተር በሰብአዊ መስክ ላደረጉት አስተዋጽኦ በእ.አ.አ 2002 የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ጂሚ ካርተር ከአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ሁሉ ረጅም ዕድሜ የኖሩ ናቸው። ከባለቤታቸው ራዝሊን ጋራ የቆዩበት የትዳር ዘመንም እንደ አሜሪካ ፕሬዝደንት እና ቀዳማዊ እመቤት ረጅሙ ነው። Read more