የሶማሊያ ፕሬዝደንት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ
newsare.net
ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የቆዩት እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጋራ የተወያዩት፣ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼኽ መሐመድ በኢትዮጵያየሶማሊያ ፕሬዝደንት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ
ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የቆዩት እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጋራ የተወያዩት፣ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼኽ መሐመድ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው፣ ዛሬ እሑድ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። የፕሬዝደንቱን መመለስ ይፋ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፣ «የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻችንን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች ካደረግን በኋላ ዛሬ ከሰዓት ፕሬዝደንት ሐሰን ሼኸ መሐሙድን ሸኝቻለሁ» ሲሉ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ትላንት ቅዳሜ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ማምሻውን ሁለቱ ሀገራት በአወጡት የጋራ መግለጫ፣ መሪዎቹ በመዲናቸው ሙሉ የዲፕሎማሲያዊ ውክልና እንዲኖር በማድረግ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን «ወደነበረበት ለመመለስ እና ለማሻሻል» መስማማታቸውን አስታውቀዋል። የጋራ መግለጫው አክሎም፣ «ለቀጠናው መረጋጋት፣ በሁለቱ ሀገራት መካከለ በጋራ እምነት፣ በመተማመን እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ትብብር እንደሚያስፈልግ መሪዎቹ አረጋግጠዋል» ይላል። የሶማሊያና የኢትዮጵያ ግንኙነት የሻክረው፣ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ነጻ ሀገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋራ፣ አወዛጋቢ የባሕር በር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጥር ጥር 1 ቀን 2024 ዓ.ም ከተፈራረመች በኋላ ነው። በወቅቱ የተካሔደውን ስምምነት ተከትሎ መግለጫ ያወጣችው ሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ላይ ግልጽ ጥሰት ፈጽማለች ስትል ቁጣዋን ገልጻ ነበር። ባለፈው ዓመት ኀሙስ፣ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ሶማሊያ ኢትዮጵያን በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብነት በመውቀስ፣ በሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሐመድ ዋሬ፣ በ72 ሰዓታት ውስጥ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አስታውቃ ነበር። በተጨማሪም፣ ከፊል የራስ ገዝ ግዛት በኾነችው ፑንትላንድ እና ራሷን እንደ አገር በምትቆጥረው በተገንጣይዋ የሶማሊላንድ ግዛት ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች እንዲዘጉ ወስና ቀን ማስቀመጧን ሶማሊያ ይፋ አደረገች። በታኅሣሥ ወር በቱርክ ሸምጋይነት የተካሄደው ድርድር እና ስምምነት ግን የሁለቱን ሀገራት ውጥረት አርግቦታል። ሁለቱ ሀገራት የሶማሊያውን ፕሬዝደንት የኢትዮጵያ ጉብኝት ተከትሎ ትላንት በአወጡት የጋራ መግለጫም፣ ዐብይ እና መሐሙድ የአንካራው ስምምነትም ለማስፈፀም ቁርጠኛ መኾናቸውን ገልጸው፣ በስምምነቱ ላይ የተቀመጠውን ዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮችንም ለማፋጠን መስማማታቸው አስታውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኤርትራ፣ የግብፅ እና ሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ካይሮ ላይ የጋራ ውይይት አካሂደዋል። ውይይቱ የሦስቱ ሀገራት መሪዎች ኅዳር ወር ላይ አስመራ ላይ የሦስትዮሽ ጉባኤ ካደረጉ በኋላ የመጀመሪያው ነው። የግብጽ መንግሥት ሚዲያ አል - ሀራም የሀገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዳር አብድላቲን ጠቅሶ “በቀይ ባህር ውስጥ ምንም ዐይነት ወታደራዊ ወይም የባህር ሃይል አባል ያልሆነ ወይም የባህር ዳርቻው አካል ያልኾነ መንግሥት ተቀባይነት የለውም" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከሶማሊያ እና ከኤርትራ አቻቸው አህመድ ሞአሊም ፊቂ እና ኦስማን ሳሌህ ጋራ በመኾን መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። የሦስትዮሹ ውይይት በቀጣይ በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ላይ እንደሚካሔድ ቀኑን ሳይጠቅሱ አስታውቀዋል። Read more