በዋሽንግተኑ የአውሮፕላን አደጋ ላይ ምርመራ ቀጥሏል
newsare.net
ረቡዕ ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በረራ ላይ እያሉ በመጋጨታቸው ለ67 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑትን ሁለት አውሮፕላኖች ከወደቁበት የፖቶማክ ወንዝ ለበዋሽንግተኑ የአውሮፕላን አደጋ ላይ ምርመራ ቀጥሏል
ረቡዕ ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በረራ ላይ እያሉ በመጋጨታቸው ለ67 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑትን ሁለት አውሮፕላኖች ከወደቁበት የፖቶማክ ወንዝ ለማውጣት የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው። ከበርካታ የአሜሪካ ተቋማት የተውጣጡት መርማሪዎች፣ ከሄሊኮፕተር ጋር ተጋጭቶ ወንዙ ውስጥ በገባው የአሜሪካ አየር መንገድ ውስጥ የሚገኘውን እና «ጥቁሩ ሳጥን» በመባል የሚታወቀውን የበረራ መረጃ የሚያስቀምጥ መሳሪያ ማግኘት ችለዋል። ዋናተኞች ወደ ወንዙ ውስጥ ጠልቀው በመግባት ተጨማሪ የአውሮፕራኑን ስብርባሪ አካል ለማግኘት እንደሚሞክሩም የእሳት አደጋ መከላከያ ባለስልጣናት አመልክተዋል። የብሔራዊ ትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ የበረራ መረጃ መመዝገቢያውን ሳጥን እና በአብራሪዎቹ ክፍል ውስጥ የተቀዱ የድምፅ መረጃዎችን ከመረመረ በኃላ፣ አውሮፕላኖቹ በምን ምክንያት እንደተጋጩ ፍንጭ ሊያገኝ እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። በአሜሪካ አየር መንገድ ከተሳፈሩት መንገዶችን እና የበረራ ሰራተኞች መካከል በህይወት የተገኘ የሌለ ሲሆን በወታደራዊ ሄሎኮፍተሩ ውስጥ የነበሩት ሦስት ሰዎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን የፌደራል እና የአካባቢው ባለስልጣናት ሐሙስ እለት አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለፌደራሉ የበረራ አስተዳደር መስሪያ ቤት ምክትል አስተዳዳሪ መሾምን ያካተተ ሁለት የሥራ ማስፈፀሚያ ትዕዛዞችን ሐሙስ ከሰዓት በኃላ ፈርመዋል። ትዕዛዙን በፈረሙበት ወቅትም፣ ለደረሰው የግጭት አደጋ የብዝሃነት መርሃ ግብሩ ተጠያቂ ነው ሲሉ ያለምንም ማስረጃ ከሰዋል። ትራምፕ በፌደራል መንግስት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የተተገበሩ የብዝሃነት፣ እኩልነት እና አካታችነት ፖሊሲዎችን በመጥቀስ፣ በዲሞክራት ፕሬዝዳንቶች ባራክ ኦባማ እና የጆ ባይደን የተመሩት የቀድሞ አስተዳደሮች የትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን የቅጥር መስፈርት ዝቅ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ይህን ለማወቅ «ምክንያታዊ አስተሳሰባቸውን» መጠቀማቸውን ገልጸዋል። በሄሊኮፕተሩ ላይ የነበሩትን ሦስቱንም ወታደሮች ጨምሮ ቢያንስ 28 አስክሬኖች እስካሁን ከወንዙ ማውጣት ተችሏል። Read more