ሩቢዮ ለእስራኤል የሚደረግ የአራት ቢሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ እንዲፋጠን አደረጉ
newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ትላንት ቅዳሜ ለእስራኤል አራት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የተፋጠነ ወታደራዊ እርዳታ ለማድረስ መፈረማሩቢዮ ለእስራኤል የሚደረግ የአራት ቢሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ እንዲፋጠን አደረጉ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ትላንት ቅዳሜ ለእስራኤል አራት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የተፋጠነ ወታደራዊ እርዳታ ለማድረስ መፈረማቸውን ተናግረዋል። በዚህ ዓመት ጥር ወር ላይ ሥራውን የጀመረው የትራምፕ አስተዳደር እስካሁን ድረስ 12 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ወታደራዊ ሽያጭ፤ ለእስራኤል መፍቀዱን ሩቢዮ በመግለጫቸው አስታውቀዋል። መግለጫው አያይዞም “አሜሪካ ለእስራኤል ደህንነት ያላትን የረዥም ጊዜ ቃልኪዳን ለሟሟላት፤ ስጋቶችን ለመከላከል የሚያስችል ዘዴን ጨምሮ ሁሉንም ያሏትን አማራጮች መጠቀሟን ይቀጥላል” ብሏል። ሩቢዮ ለእስራኤል ወታደራዊ ዕርዳታ ለማድረስ የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣናቸውን መጠቀማቸውን ገልጸዋል። በአሁን ሰዓት እስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪ ተብሎ የተመዘገበው ሀማስ ድርጅት ጋር በቋፍ ላይ ያለ የተኩስ አቁም ውስጥ ይገኛሉ። Read more