የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዩን ከእስር ተለቀቁ
newsare.net
የደቡብ ኮሪያ ፍርድቤት በክስ ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የእስር ማዘዣ እንዲሰረዝ መወሰኑን ተከትሎ አቃቢ ህግ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ላለመጠየቅ በየደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዩን ከእስር ተለቀቁ
የደቡብ ኮሪያ ፍርድቤት በክስ ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል የእስር ማዘዣ እንዲሰረዝ መወሰኑን ተከትሎ አቃቢ ህግ በውሳኔው ላይ ይግባኝ ላለመጠየቅ በመወሰኑ ዛሬ በሴኡል ከሚገኘው እስርቤት ተለቀዋል፡፡ ዮን በእአአ ታህሳስ 3 ቀን ባሳለፉትና ለአጭር ጊዜ በቆየው የማርሻል ህግ ምክንያት ከስራቸው እንደታገዱ የሚቆዩ ሲሆን በአመፅ የቀረበባቸው ክስም እንዳለ ይቆያል ተብሏል፡፡ የወንጀል ጉዳዩ በስልጣን ላይ በሚኖራቸው ቆይታ ዙርያ ክሚታየው የፍርድ ሂደት የተለየ ሲሆን በህገ-መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ወደ ሥራ ይመለሱ ወይም ከሥልጣናቸው ይነሱ በሚለው ጉዳይ ላይ በሚቀጥሉት ቀናት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል። Read more