newsare.net
ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ያለው የዕርዳታ አቅርቦት ከሚያስፈልገው አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ሞትና ረሃብ እየተስፋፋ እንደሚገኝ የየእርዳታ አቅርቦት በትግራይ
ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ያለው የዕርዳታ አቅርቦት ከሚያስፈልገው አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ሞትና ረሃብ እየተስፋፋ እንደሚገኝ የትግራይ ክልል የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ በቅርቡ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ በበኩላቸው በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት የሚደረግ የእርዳታ አቅርቦት እየቀጠለ መሆኑን ገልፀው የፌዴራሉ መንግሥት የትግራይ ሕዝብ የእርዳታ እህል እንዲደርሰው የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው ብለዋል። ወደ ትግራይ ክልል የገባውን እና እየገባ ያለውን የእርዳታ አቅርቦት በተመለከተ የትግራይ ክልል የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊዎችን አነጋግረናል። (የሁለቱንም ኃላፊዎች ምላሽ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ) Read more