newsare.net
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት(USAID) በዓለም የምግብ ፕሮግራም(WFP) አማካይነት በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል የሚያሰራጨው የርዳበኢትዮጵያ የርዳታ እህል ምዝበራ እስከ አሁን ባሉ መረጃዎች የሚታወቀው
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት(USAID) በዓለም የምግብ ፕሮግራም(WFP) አማካይነት በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል የሚያሰራጨው የርዳታ እህል፣ በተገቢው መንገድ “ለተረጂው ባለመድረሱ”፣ የርዳታ ዕደላው እንዲቋረጥ ማድረጉን፣ በግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. አስታውቆ ነበር። ይኸው የርዳታ እህል ምዝበራ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ «ግዙፉ» እንደኾነ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅቱ አመልክቷል። ምንም እንኳን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቱ፣ በኢትዮጵያ ያቋረጠው የምግብ ርዳታ በድጋሚ እንዲሰጥ ቢፈቅድም፤ በአገሪቱ የርዳታ እህል ምዝበራ የረጅም ዓመታት ዕድሜ እንዳለው አውስቷል። የዓለም የምግብ መርሐ ግብር(WFP) እና የዩናይትድ ስቴትሱ ዓለም አቀፍ የልማት ተራዶኦ (USAID)፣ ከዚኽ ምዝበራ ጀርባ ማን እንዳለ ምርመራ እያደረጉ መኾናቸውን ቢያስታውቁም፣ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት መሻከሩ ተጠቁሟል። ሮይተርስ የዜና ወኪል፣ በትግራይ ክልል ተዘዋውሮ፣ የርዳታ እህሉ በማን እንደተዘረፈ እስከ አሁን ድረስ የታወቁት መረጃዎች ምን እንደሚመስሉ፣ የሁለቱን ዓለም አቀፍ ተቋማት ባልደረቦች እና በክልሉ ያሉ ባለድርሻ አካላትን አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more