newsare.net
ሩስያ ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት በዩክሬን ዲኒፕሮ ከተማ አንድ ህፃን ጨምሮ ሶስት ሰዎችን ሲገደሉ በኪየቭ እና አካባቢው ላይ በደረሰው ጥቃት ደግሞ ታዳጊን ጨሩስያ በማዕከላዊ ዩክሬን ባደረሰችው ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ
ሩስያ ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት በዩክሬን ዲኒፕሮ ከተማ አንድ ህፃን ጨምሮ ሶስት ሰዎችን ሲገደሉ በኪየቭ እና አካባቢው ላይ በደረሰው ጥቃት ደግሞ ታዳጊን ጨምሮ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናቱ ዛሬ አስታውቀዋል፡፡ የማዕከላዊ ዲኒፕሮ ፔትሮቭስክ ክልል ገዥ ሰርጊ ሊሳክ እንዳሉት በዲኒፕሮ ላይ በአንድ ሌሊት በደረሰ ጥቃት 19 ሰዎች ጉዳት የደርሰባቸው ሲሆን በርካታ ሕንፃዎች ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡ ባለ ሁለት ፎቅ የመኖሪያ ሕንፃ መውደሙንም ገልጸዋል፡፡ በሩሲያ ወረራ ኪየቭን ጨምሮ የዩክሬን ከተሞች የሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የሚሳኤል ጥቃቶች በተደጋጋሚ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ሞስኮ በኤሌክትሪክ ሃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እየፈፀመች ባለችበት በአሁኑ ወቅት ኪየቭ ገና ከባዱ ክረምት ከመግባቱ በፊት ከአጋሮቿ ተጨማሪ የአየር መከላከያ እንዲላክላት እየጠየቀች ነው፡፡ Read more