newsare.net
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከዋና ከተማይቱ ካርቱም በስተደቡብ በአል-ጃዚራ ግዛት ውስጥ ባሉ መንደሮች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 50 ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ መቁበሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር 50 ሰዎች ተገድለዋል ከ200 በላይ ቆስለዋል ተባለ
የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከዋና ከተማይቱ ካርቱም በስተደቡብ በአል-ጃዚራ ግዛት ውስጥ ባሉ መንደሮች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 50 ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ መቁሰላቸውን የመብት ተሟጋቾች ተናገሩ፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው በግዛቲቱ የነበሩ አንድ ወታደራዊ አዛዥና የተወሰኑ ወታደሮቻቸው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ከድተው የሱዳን ሠራዊትን መቀላቀላቸው ከተነገረ በኋላ መሆኑን ተሟጋቾቹ ገልጸዋል፡፡ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ “የአል ሳሪሃ እና አዝራቅ መንደሮች ጥቃት ደርሶባቸዋል” ሲሉ በሱዳን የረድኤት ሥራዎችን የሚያስተባበሩ የበጎ ፈቃድ ቡድኖች ለኤኤፍፒ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ አካባቢው በከባድ መሣሪያ ድብደባ ሥር የሚገኝና የግንኙነት መስመሮችም የተቋረረጡ በመሆናቸው ቁስለኞችን ለማውጣት አስቸጋሪ መሆኑን መግለጫቸው አመልክቷል፡፡ ከትላንት በስቲያ ዓርብ የሱዳን የዶክተሮች ህብረት “በፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች ለዘር ማጥፋት አደጋ ተጋልጣዋል” የተባሉትን ንጽሃን ዜጎች ከተከበበው አካባቢ እንዲወጡ የሰብአዊ ኮሪደር እንዲያስከፍት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ተማጽኗል፡፡ “የሱዳን ሠራዊት ሰላማዊ ዜጎችን የመከላከል ብቃት የሌለው በመሆኑ” የነፍስ አድን ሥራው የማይቻል ሆኗል ሲል የዶክተሮቹ ህብረት አክሏል፡፡ በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደሉ ሲነገር፣ አንዳንዶቹ የሟቾቹን ቁጥር እስከ 150, 000 እንደሚያደርሷቸው ዘገባው አመልክቷል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከ7ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ መሆናቸውን በመግለጽ “በዓለም ትልቁ የተፈናቃዮች ቀውስ” ሲል ጠርቶታል፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ቀውሱ ለሱዳን አጎራባች ሀገራት የሚተርፍ መሆኑን አመልክቷል፡፡ አካባቢዎቹን ለኢኮኖሚ ችግር፣ የጸጥታ ጉዳዮች እና ከተፈናቃዮች ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ሌሎች ፈተናዎች እንደሚጋልጣቸው በማስጠንቀቅ “የግጭቱ ቀጣናዊ ተጽእኖ እጅግ ከባድ ነው” ብሏል፡፡ Read more