newsare.net
በምስራቅ ሊባኖስ ቤካ ሸለቆ አቅራቢያ በሚገኙ የሂዝቦላ ዒላማዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ ያስጠነቀቀችው እስራኤል፣ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀውእስራኤል የምስራቅ ሊባኖስ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አዘዘች
በምስራቅ ሊባኖስ ቤካ ሸለቆ አቅራቢያ በሚገኙ የሂዝቦላ ዒላማዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ ያስጠነቀቀችው እስራኤል፣ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ ባስተላለፉት መልዕክት በአልቤክ፣ አይን ቦርዴይ እና ዶውሪስ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው መውጣት አለባቸው ብለዋል። የእስራኤል ባለሥልጣናት የሚያስተላልፏቸው ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያዎችን ተከትሎ እስራኤል የአየር ድብደባዎችን የምታካሂድ ሲሆን፣ የጥቃቱ ዓላማ ሂዝቦላህን ከእስራኤልና ሊባኖስ ድንበር ለመግፋት መሆኑን ባለስልጣናቱ ይገልጻሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ፣ እስራኤል የፍልስጤም ስደተኞችን የሚደግፈውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለማገድ ባወጣችው አዲስ ሕግ ዙሪያ ስጋታቸውን ገልጸው ለእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ደብዳቤ ጽፈዋል። የደብዳቤውን ይዘት አስመልክተው የመንግስታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ «ሕጉ ተግባራዊ ከሆነ በከበባ ስር በሚገኘው ግዛት የሚኖሩት ፍልስጤማውያን ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ግልፅ ነው» ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ማክሰኞ እለት በሰሜናዊ ጋዛ በሚገኝ ባለአምስት ፎቅ የመኖሪያ ህንፃ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 70 ሰዎች መሞታቸውን የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል። Read more