newsare.net
ዙሃይ በተባለች የደቡባዊ ቻይና ከተማ አንድ የመኪና አሽከርካሪ በስፖርት ማዕከል ስፖርት ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች መሃል መኪናውን እየነዳ ገብቶ 35 ሰዎችን ሲገድልቻይና ውስጥ የመኪና አሽከርካሪ 35 ሰዎች ገጭቶ ገደለ
ዙሃይ በተባለች የደቡባዊ ቻይና ከተማ አንድ የመኪና አሽከርካሪ በስፖርት ማዕከል ስፖርት ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች መሃል መኪናውን እየነዳ ገብቶ 35 ሰዎችን ሲገድል ሌሎች 43 ሰዎች ማቁሰሉን ፖሊስ አስታወቀ። የስድሳ ሁለት ዓመቱ የመኪናው አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ ትላንት ሰኞ ማታ አስታውቋል። ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ጥቃት ወይም አደጋ ይሁን ለጊዜው አለመታወቁን ፖሊስ አመልክቷል። ድርጊቱ የተፈጸመው ከተማዋ በየዓመቱ የቻይና ህዝባዊ ነጻ አውጪ ሠራዊት የአቪየሽን ትርዒት የምታስተናግድ ስትሆን ትርዒቱ ዛሬ ማክሰኞ ተከፍቷል። Read more