newsare.net
የምግብና ሌሎችንም ዕርዳታዎችን ለማድረስ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የቻድ ድንበር መሻገሪያን ክፍት ማድረጉን እንደሚቀጥል የሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት ዛሬ አስታውየሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት የቻድ ድንበር መሻገሪያ ክፍት መሆኑ እንደሚቀጥል አስታወቀ
የምግብና ሌሎችንም ዕርዳታዎችን ለማድረስ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የቻድ ድንበር መሻገሪያን ክፍት ማድረጉን እንደሚቀጥል የሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት ዛሬ አስታውቋል። አድሬ በሚል የሚታወቀው የድንበር መተላለፊያ በዳርፉር እና ኮርዶፋን ለሚገኙና ለረሃብ ለተጋለጡ ሰዎች ዕርዳታ ለማድረስ አስፈላጊ መሆኑን የረድኤት ድርጅቶች ይገልጻሉ። የመንግስት አካላት በበኩላቸው ድንበሩን ከፍቶ ማቆየት ለፍጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሣሪያ ማስተላለፊያነት እንዲያገለግል ያደርጋል በሚል ተቃውመውታል። በሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለቸነፈር የተጋለጡ መሆናቸውን እንዲሁም በዳርፉር በሚገኝ አንድ መጠለያ ረሃብ መግባቱን ባለሙያዎች አስታውቀዋል። በሱዳን ሁለቱ ተፋላሚ ጀኔራሎች “ወሳኝ” ብለው የሚገልጹትን ወታደራዊ ድል በመሻታቸው፣ ፖለቲካዊ መፍትሄ የመገኘቱን ዕድል አጥብቦታል። ጦርነቱ ከፈነዳበት ሚያዚያ 2016 ወዲህ 11 ሚሊዮን ሠዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዓለም አስከፊው መፈናቀል ሲል ገልጾታል። Read more