newsare.net
በቅርቡ ስልጣን የሚረከቡት ዶናልድ ትራምፕ አዲሱን አስተዳደራቸውን እያዋቀሩ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ፣ የነዳጅ መስክ አገልግሎት ድርጅት መስራች የሆኑትትራምፕ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ሥራ አስፈፃሚን ለኃይል መስሪያ ቤቱ ጸሐፊነት መረጡ
በቅርቡ ስልጣን የሚረከቡት ዶናልድ ትራምፕ አዲሱን አስተዳደራቸውን እያዋቀሩ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ፣ የነዳጅ መስክ አገልግሎት ድርጅት መስራች የሆኑት ክሪስ ራይትን የ ዩናእትድ ስቴትስን የኃይል መስሪያቤት እንዲመሩ መርጠዋል። የሽግግር ቡድኑ የፕሬዚደንቱን ምርጫ ቅዳሜ ከሰዓት በኃላ ይፋ አድርጓል ። አርብ እለት ትራምፕ ፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ መስሪያቤትን እንዲመሩ በመረጧቸው የቀድሞው የሰሜን ዳኮታ ግዛት አስተዳዳሪ ዳግ በርገም የሚመራ አዲስ ብሔራዊ የኃይል ምክር ቤት ይፋ አድርገዋል። በአዲሱ ኃላፊነታቸው መሰረት በርገም በኃይል ማመንጨት ፍቃድ ፣ምርት ፣ ስርጭት ፣ቁጥጥር እና ማጓጓዝ ላይ የሚሳተፉትን ሁሉንም አስፈፃሚ ቅርንጫፍ ተቋማት የሚያካልል ቡድንን እንደሚመሩ ትራምፕ በመግለጫቸው አስታውቀዋል ። የብሔራዊ ኃይል ምክር ቤት ሊቀመንበር እንደመሆናቸው ፣ በርገም በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱም መቀመጫ እንደሚኖራቸው ተመራጩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል። ራይት ፣ ኮሎራዶ ላይ መሰረት ያደረገው ፣ ሊበርቲ ኢነርጂ የተሰኘ ኩባንያ ዋና ኃላፊ ቢሆኑም ፣ የፖለቲካ ልምድ ግን የላቸውም ። ነዳጅ ማመንጨትን ጨምሮ ለነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ኢንዱስትሪ ተሟጋች በመሆናቸውም ይታወቃሉ። በአውሮፓዊያኑ 2019 ፣ አደገኛ አለመሆኑን ለማሳየት ፈሳሽ ነዳጅ እስከመጠጣት ደርሰዋል ። በመጋቢት 2024 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ይፋ የተደረገው የአሜሪካ ኃይል መረጃ አስተዳደር ሪፖርት እንደሚያሳየው ፣ ሀገሪቱ ላለፉት ስድስት ተከታታይ ዓመታት በማንኛውም ጊዜ ከማንኛውም ሀገር የበለጠ ድፍድፍ ዘይት አምርታለች። ወርሃዊ የአሜሪካ ድፍድፍ ዘይት ምርት መጠን በአውሮፓዊያኑ ታህሳስ 2023 ከ13.3 ሚሊዮን በርሜል የደረሰ ሲሆን ፣ ይህም በወረሃዊው የምርት መጠን ልኬት ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል(AP)። Read more