newsare.net
የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደአ መከላከያ ምስክሮች የመጥሪያ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደየአቶ ታዬ ደንደአን ተጨማሪ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ
የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደአ መከላከያ ምስክሮች የመጥሪያ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግሥት ሥርዓት ችሎት፣ የተከሳሹን ቀሪ የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። “የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ ኾነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ኀይሎች ጋራ በመተሳሰር ለጥፋት ተልእኮ በኅቡእ ተንቀሳቅሰዋል፤” በሚል ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ታዬ ደንዳአ ቀሪ ምስክሮቻቸውን እንዲያቀርቡ መጥሪያ ለመጻፍ፣ ለዛሬ ኅዳር 17፣ 2017 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቶ የነበረ ሲኾን፣ ፍርድ ቤቱ ለምስክሮቹ መጥሪያ እንዲጻፍ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተከሳሹ ከዚህ ቀደም የምስክሮቻቸው ማንነት በይፋ እንዳይገለጽ በጠየቁት መሰረት መጥሪያ እንዲጻፍ ትዕዛዝ የተሰጠው ለማን እንደኾነ በፍርድ ቤቱ በይፋ አልተገለጸም። አቶ ታዬ ጠበቃ የማግኘት መብት መነፈጋቸውን ጨምሮ በእስር ቤት እንደተፈጸመባቸው የገለጹት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አጣርቶ ለፍርድ ቤት እንዲያቀርብ ጥቅምት ስምንት ትዕዛዝ ተሰጥቶት ነበር። በሌላ በኩል በዛሬው ችሎትም ያለጠበቃ የቀረቡት አቶ ታዬ፣ ከዚህ ቀደም አቅርበዋቸው የነበሩትን ዐቃቤ ሕግ ክስ ሳይ መሰርትባቸው ለወራት እንዳቆያቸዉ፣ ቤተሰባቸዉ ላይ እንግልቶች መድረሱንና፣ የጥብቅና አገልግሎት ሊሰጧቸው የነበሩ ጠበቆችን የሀገሪቱ ደህንነት መሥሪያ ቤት በማስፈራራት የሕግ ድጋፍ እንዳያገኙ መከልከላቸውን በተመለከተ ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸው በድጋሚ አቤቱታ አቅርበዋል። ለተከሳሹ አቤቱታ ምላሽ የሰጡት የፍርድ ቤቱ የመሐል ዳኛም ‘ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ይህን ጉዳይ እንዲያጣራ ትእዛዝ ማስተላለፉን ገልፀዉ፣ ኮሚሽኑም ይህንኑ የማጣራት ሥራውን በ30 ቀን ጨርሶ እንደሚያቀርብ ምላሽ መስጠቱን" አስታውሰዋል። ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more