newsare.net
በኢራን የሚደገፉት የኢራቅ ታጣቂዎች የሶሪያ መንግሥት ትልቋን የአሌፖ ከተማ በያዙት ታጣቂዎች ድንገተኛ ግሥጋሤ ላይ የሚያካሂደውን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ለየኢራቅ ሚሊሻዎች መንግሥት በአማፂያን ላይ የሚያካሂደውን አጸፋዊ ጥቃት ለመደገፍ በሶሪያ ተሰማርተዋል
በኢራን የሚደገፉት የኢራቅ ታጣቂዎች የሶሪያ መንግሥት ትልቋን የአሌፖ ከተማ በያዙት ታጣቂዎች ድንገተኛ ግሥጋሤ ላይ የሚያካሂደውን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ለመደገፍ ወደሶሪያ ዘምተዋል ሲሉ አንድ የታጣቂዎቹ ባለስልጣን እና የሶሪያ የጦርነት ተከታታይ አካል አመልክተዋል፡፡ በጂሃዳዊው ሃያት ታህሪር አልሻም ቡድን የሚመሩት ሰርጎ ገቦቹ ባለፈው ሳምንት አሌፖ ላይ ከሁለት አቅጣጫ ጥቃት አድርሰው ወደ ገጠራማዎቹ ኢድሊብ እና ሃማ ግዛቶች ተሻግረዋል፡፡ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አርጋቺ ከሶሪያው ፕሬዘዳንት በሽር አሳድ ጋር ትላንት እሁድ ደማስቆ ላይ የተገናኙ ሲሆን፤ ቴህራን ለሶሪያ መንግሥት ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ትላንቱኑ በመቀጠል ከአማጺያኑ ዋና ደጋፊ ጋር ለመወያየት ወደ ቱርክ አንካራ ተጉዘዋል፡፡ መቀመጫውን በብሪታንያ ያደረገው የተቃዋሚዎች የሶሪያ የሰብዓዊ መብት ተከታታይ ቡድን ወደ 200 የሚጠጉ ኢራቃውያን ታጣቂዎች በአነስተኛ የጭነት መኪናዎች ወደ ሶሪያ ማቅናታቸውን አስታውቋል። የሶሪያ ጦር የአማጺያኑን ጥቃት በመመከት በሚያካሂደው ውጊያ ለማገዝ አሌፖ ላይ ይሰፍራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አክሎ አስታውቋል፡፡ Read more