newsare.net
ዛሬ ቅዳሜ በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋም በፌስቡክ ገጹ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ኀዳር 28/2017 አስታውቋበመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተቋረጠ
ዛሬ ቅዳሜ በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋም በፌስቡክ ገጹ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ኀዳር 28/2017 አስታውቋል። አገልግሎቱ ለኤሌክትሪክ መቋረጡ ምክንያት የሲስተም ችግር መሆኑንም ባሰፈረው አጭር መግለጫ ጠቁሟል። «የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው።» በማለት ዜጎች በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳሰቧል። ስለጉዳዩ የአሜሪካ ድምጽ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እየሞከረ ነው። Read more