newsare.net
በጋና በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የገዥው 'ኒው ፓትሪዎቲክ ፓርቲ' የወከሉት ምክትል ፕሬዘዳንት ማሃማዱ ባዉሚያ ተሸንፈዋል፡፡ በሃገሪቱ የተንሰራፋው ኢኮየጋና ገዥ ፓርቲ እጩ በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው ተሸነፉ
በጋና በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የገዥው 'ኒው ፓትሪዎቲክ ፓርቲ' የወከሉት ምክትል ፕሬዘዳንት ማሃማዱ ባዉሚያ ተሸንፈዋል፡፡ በሃገሪቱ የተንሰራፋው ኢኮኖሚያዊ ችግርን ተከትሎ መራጮች ላይ የነበረው ስጋት ለሽንፈታቸው ምክንያት ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ትላንት የተካሄደው ምርጫ ሽንፈት ተከትሎ ለሁለት የምርጫ ጊዜ በፕሬዘዳንት ናና አኮ ፋዶ አማካኝነት ሃገሪቱን የመራትና በዋጋ ንረት እና እዳን በጊዜው ያለመክፈል የከፋ ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ ሃገሪቱን ከቷታል በሚል የሚወቀሰው የገዥው ፓርቲ የስልጣን ጊዜ የሚያበቃ ይሆናል፡፡ ባውሚያ “የጋና ህዝብ ተናግሯል፣ ህዝቡ በዚህ ጊዜ ለለውጥ ድምጽ ሰጥቷል እናም በትህትና እናከብራለን« ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡ ምርጫውን ላሸነፉት የተቃዋሚው ‘ናሽናል ዲሞክራቲክ ኮንግረስ’ እጩ እና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማን ደውለው እንኳን ደስ ያለዎት ማለታቸውንም ተናግረዋል፡፡ ተመራጩ ማሃማም የስልክ ጥሪው እንደደረሳቸው በX የማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ አረጋግጠዋል፡፡ የማሃማ ደጋፊዎች አክራ ከሚገኘው የፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ ዋና መሥሪያ ቤት ውጭ ተሰብስበው ደስታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ ማሃማ የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ »ወሳኝ" በሆነ ሁኔታ ማሸነፋቸውንና ፓርቲያቸውም በሃገሪቱ ፓርላማ ምርጫ ማሸነፉንም ምክትል ፕሬዘዳንቱ ባውሚያ ተናግረዋል፡፡ በዲሞክራሲያዊ መረጋጋት ታሪክ ባላት ጋና ሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲዎች 'ኒው ፓትሪዎቲክ ፓርቲ' እና ‘ናሽናል ዲሞክራቲክ ኮንግረስ’ ሃገሪቱ ወደ መድበለ ፓርቲ ፖለቲካ ከተመለሰች እኤአ በ1992 በኋላ እየተፈራረቁ መርተዋል፡፡ Read more