newsare.net
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ፣ «ፈረስ ቤት» በተባለች ከተማ ኅዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም የፋኖ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት 37 ሲቪሎች መገበደጋ ዳሞት ወረዳ ከ30 በላይ ሲቪሎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአማራ ክልል መንግሥትና ነዋሪዎች ተናገሩ
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ፣ «ፈረስ ቤት» በተባለች ከተማ ኅዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም የፋኖ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት 37 ሲቪሎች መገደላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። በሌላ በኩል የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የሟች ቤተሰቦችና የከተማው ነዋሪዎች፣ የወረዳውን አስተዳዳሪ ጨምሮ ከ30 በላይ የወረዳው አመራሮች በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ ባሏቸው የፋኖ ታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ ሰዎቹ የተገደሉት ሐሙስ ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ነው ብለዋል። ላለፉት ሁለት ወራት በፋኖ ቁጥጥር ሥር እንደነበሩ አንድ ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈልጉ የመንግሥት አንድ ግለሰብ ፣ ግድያው ሲፈጸም በቦታው ነበርኩ ብለዋል። አንድ ሌላ ግለሰብ ደግሞ፣ የቅርብ ቤተሰባቸው አባል እንደተገደለባቸው ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ከፋኖ ታጣቂዎች መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ከፌደራልና ከክልል ባለሥልጣናትም መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more