newsare.net
በጋና ምርጫ የቀድሞው ፕሬዚደንት ጆን ድራሃሚ ማሃማ አሸነፉ፡፡ የገዢው ፓርቲ ዕጩ ተፎካካሪ የሆኑት ምክትል ፕሬዚደንቱም መሸነፋቸውን ተቀብለዋል፡፡ ናሚቢሰሞነኞቹ የጋና እና የናሚቢያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫዎች
በጋና ምርጫ የቀድሞው ፕሬዚደንት ጆን ድራሃሚ ማሃማ አሸነፉ፡፡ የገዢው ፓርቲ ዕጩ ተፎካካሪ የሆኑት ምክትል ፕሬዚደንቱም መሸነፋቸውን ተቀብለዋል፡፡ ናሚቢያ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዚደንት መርጣለች፡፡ ሰሜኑን እና ደቡቡን የሀገሪቱን ክፍል የሚለየውን የቅኝ አገዛዝ ዘመን አጥር ለማስወገድ እንደሚሰሩ አዲስ ተመራጯ ፕሬዚደንት ኔቱምቦ ናንዲ ኢንዳይትዋህ ቃል ገብተዋል፡፡ «Red Line» ወይም ቀዩ መስመር ተብሎ የሚጠራው 1000 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ እርዝማኔ ያለው አጥር የታጠረው ከሰሜኑ የናሚቢያ ክፍል ወደ ደቡቡ የግብርና ውጤቶች በተለይ የቀንድ ከብቶች እና ሥጋ እንዳይገባ ለመቆጣጠር መሆኑን ከዋና ከተማዋ ክዊንድሆክ በቪታሊዮ አንጉላ ያጠናቀረው ዘገባ ያወሳል፡፡ በሳምንታዊው አፍሪካ ነክ ርዕሶች ፕሮግራም ተካትተዋል፡፡ Read more