newsare.net
ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ታግደው የነበሩ፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች ዛሬ እግዳቸው ተነስቷል። በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበበሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ
ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ታግደው የነበሩ፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች ዛሬ እግዳቸው ተነስቷል። በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በኅዳር ወር ውስጥ በቀናት ልዩነት እግድ ተጥሎባቸው የነበሩት፣ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባሉ ድርጅቶች ናቸው፡፡ ለእግዱ ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው ደግሞ፣ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል፣ እንዲሁም የአገርንና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር አከናውነዋል የሚል ነበር፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ እግድ በተጣለባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ “በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ” እንደሚሰጥ ኅዳር 19 መግለጫ በሰጡበት ወቅት ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ታኅሣሥ 2 እግዱ መነሳቱ ታውቋል፡፡ ታግደው ከነበሩት ድርጅቶች አንዱ የኾነው የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ አምሃ መኮንን፣ እግዱ መነሳቱን የሚገልጽ ደብዳቤ ከማስጠንቀቂያ ጋራ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more