newsare.net
የሞልዶቫ ፓርላማ ሩሲያ በያዝነው የክረምት ወር የአውሮፓ ኅብረት እጩ ወደሆነችው ሀገር ትልክ የነበረውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ልታቋርጥ ትችላለች በሚል ሥጋየሩሲያ የጋዝ አቅርቦት ይቋረጣል በሚል ሥጋት ውስጥ የገባችው ሞልዶቫ የአስቸኳይ ጊዜ ዐወጀች
የሞልዶቫ ፓርላማ ሩሲያ በያዝነው የክረምት ወር የአውሮፓ ኅብረት እጩ ወደሆነችው ሀገር ትልክ የነበረውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ልታቋርጥ ትችላለች በሚል ሥጋት በኃይል አቅርቦቱ ዘርፍ ተፈጻሚ የሚኾን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አጽድቋል። 101 መቀመጫዎች ያሉት የሞልዶቫ ምክር ቤት ከመጭው ሰኞ አንስቶ የሚጀምር እና ለ60 ቀናት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ለማጽደቅ ድምጽ ሰጥቷል። በዐዋጁም መሠረት ሞስኮ ለትልቁ የሞልዶቫ የጋዝ ማመንጫ ‘ኩሲዩርጋን’ የምታቀርበውን የጋዝ አቅርቦት የምታቋርጥ ከኾነ “አይቀሬ ፈተና” ይደቅናል ያሉትን ሁኔታ ይመራል። የኩሲዩርጋን የኃይል ማመንጫ በሩሲያ ዘመሙ የትራኒስትሪያ ግዛት ይገኛል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 መገባደጃ ሩሲያ ከሞልዶቫ በምትዋሰነው ዩክሬን የከፈተችውን ጥቃት ተከትሎ የኩሲዩርጋን የኃይል ማመንጫ ሥራ ተቋርጦ ነበር። Read more