newsare.net
እስራኤል በፍልስጤም ግዛት በሀማስ ታጣቂዎች ላይ ባካሄደችው ጥቃት ከ45 ሺሕ በላይ ሰዎችን ገድላለች ሲል የጋዛ ጤና ሚንስቴር ዛሬ ሰኞ በአወጣው መግለጫ አስታወበጋዛ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ45 ሺሕ ማለፉን የሀገሩ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
እስራኤል በፍልስጤም ግዛት በሀማስ ታጣቂዎች ላይ ባካሄደችው ጥቃት ከ45 ሺሕ በላይ ሰዎችን ገድላለች ሲል የጋዛ ጤና ሚንስቴር ዛሬ ሰኞ በአወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ በግጭቱ ወደ 107 ሺሕ የሚጠጉ ሰዎች መቁሰላቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል። አሃዙ ሲቪሎችና እና ተዋጊዎችን ለይቶ አላስቀመጠም። ነገር ግን ቀደም ሲል ሚንስቴሩ በአወጣቸው መግለጫዎች ከተገደሉት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚኾኑት ሴቶች እና ህጻናት መኾናቸውን አስታውቋል፡፡ የጋዛ ጤና ሚንስቴር በዕለታዊ መግለጫው ባለፉት ቀናት 52 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። የጋዛ የሲቪል መከላከያ እና የሆስፒታል ባለሥልጣናት የትላንቱ ደም አፋሳሽ ጥቃት በሰሜናዊ ጋዛ ከተማ እና በደቡባዊ ጋዛ ካን ዮኒስ እንዲሁም በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው የኑሴራት የስደተኞች ካምፕ የደረሱትን ጥቃቶች እንደሚያካትት አመልክተዋል፡፡ የእስራኤል የጦር ኃይል ትላንት እሁድ በኑሴራት የሀማስን የዕዝ እና ቁጥጥር ማዕከል መምታቱን ተናግሯል። እስራኤል “የሀማስ ታጣቂዎች ፍልስጤማዊያን ሲቪሎች ባሉባቸው አካባቢዎች ይንቀሳቀሳሉ” በማለት በተደጋጋሚ የምትወነጅል ሲሆን ፍልስጤማውያን እና የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸው “የእስራኤል ጦር የሲቪሎችን ሞት ለመከላከል በቂ ሥራ እየሠራ አይደለም” በማለት ይከሳሉ። Read more