newsare.net
በሞዛምቢክ በተከሰተው ከፍተኛ አውሎ ነፋስና ዝናብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 45 ማሻቀቡ ተነግሯል። ባለፈው እሑድ የሰሜን ሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ ክፍለ ግዛትን በበሞዛምቢክ አውሎ ነፋስ የሞቱት ቁጥር ወደ 45 አሻቀበ
በሞዛምቢክ በተከሰተው ከፍተኛ አውሎ ነፋስና ዝናብ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 45 ማሻቀቡ ተነግሯል። ባለፈው እሑድ የሰሜን ሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ ክፍለ ግዛትን በመታው አውሎ ነፋስ እና ዝናም ሠላሳ አራት ሰዎች መሞታቸውን ትላንት ማክሰኞ የወጣው የመጀመሪያው አሃዝ አሳይቶ ነበር፡፡ በአውሎ ነፋሱ 500 የሚኾኑ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ አደጋ መከላከል ባለሥልጣን አስታውቋል። 36 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች መሉ በሙሉ አሊያም በከፊል ፈርሰዋል። 181 ሺሕ ሰዎች በከፍተኛው አውሎ ነፋሱ ተጠቂ ኾነዋል። የአደጋ መከላከል ማዕከሉ በአወጣው በኋለኛው አሃዝ መሠረት ካቦ ዴልጋዶ ውስጥ 38 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ናምፑላ ክፍለ ሀገር ውስጥ ደግሞ አራት ሰዎች ሞተዋል፡፡ ወደ መሃል ሀገር ገባ ብላ በትምገኘው ኒያሳ ውስጥ ደግሞ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡ የደረሰበት ያልታወቀ አንድ ሰው መኖሩንም መረጃው አመልክቷል፡፡ በሰዓት 260 ኪ.ሜ. ፍጥነት የነበረው ነፋስና ከፍተኛ ዝናም ቀድሞውንም ግጭትና ደካማ መሠረተ ልማት የነበረውን የሞዛምቢክን ሰሜናዊ ክፍል አጥቅቷል። አውሎ ነፋሱ በሕንድ ውቅያኖስ የምትገኘውን የፈረንሣይ ደሴት ማዮትን ከመታ በኋላ ነበር ወደ ሞዛምቢክ ያቀናው። በማዮት ቢያንስ በመቶ ወይም በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሳይገድል እንዳልቀረ ተሰግቷል። Read more