newsare.net
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል ተባብሶ በቀጠለው ግጭትና የተኩስ ልበወራ ጃርሶ ወረዳ ቡና ለመጠጣት የተሰባሰቡ ሰዎች በፍንዳታ መጎዳታቸውን ቤተሰቦች ገለጹ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል ተባብሶ በቀጠለው ግጭትና የተኩስ ልውውጥ ምክኒያት፣ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን የተጎጂ ቤተሰብ እና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። የተጎጂ ቤተሰብ አባል መኾናቸውን የገለጹ ግለሰብ ፣ ከቤታቸው ደጃፋ በሚገኝ ዛፍ ጥላ ስር ኾነው ቡና በመጠጣት ላይ የነበሩ ሰዎች እና ሕፃናት ጭምር ከርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ፍንጣሪ መገደላቸውን ተናግረዋል። በወረዳው ደረሰ በተባለው ጉዳት ዙሪያ ከክልሉ ባለሥልጣናት ጀምሮ እስከ ወረዳው ድረስ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ለማነጋገር የአሜሪካ ድምፅ ያደረገው ጥረት ባለ ሥልጣናቱ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምክንያት ሊሳካ አልቻለም። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። Read more