newsare.net
በሰባት የአማዞን መጋዘኖች የሚገኙ ሠራተኞች ከዛሬ ሐሙስ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መትተዋል። ሠራተኞቹ አድማውን የጠሩት አማዞን ባለፈው እሑድ ቀጠሮ ተይዞለየአማዞን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ
በሰባት የአማዞን መጋዘኖች የሚገኙ ሠራተኞች ከዛሬ ሐሙስ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መትተዋል። ሠራተኞቹ አድማውን የጠሩት አማዞን ባለፈው እሑድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረውን የአሠሪ እና ሠራተኛ ውል ድርድር ችላ ብሏል በሚል ነው። በአድማው የሚሳተፉት በኒው ዮርክ፣ ካሊፎርኒያ፣ ኢሊኖይ እና ጆርጂያ በሚገኙ የአማዞን የሸቀጥ ማከማቻና ማደራጃ መጋዘኖች የሚሠሩ ሠራተኞች መኾናቸው ታውቋል። አማዞን በበኩሉ አድማው በሥራው ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ብሎ እንደማይጠብቅ አስታውቋል። የሠራተኛ ማኅበሩ በአሥር የአማዞን መጋዘኖች የሚገኙ 10 ሺሕ ሠራተኞችን እንደሚወክል አስታውቋል። አማዞን በአጠቃላይ በዋና ዋና ቢሮዎችና መጋዘኖች የሚሠሩ 1.5 ሚሊዮን ሠራተኞች አሉት፡፡ ዛሬ አድማ የመቱት በሳን ፍራንሲስኮ፣ ካሊፎርኒያ መጋዘን ውስጥ የሚሠሩ እንዲሁም በሌሎች አራት ግዛቶች ውስጥ የሚገኙና ሸቀጥ ለሥርጭት በሚያዘጋጁ ጣቢያዎች ውስጥ የሚሠሩ መኾናቸው ታውቋል። በሌሎች ሥፍራዎች የሚገኙ የአማዞን ሠራተኞችም አድማውን ለመቀላቀል ዝግጁ መሆናቸውን የሠራተኛ ማኅበሩ አስታውቋል። ሸቀጡን የሚያጓጉዙ ሾፌሮች የኩባንያው ተቀጣሪዎች ሳይሆኑ፣ ለሦስተኛ ወገን የሚሠሩ መሆናቸውን አማዞን ይገልጻል። የአክሲዮን ገበያ ዛሬ ማለዳ በተከፈተበት ወቅት የአማዞን ድርሻ በአንድ በመቶ ከፍ ብሏል። Read more